Get Mystery Box with random crypto!

ደብዳቤዎች ❤💖

የቴሌግራም ቻናል አርማ monhappy — ደብዳቤዎች ❤💖
የቴሌግራም ቻናል አርማ monhappy — ደብዳቤዎች ❤💖
የሰርጥ አድራሻ: @monhappy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ዛሬ ካልሆነ ነገ ይሆናል። ነገ ካልሆነ ከነገ
ወድያ ይሆናል።እሱም ካልሆነ ደም
አንድ ቀን መሆኑ አይቀርም..ብቻ ተሰፈ
አትቁረጥ..መውድቅ እንዳለ መነሳትም አለ..
መዋረድ እንዳለ መክበርም አለ..
እግዛብሔር እምትወዱትን ህይወት ይስጣቹ..
Cross @BINCJ90 For Spam @BINCJ90_bot
Techmare gp @Durye_fitu

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-11 21:19:18 https://youtube.com/channel/UCU5hBSqekCmk-cEd-4JhvcA
815 views Jack , 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 20:52:05 "ናፊባ"
ክፍል ~ አንድ

#አዲስ አበባ ፒያሳ
..ኦልድ ታውን(Old Town Bar & Restaurant)
የጣራው ስር መናፈሻ ነፋሻማነቱ ደስ ይላል። ጨረቃዋ በግማሽ ለመድመቅ ከኮከቦቹ ጋር የፅሐይን መጥለቅ ብቻ አሰፍስፋ ትጠብቃለች። ፍም የመሰሉት የምዕራብ ሰማዮች የምድርን አተካራ ለጥቃ የምትሰናበተውን ፅሐይ ለማስገባት አጅበዋታል። ይሄን ሁሉ ትዕይንት ፊትለፊቱ ካለ የቤት መስታወት ነው የሚመለከተው። "ምነው ወዳጄ ፍዝዝ ብለህ ቀረህ ምን እያየህ ነው?"አለ ዮዳሄ የጓደኛውን የመስፍንን አይን የሳበውን ትዕይንት ለመመልከት እየዞረ። መስፍን አንገቱን ነቀነቀና "ምንም ዝም ብዬ ፊት ለፊት ስመለከት በመስታውቱ ውስጥ ሰማዩን እየቃኘሁ ነበር"አለና የሚጠጣውን የሐበሻ ጃምቦ አንስቶ ችርስ አለው" ጠርሙሶቻቸውን ከፍ አድርገው"ችርስ ችርስ "ተባባለው ጠጡ።
ማዶ ጃንጥላው ስር በከፊል ጡቶቿን አጋልጦ ያሰጣ ልብስ ለብሳ የጭኖቿን ብርቱካናማነት የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ለብሳ ከሎሚ የነጡ ተረከዞቿና በአንደኛው እግሯ ላይ አሳርፋ አራዳዋን የምትልፍ አንዲት ሴት ፊት ለፊታቸው ተቀምጣ መስፍንና ዮዳሔን ትገላምጣለች። ነገር ግን አንዳቸውም ሊያይዋት አልቻሉም።
