Get Mystery Box with random crypto!

Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

የቴሌግራም ቻናል አርማ mohamossen — Moha Mossen መሐመድ ሐሰን M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mohamossen — Moha Mossen መሐመድ ሐሰን
የሰርጥ አድራሻ: @mohamossen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.19K
የሰርጥ መግለጫ

መሐመድ ሐሰን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-26 11:27:41 አንድ ልምራ ባይ ነው አሉ ... እናም ጎረቤቶቹን ከየቤታቸው እያንኳኳ ጠርቶ ሁሉንም ሰዎች ሜዳ ላይ ሰበሰባቸው። ከሰበሰበ በኋላ "በሉ አሁን እያንዳንዳችሁ እጅ እያወጣችሁ የተሰበሰብንበትን ዓላማ" ንገሩኝ’’ አለ አሉ። ይህ ልምራ ባይ ሕወሓትን ያስታውሰኛል።
.
.
አሁንም ሂዊ ወጣቱን ከያለበት አሳዳ፣ አሰልጥናና አስታጥቃ ... ተንኩሳ ከተኮሰች በኋላ የቀሩትን ሰብስባ: "በሉ እንግዲህ አሁን ክላሻችሁን እያወጣችሁ ለምን እንደምንዋጋ ንገሩኝ" የምትል የምድራችን ጉድ ናት።
.
.
የህወሐት ዓላማ ምን እንደነበር፣ ለማንና ለምን እንደሚታገል የሚያስረዳኝ ከተገኘ የጠየቀኝን ሁሉ በወሮታነት አቀርባለሁ።
390 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:28:47 ሂዊ እኮ የምታደርገውን አታውቅም! #ከነዳጆቿ ላይ ነዳጅ ሰረቀች ነው የምትሉን? የነዳጇን ነዳጅ ሰርቃ በምኗ ልትንቀሳቀስ ነው
418 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:06:35
ይህንን #ውድና_የተከበረ ሀይል:
ማገዝ ያልቻለ አይገዝግዘው፣
ማክበር ያልቻለ አይክበርበት! አያዋርደው! በስሙ አይነግድ!
ቁስሉን መረዳትና ማከም ያልቻለ ቁስሉን ደጋግሞ አይውጋው! አይደለም ለትችትና ነቀፌታ ለማወደስም ገና ሩቅቅ ነን።
#ክበርለ እናንተ ለፀጥታ ሀይሎች በሙሉ ይሁን።
#ኢትዮጵያዊነትአሸናፊነት
420 views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 11:20:40 #መንግስትንና #ወያኔን አንድና ያው በሆነ እኩል ሚዛን ላይ አስቀምጦ መስፈርና መደምደም ሀገርን ድጋሚ እንደመድፈር ነው። እንዲህ ያለው ድምዳሜ አንድም #የድንቁርና፣ ሁለትም #የባንዳነት፣
አለያም የከርሳቸውን ጥልቀት ከማስረገጥ ውጪ፣ እንዲህ ያለው ድምፅ ውስጡ ሰላምም፣ የሰላም ፍላጎትም፣ ሰላማዊነትም፣ ጤነኛነትም የለም። እውነት የራቃቸው▮ከሰላም ጋር የማይተዋወቁ ግፈኞች ቅጥፈትም ነው።
449 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:04:21 #እያለቀስንና #እያነከስን ወደ መፍትሄው ተራራ ከመውጣት ውጪ፣ የአረመኔዎቹ ቃል አቀባይ መሆን ወደከፋው ሁሉ የሚያደርስ ነው
222 views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:03:53 #በውግዘት___ስም ❸
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
“ደላንታ የሚባል ሀገር አንድ እጅግ ሀብታም፣ ሀይለኛና ህዝብ የሚያደንቀው ትዕቢተኛ ሰው ነበር።” ይሉናል ሊቁ ኅሩይ ወልደሥላሴ «የለቅሶ ዜማ ግጥም» በሚል መፅሐፋቸው። ያ ሀብታምና ኅይለኛ ሰው እንደልቡ፣ ሲያስከትል፣ ሲያዝ፣ ሲያስፈፅምና ያሻውን በትዕቢት ሲያደርግ ያስተዋሉ አንድ የሀይማኖት መምህር ወደቤቱ መመላለስና ቀስ በቀስ የመጽሐፍ ቃል ያስተምሩት ጀመሩ። ለዘመናት የገነባው የትዕቢት ዓለት እያደር ተፈረካከሰ። አምላኩም ረድቶት ከልጅነቱ እስከ ዐዋቂነቱ የሰራው ግፍ ወለል ብሎ ታየው። ከዚያ ደግሞ በዚያ ትዕቢቱ የተነሳ እሳቱ የማይጠፋ፣ ትሉ የማያንቀላፋ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ያለበት ሥፍራ ከሞት በኋላ እንደተዘጋጀለት ታወቀውና እንዲህ ብሎ አለቀሰ...
“የወንድሜ ራሱ ጉተናው አማረ
እኔም ባልተሰራኹ ይሻለኝ ነበረ።”
#ማውገዝ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከልጅነት እስከዕውቀታችን፣ በየሥርዓቱና በየዘመኑ፣ በየምክንያቱና በየሰበቡ፣ ብዙ ሕይወት ሲቀጠፍ፣ ብዙ ደም ሲፈስ፣ ብዙዎች ሲፈናቀሉና ተስፋቸው ሲፈጠፈጥ የዚህን ሁሉ ግፍ ሥረመሰረት አስተውለን፣ እንደ ደላንታው ትዕቢተኛ “ምነው ባልተሰራሁ! ምነው ይህንን ባልሰራሁ? ምነው ይህንን ባላደረግን ብለን ወደራሳችን ጠቁመን፣ የማያዳግም መፍትሔ እንደማምጣት፣ ልክ እንደአባቶቻችን እኛም ጣታችንን ወደሌሎች መቀሰሪያ “ውግዘት” የተባለች ዘመናዊ ከ“ከደሙ ንጹሕ ነኝ” የምንልባት መንገድ ቀይሰናል።