"ሁለታችንም የሚያመሳስለን ነገር አለ። ግን እስከመቼ ድረስ ነው በዚህ ኮንዲሽን የምንቀጥለው?"አለ ዮዳሔ ሁለቱንም እጆቹን አገጩ ላይ አስደግፎ " አላውቅም ዮዳሔ አታስጨንቀኝ ውስጤ ላይ የሚላወሰው ጥያቄ ይበቃኛል። አንተ ደግሞ አትጨምርብኝ እንጅ"አለና መስፍን ጃምቦውን ጭልጥ አድርጎ ጠጥቶ አስተናጋጇን ጠርቶ እንድትደግመው አዘዛት። ዮዳሔ ዝም ብሎ ተመለከተውና "ግን በእውነት ምንም ሊገባኝ አልቻለም ምን ሆነህ ነው ከእኔ የተለዬ እንደዚህ ያደረገህ ከቀን ወደቀን እየተቀየርክብኝ ነውኮ" "አንተ ላይ ብቻ አይደለም የተቀየርኩት ወዳጄ ራሴም ጭምር ላይ ነው የተለወጥኩት። አሁን ዝም ብለህ ጥያቄህን መጠየቅ አቁምና ጠጣ። ቀኑ ቅዳሜ ነው የቤቱ ቫይቭ ደግሞ ደስ ይላል። እዚህ እንስከርና ወርደን እንጨፍራለን"አለ መስፍን ፊቱ እንደተኮሳተረ "እሺ በቃ ጓደኛዬ "አለና ዮዳሔ ከፍ አደረገለትና ጠጥቶ "ሽንት ቤት ደርሼ መጣሁ"ብሎ ሄደ። መስፍን ዙሪያ ገባውን እያማተረ ሳለ ፊት ለፊት ከተቀመጠችው ልጅ ጋር ተፋጠጠ፡። ጠቀሳት ጠቀሰችው ሄዶ እንድትቀላቀላቸው ጠየቃት ተስማምታ ሶስተኛ ወንበር ስባ ተቀመጠች። ዮዳሔ ሲመጣ ደንግጦም ደስ ብሎትም "ከየት አገኘኻት ባክህ ብሎ ተቀመጠ። "ያው ብቻዋን ስለሆነች እኛም ብቻችንን ስለሆንን ከሁለት ሶስት መሆን ይሻላል ብዬ ጋበዝኳት እሷም ተስማማች"አለ መስፍን። "ጥሩ ነው ያደረከው "አለና ዮዳሄ ወደ ልጅቷ ፈገግ ብሎ ጠጋ ብሎ" እንተዋወቅ ዮዳሔ እባላለሁ። እሱ ደግሞ ብሎ ወደ መስፍን ሲዞር ገላመጠው በዚህ ጊዜ አንድ ነገር አስታወሰ"በፍፁም መጠጥ ቤት ላገኘኸው ሰው ሙሉ ራስህን ማስተዋወቅ የለብህም። የመጠጥ ቤት ስም ሊኖርህ ይገባል። እኔ ለምሳሌ በረከት በሚል ስም ነው የምተዋወቀው። የሚፈጠረው አይታወቅም አንተን የሚያጠቃህ ሰው ሰው የሚልክብህ ስምህን ነግሮ ነው ስለዚህ አንተም ስም ሊኖርህ ይገባል! ኧረ አሻፈረኝ ካልክ አይመለከተኝም ነገር ግን እኔን ለሰው ከማስተዋወቅህ በፊት ለማላቀው ሰው የምተዋወቅበትን ፌክ ስሜን መዘንጋት የለብህም"እንዳለው አስታውሶ " እ እሱ ደግሞ በረከት ይባላል "አለ ና የእሷን ስም ጠየቃት። "እኔ ሒወት እባላለሁ!" "ጥሩ ስም ነው በቃ እንጫወት ቆንጆ" ብሎ ብርጭቆውን ከብርጭቆዋ ጋር አጋጭቶ ፉት አለ። ጨዋታቸውን እያደሩ መጠጡም እየበዛ ሄደ።ጣራው ያለውን ነፋሻማነት እንደ እርጎ ከሚገመጠው ጃምቦ ጋር እያጣጣሙ እያለ ጃምቦ አልቋል ተብለው ታች ወርደው ክለቡን ተቀላቀሉ። ቆሞ የሚጠጣ ሞልቷል። የዘፈኑ ድምፅ ከቤቱ አልፎ ውጭ ላይ ይሰማል። የጨፋሪው ተከታይ ዜማ ለጉድ ነው።መስፍን ሒወትና ዮዳሔ እየጨፈሩ ባለበት ሽንት ቤት ደርሶ ሲመለስ ነፍሳቸውን አያውቁም። የሒወትና የዮዳሔ በፍጥነት መግባባትና መመቻቸት እያስገረመው ሙዳቸውን ላለመረበሽ ሒሳብ ከፍሎ ትቷቸው ወጣ።
ሒዎትዮዳሔ ለብዙ ጊዚያት የሚተዋወቁ ጓደኛሞች እንጅ ከስአታት በፊት የሚተዋወቁ አይመስሉም። ሰውነታቸው በላብ እስኪጠመቅ ድረስ ሲጨፍሩ ቆይተው ሲመለሱ መስፍንን ከቦታው አጡት። "እንዴ በረከት የት ሄደ?"አለች ሒዎት ቀድማ "አላውቅም። ምንም አልነገረኝም" "እንዴት ሳይነግርህ ይሄዳል? ነው ብቻውን ስለሆነ ደብሮት ነው?"አለች ሒዎት። "አይ እይደዛ አይደለም። ብቻውን ሆነ አልሆነ ግድ የለውም።በቃ ተይው እኛ እንዝናና አለና በጆሮዋ የሆነ ነገር አንሾካሾከላት፣ ከት ከት ብላ ሳቀችና ቶርክ መቶረክ ጀመረች። ዮዳሔ ወገቧን ይዞ ኤግለስ ያስጨፍራት ጀመር። "የአጨፋፈር አይነትና ጭፈራ ግን አንተ ጋር ነው ያሉት"አለችው ጆሮው ስር ተደግፋ "አመሰግናለሁ አንቺም በጣም ጎበዝ ጨፋሪ ነሽ ተመችተሽኛል"አላት "እኔም አመሰግናለሁ ሒሳብ እንክፈልና እንውጣ?!"አለች ሒወት "እሺ "አለና አስተናጋጇን ጠራት። ሒሳብ ለመክፈል እርስ በእርስ እየተገላገሉ ሳለ አስተናጋጇ "ሒሳብ ተከፍሏል። ጓደኛችሁ ነው ከፍሎ የሄደው እና ይቺን ወረቀት ደግሞ ለአንተ እንድሰጥህ ሰጥቶኛል "ብላ የተጠቀለለችውን ወረቀት ሰጠችው። ዮዳሔ ጥቅሏን ቀስ አድርጎ ፈታና አነበባት "ወዳጄ ራስህን ጠብቅ ጥንቃቄ ማድረግህን እንዳትረሳ። አገኘሁ ብለህ ዝም ብለህ ዘው እንዳትል ነግሬሀለሁ!"የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ነበር። ዮዳሔ ሳቅ አለና ወረቀቷን ጨምደድ አድርጎ ወደ ኪሱ አስገባት። "ምን ብሎህ ነው?" "ተይው ባክሽ ዝም ብሎ ነው"አለ እየሳቀ "ገብቶኛል።ተወው"አለች ሕሊና ፈገግ ብላ። "እሺ ከገባሽ ጥሩ እና "መሀል ሆቴል" ጋር አልጋ ብንይዝ አይሻልም ትያለሽ?" "አዎ ደስ ይለኛል ግን እስካሁን አያልቅም?" "እንጃ የሚያልቅ አይመስለኝም።ቸክ አድርገን እዛው አካባቢም መያዝ እንችላለን"አላትና ወጡ። በሲኒማ አምፒር ታጥፈው የግሪክ ቤተክርስቲያንን በግራ ትተው ተሻግረው መሀል ሆቴል ጋ ደረሱ። የእንግዳ ተቀባይዋም በስነስርዓት ከተቀበለቻቸው በኋላ አንድ አልጋ ብቻ እንደቀረ ነግራቸው ከፍለው ቁልፍ ይዘው ገቡ።
****
<በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን - አይተውት አለፉ››
የሚል የቀዬ እርዚቅ
የሚል የሰው ግጥም የሚል የአበሽ ቅኔ
ልብ አውቃዬ ሆኖ
ልክ እንደ አገር መዝሙር እንዳልዘመርኩ እኔ
ከአፍታ ዕድሜ በኋላ
የሆነውን ሁሉ ታሪኬን ቀየርሽው
ከትናኝ ከልለሽ
ከብናኝ አራግፈሽ ወስደሽ ልትፈውሽው
ሰው አይቶ ያለፈውን
የጣልኩት ራሴን - አየሁ ስታነሽው!!