1. ቃሉ ገብቶናል
በመሰረቱ ሊቁ ዐለቃ ደስታ ተክለወልድ “አወገዘ” የሚለውን ቃል ሲፈቱት ፤ “ገዘተ፣ ክፉ ሥራን፣ ክሕደትን ከለከለ፣ ተው አለ ፤ እንቢተኛን ፡ ከሕዝብ አንድነት ፡ ለየ ፡ ወገደ...” ነው ይላሉ። መለየት የምትለዋ ቃል... አንድ ሰው ሌላውን በአንድ ተግባር ለማውገዝ፣ እሱ ከዚያ ሥራ ነፃ መሆኑንና ከ“ደሙ ንፁህ” መሆኑን ማረጋገጥ ይገባዋል። በቀላል አማርኛ አውጋዥ፣ ራሱ ተወጋዥ አለመሆኑን ያውቃል ወይ? ነው።
በዚህ ሁሉ ምስኪን ህዝብ ደም ውስጥ ምንም አላዋጣንም?
በቃልም?
በተግባርም?
በጥላቻ ንግግርም?
ግጭት በማማባስም?
ያልገባን ነገር ውስጥ ተሳትፈን በመፈትፈትም?
በአንድም ይሁን በሌላ፣ በቃልም ሆነ በግብር፣ በማስፈፀምም ሆነ በትብብር፣ ጥፋትን ወደብሔርና ሀይማኖት በመለጠጥና እሳቱን ወደ ሰደድ እሳት በመቀየር... አልተሳተፍንም ወይ?

2. የውግዘት አዙሪት
ግፍ ሲፈፀም... በቅንነት ከሚጮኹት ይልቅ ድምፃቸው ጣሪያ የሚበጥሰው የሟቾችን እምነትና ብሔር እያረጋገጡ የሚጮኹት ናቸው። ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ፀጥ ያሉ መስጊድ ሲቃጠል ድምፃቸው ይጠነክራል፤ መስጊድ ሲቃጠል ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚዳክሩት ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ሀገር ካልፈረሰ ይላሉ። ብሔሩም ከሀይማኖቱ ጋር እየተቀየጠና እየተናበበ፣ ሬሳውን እየቆጠረ... ለራሱ በአባላት እና ደጋፊዎቹ መጮህ ማስጮህ... ለሌላው ሲሆን ዝም ጭጭ ማለትን ዓመሉ ካደረገ ከራረመ። ለምን በጋራ አይወገዝም ሲባል... የኔ ሲገደል እሱ ዝም ብሏል፣ የኔ ሲቃጠል የት ነበራችሁ... ይባባላል በየተራ። ይሄ የውግዘት ቅብብል ... የውግዘት አዙሪት ስር ቀረቀረን እንጂ ምን ጠቀመን?