ይህን እኔ ያየሁ
ሰርክ እንዲህ እላለሁ፤
እንኳ ራስን ጥሎ - ገፍቶ ጣይ ባለበት
ሰው በሰው ላይ ሊያሴር - በሚማስንበት
በዚህ ከይሲ ዘመን - በዚህ የክፋት ዓለም
ሰው ራሱን ሲጥል
እያለፉ መሄድ - የሚገርም አይደለም፤

እልፎች ራስ ጥለው - ተስፋ ሲቆልፉ
እልፎቹም ገፍተረው - እየጣሉ ሲያልፉ
ነገር ግን
ከአመድና አቧራ - ከደይን የሚያነሱ
ድንገት ተወርውረው - ለጭንቅ የሚደርሱ
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ !!
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ!!"ብሎ በውብ አነባበብ ግጥሙን አነበበላት ተሕሚድ

ሼር
@monhappy
@monhappy

የደራሲው ቀደምት ስራዎች
#መቅደላዊት
#ኤሴቅ
1.0K views Jack , 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 20:41:30 Hi endat nachu @BINCJ90
763 views Jack , 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-13 10:18:16 ፡ የሰካራሙ ሰው ደብዳቤ
( ቁጥር 1129 )

እንደ እብድ ነው እምታየኝ…እማወራው ብዙውም እንደማይገባት አውቃለው…በዛም ላይ ጥያቄዋችዋ አይልቁም…ቀጠለችም…የመጀመሪያው ንሰሀ መፀፀት ነው…!አቦ ለእናተ ግን ፈጣሪ ያጣችሁትን ይስጣቹ
@monhappy
@BINCJ90
2.1K views Jack , 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 09:28:14 የጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር "Luigi Di Maio" ስለ ፈረንሳይ እንዲህ ይላል!
"....ፈረንሳይ አፍሪካ ውስጥ ያሏት ቅኝ የተገዙ ሃገራትን ባትይዝ ኖሮ የዓለማችን ምናልባትም 30ኛው ኢኮኖሚ ትሆን ነበር! ነገር ግን የአፍሪካ ሃገራትን በመያዟ እና ከቅኝ ግዛት በኃላም በተዘዋዋሪ በቀኝ ግዛቷ ስር እነዚህ ሃገራት እንዲቆዩ በማድረጓ ምክንያት አሁን ላይ ኢኮኖሚዋ የዓለማችን 7ተኛ መሆን ችሏል! ፈረንሳይ ካለ አፍሪካ ተራ ሃገር ናት!..."
በአጭሩ እነዚህ የአፍሪካ ሃገራትን የሚመሩ ግለሰቦች የፈረንሳይን ጥቅም ማስጠበቅ ካልቻሉ በዚህም በዚያም ይወገዳሉ! ጥቅሟን የሚያስጠብቁ ከሆነ ደግሞ አንደላቃ ታኖራቸዋለች!
ማሳያ!
"Elf" የተባለው የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ታማኝ ለሆኑ የአፍሪካ መሪዎች ረብጣ ጉቦ እና ቆነጃጂት ቅምጦችን ይሰጥ እንደነበር እ.ኤ.አ 1994 ላይ ተጋልጧል! ስለ "Elf scandal" ማንበብ ትችላለህ! በየዓመቱ ለነዚህ መሪዎች 15 ሚልዮን ይሮ ወጪ ይደረግ ነበር!
ሴኔጋላዊው ሙዚቀኛ "Akon" አንድ ቃለ መጠይቁ ላይ "....ፈረንሳይ ሁሉንም ነገር መውሰድ ትወዳለች! መስጠት የሚባል ነገር ግን አታውቅም! የዛሬ ሶስት እና አራት መቶ አመታት መጥተው የዘረፏቸው የአፍሪካ ሃገራት አሁንም ድረስ አንድ ኢንች ወደፊት ፈቅ ማለት አልቻሉም!...." ይላል!
ማጠቃለያ!
ይህንን የፈረንሳይ "Monetary colonization" እና "Colonial tax" ያጋለጠችሁ የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር "Arikana Chihombori" ምን እንደተደረገች ታውቃለህ?
ገምት?
.
.
.
"የዛሬ ሁለት አመት በአፍሪካ ህብረት ቀጭን ደብዳቤ ተባራለች!"
ያባርራት ማን እንደሆነ ታውቃለህ?
የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚንስትር እና አዲስ አበባ ያስቀመጥነው የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር "Musa Faki Mahamat"!
በነገራችን ላይ 26 የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ፈረንሳይኛ ይነገራል! ከዚህ ውስጥ 20 የሚሆኑት የስራ ቋንቋቸው ፈረንሳይኛ ነው! በ 2050 ከዓለማችን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውስጥ 80% የሚሆነው የሚገኘው አፍሪካ ውስጥ ይሆናል! (Projection ነው! የቀኝ ግዛት projection)
መልካም ቅዳሜ! ፈካ፣ ዘና፣ፀዳ ያለ ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

@monhappy
@BINCJ90
1.8K views Bĩnyam , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 09:28:14 የቅዳሜ ቀደዳ 29-(፳፱)
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? ወደ ቅዳሜያችን ተመልሰናል! እስቲ አንድ ፅድት ያለ ነገር ላጫውትህ!
.
.
.
ምን መሰለህ?
14 የአፍሪካ ሃገራት ለረጅም ዘመናት ተገደው ስለሚቀልቧት አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ሳስብ ይደንቀኛል!
እ.ኤ.አ ከ 1960ዎቹ በኃላ አውሮፓውያኑ አፍሪካን ተገደውም ሆነ ወደው መልቀቅ የጀመሩበት ግዜ ነበር! ታድያ በዛን ወቅት እንግሊዝን በቅኝ ግዛት ትገዳደራት የነበረችው ፈረንሳይ መካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ እና አንዳንድ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት የግሏ ነበሩ!
ፈረንሳይ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራትን ለቃ ስትሄድ ሃገራቱን "PACT: for the continuation of colonization" የሚባል ስምምነት እንዳስፈረመቻቸው ይነገራል!
ስምምነቱ በአጭሩ እንዲህ ይላል!
"....በቀኝ ግዛት በያዝኳቹ ግዜ ፈረንሳይ ለእያንዳንዳችሁ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን አፍስሳለች! ትምህርት ቤቶችን ሰርተናል፣ መንገድ እና ሆስፒታሎችን ገንብተናል፣ ብዙ የመሰረተ ልማት አውታሮችንም ዘርግትናል! ስለዚህ ነፃነታችሁን የምትፈልጉ ከሆነ በግዴታም ይሁን በውዴታ ይህንን ስምምነት መፈረም ይኖርባችኃል! ለእያንዳንዳችሁ ሃገራት ፈረንሳይ "CFA franc" የሚባል የመገበያያ ገንዘብ ትሰጣችኃለች! የምትገበያዩት በዚህ ገንዘብ ብቻ ይሆናል! የገንዘቡን ህትመት የምትቆጣጠረው ፈረንሳይ ብቻ ናት! እያንዳንዳችሁ የሃገራችሁን 85% የሚሆነውን ገንዘብ(reserve) የምታስቀምጡት የፈረንሳይ ማዕከላዊ ባንክ ይሆናል! እናንተ ጋር መቀመጥ የሚችለው 15% የሚሆነውን ብቻ ነው! ከዚህ የበለጠ ገንዘብ የምትፈልጉ ከሆነ የፈረንሳይን ፍቃድ መጠየቅ ይኖርባችኃል! 85% የሚሆነውን የሃገራችሁን "reserve" የፈረንሳይ የገንዘብ ሚንስትር ያስተዳድራል!...."
ይቀጥላል!
"....ምንም አይነት የጦር መሳርያ የምትፈልጉ ከሆነ መግዛት የምትችሉት ከፈረንሳይ እና ፈረንሳይ ብቻ ነው! የሃገራችሁን መከላከያ ማሰልጠን የምትችለው ፈረንሳይ ብቻ ናት! ከፈረንሳይ ፍቃድ ውጪ ከየትኛውም ሃገር ጋር የጦር(ወታደራዊ) ስምምነት መፈፀም አትችሉም! የፈረንሳይ ጦር እንደፈለገው ሃገራችሁ ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላል!
በሃገራችሁ ውስጥ የሚካሄድ ማንኛውም ጉዳይ የፈረንሳይ መንግስትን ጥቅም አደጋ ላይ የጣለ መስሎ ከተሰማን ፈረንሳይ ወታደሮቿን ልካ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ትችላለች! የእያንዳንዳችሁ ሃገራት የስራ ቋንቋ ፈረንሳይኛ መሆን አለበት! ሃገራችሁ ውስጥ ተቆፍሮ የወጣው ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ተቆፍሮ የሚወጣውም የተፈጥሮ ሃብት በቀደምትነት መሸጥ ያለበት ለፈረንሳይ ነው! የሃገሮቻችሁ የውጪም ሆነ የንግድ ፖሊሲ ለፈረንሳይ መንግስት በሚስማማ መልኩ መቀረፅ አለበት!..."
ጌታዬ! ይህ ስምምነት ፈረንሳይ 14 በቀኝ የገዛቻቸውን የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሃገራትን ለቃ ስትሄድ ያስፈረመቻቸው ነው! ሃገራቱ ቤኒን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሴኔጋል፣ ኮትዲቯር፣ ማሊ፣ ኒጀር ፣ ቶጎ፣ ካሜሩን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጊኒ ቢሳኡ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ እና ጋቦን ናቸው!
ይህ ስምምነት እውነት እንደሆነ ደግሞ የቀድሞዋ የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር "Arikana Chihombori" ትናገራለች።
አባዬ! ፈረንሳይ "colonial Tax" ትለዋለች! በሌላ አጠራሩ "Monetary colonialism" ይባላል!
ገራሚ ሃቅ አንድ!
እነዚህ 14 ሃገራት ፈረንሳይ በሰጠቻቸው እና በምትቆጣጠረው "CFA franc" የሚባል የመገበያያ ገንዘብ እንዲጠቀሙ ተደርጓል!
ገራሚ ሃቅ ሁለት!
የእነዚህ ሃገራት 85% የሚሆነው የገንዘብ ክምችት ፈረንሳይ ማዕከላዊ ባንክ ይቀመጣል! ሃገራቱ መጠቀም የሚችሉት 15% የሚሆነውን ብቻ ሲሆን ከዛ ያለፈ ካስፈለጋቸው ፈረንሳይ መፍቀድ አለባት! እንደ አምባሳደሯ ገለፃ ፈረንሳይ ይህንን ገንዘብ ወደ "Stock market" በራሷ በማስገባት በአመት ወደ 500 ቢልዮን ዶላር ታገኝበታለች! ይህንን ገንዘብ ደግሞ መልሳ ለነዚህ ሃገራት በወለድ ታበድረዋለች! (በአጭሩ እነዚህ 14 ሃገራት በየአመቱ ለፈረንሳይ 500 ቢልዮን ዶላር ያስገባሉ!)
በነገራችን ላይ የነዚህ ሃገራት ነዳጅ፣ ጋዝ፣ ወርቅ፣ ዳይመንድ ወ.ዘ.ተ የሚጋዘው ወደ ፈረንሳይ ነው!
"Areva" የሚባለው የፈረንሳይ የኑዩክለር አምራች ኩባንያ ግብዓት የሚሆነውን "Uranium" 100% የሚወስደው ከ "Gabon" ነው!
"Total" የሚባለው የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያም የሚሰራው ተመሳሳይ ነገር ነው! በአንድ ወቅት የ "Gabon" ፕሬዝዳንት የነበሩት "Omar Bongo"
"....ጋቦን ከፈረንሳይ ውጪ ሹፌር የሌለው መኪና ስትሆን፣ ፈረንሳይ ያለ ጋቦን ደግሞ ነዳጅ የሌለው መኪና ናት!..." ማለታቸው ይታወሳል!
የፈረንሳይን ተዘዋዋሪ ቀኝ ግዛት የተቃወሙ የነዚህ ሃገራት መሪዎች ታሪካቸው ግድያ ወይ መፈንቅለ መንግስት ነው!
ፈረንሳይ እ.ኤ.አ ከ 1962 እስከ 1995 ባሉት 33 አመታት 19 ጊዜ በአፍሪካ ሃገራት የፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ በግልፅ ገብታለች!
እ.ኤ.አ ከ 1960 ጀምሮ ደግሞ 40 ግዜ በአፍሪካ ጉዳይ ወታደሮቿን ጣልቃ አስገብታለች!
እ.ኤ.አ ከ 2010 ጀምሮ ብቻ ብትቆጥር ሊብያ፣ ማሊ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ እና ኮትዲቯር የመሳሰሉ ሃገራት ውስጥ የተካሄዱ የመንግስት ግልበጣዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፋለች!
ግልፅ ምሳሌዎች!
"Mali" ነፃነት ባገኘች ማግስት የመጀመርያው የሃገረቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት "Madibo keita" ሃገሩ ከፈረንሳይ ጫና እንድትወጣ እና የፈረንሳይን ተፅህኖ ለማስቆም ሲያስቡ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግባቸው እና ከዛም በእስር እያሉ እንዲሞቱ ፈረንሳይ አድርጋለች!
"Tomas Sankara" ሃገሩ "Burkina Faso" ከፈረንሳይ ጫና እንድትወጣ ጥረት ማድረግ ሲጀምር እና አዝማሚያው አላምር ሲላቸው መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት እ.ኤ.አ 1987 ላይ እንዲገደል ሆኗል!
እ.ኤ.አ 1963 ላይ የቀድሞው የ "Togo" ፕሬዝዳንት "Sylvanus Olympio" አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ለሃገሪቱ ህዝብ ለማስተዋወቅ ሲሰናዳ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት፣ በንጋታው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሎ ሬሳው "Togo" የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ እንዲጣል ተደርጓል!
የ "Benin" ፕሬዝዳንት የነበሩት "Hubert maga" እና የ"Libya"ው "Gadafi" መወገድ ጀርባም ፈረንሳይ አለች!
አሁን እንኳን የኮትዲቯር መንግስትን ደግፋ ስልጣን ላይ ያስቀመጠችው ፈረንሳይ ናት! አባዬ! እንደምታውቀው ደግሞ ፈረንሳይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ "ቡና" እና ለቸኮሌት ግብዓት የሚሆናትን "Cocoa" የምትገዛው ከኮትዲቯር ነው።
ጌታዬ! የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝድንት "Jacques Chirac" ያሉትን ታስታውሳለህ?
"....We have to be honest and acknowledge that a big part of the money in our banks comes precisely from the exploitation of the African continent!... "
1.2K views Bĩnyam , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 09:28:13
936 views Bĩnyam , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 09:28:13
909 views Bĩnyam , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 09:28:13
897 views Bĩnyam , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-02 20:31:15 የፊሊሞን ደብዳቤዋች

እነዛ ቀኖቶች እኮ አልፈዋል…እማያልፉ እሚመስሉት…ነገ የሌላቸው እሚመስሉት ቀናቶች ተከናንበው ሄደዋል…



@monhappy
@itsmehappy
1.2K views Bĩnyam , 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