3.ከማውገዝ ጠለቅ ያለ እና ፋይዳ ያለው ሚና የለንም?
ሀገራችን ውስጥ ወንጀልና ቅጥ ያጣ ግፍ የገዛ ወገኖቻችን ላይ ሲፈፀም በየተራ ስናወግዝ ነው የኖርነው።
ምን ጠቀመን? ንፁሃንን አተረፍን ወይስ ለሌላ ዙር ግፍ አመቻቸናቸው? ችግሩን ፈታነው ወይስ አባባስነው?
የድርጊቱ ቀጥተኛ ፈፃሚዎችን ፍርድቤት ዳኛቸው እንበል፣ ችግሩ የተፈጸመበት አስተሳሰብ ከማህበረሰባችን ጠፋልን?
ቅራኔዎቻችን ተፈቱ ወይስ ይብስ እየተለያየን መጣን?
ጉዳዩን የፈፀምነው ወይም ያወገዝነው ከሆነ ብሄር ጥላቻ ከሆነስ... ያ ብሄር ምን ይደረግ?
እናጥፋው?
አንድ ሀይማኖት ላይ ጣታችንን ከቀሰርንስ ያ ሃይማኖት ምን ይደረግ? በሕገመንግስት ይታገድ?
.
.
#ውግዘት ግቡ ግራ የሚያጋባ ድርጊት ነው። ስር የለውም። ንዴትን፣ ጥላቻን፣ እልህን በተቃውሞ ስም የምናወጣበት... እጅም እግርም የሌለው ጊዜያዊ እፎይታ እንጂ እረፍት አይደለም። ስንሮጥ እንታጠቀዋለን ስንሮጥ ይፈታል። ትናትን በሰፈርንበት ግፍ ዛሬ ደሞ እንሰፈራለን። ግን እንደትውልድ፣ የተሻለ ዘላቂ መፍትሔ ማቅረብ አለብን... ይገባናል... ደግሞም እንችላለን!!
.
.

#ማስታወሻ_ለሀይማኖቱ…
ውግዘት እንኳን ፊደል ለቆጠርነው ለሀይማኖት ሰዎችም ዛሬ ላይ አይሰራም። እነሱም የሞራል ስራቸውን በአግባቡ መስራት ትተው በፖለቲካ ድንኳን ውስጥ የሚጋፉ ሆነዋል። እነሱም ቢሆን በአግባቡ የድርሻቸውን ይወጡ። ልብ ማለት ያለብን ዛሬ በሀገራችን የተደገሰውና የሚነገድበት ሞት አንዱና ዋነኛው መጠቅለያው ሀይማኖት መሆኑ ልብ ይሏል።
(እመላለስበታለሁ)
305 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 10:03:52
249 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 10:45:16 #የማውገዝ_ድንኳን_እድምተኞች
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ነገር የተረጋጋ ሲመስል ሰከን ብለን ካወራናት መቼም እንደዚህ ድንኳን እድምተኞች አሳፋሪም፣ አሳዛኝም፣ ኮሚክም ነገር የለም። ደግሞም ድንኳኗ ብዙ ተራ ማጀቢያዎችና አጃቢዎች ይታደሙባታል።
"ለምን አታወግዝም?"
"ሰው ሲሞት አታዝንም ወይ?" ይሉሀል። አስተዛዛኝ መሆናቸው ነው። መፍትሄ ማንገባቸው ነው። የመጀመሪያው ድንቁርና ከዚህ ይጀምራል። እንኳን በግፍና በግፈኞች ለተገደለው ወገኔ ለየትኛው የሰው ልጅ ሞት መቅረብ የሌለበት ቆሻሻ ጥያቄ። የቀሽሞች መደበቂያ ናት። ገዳይና አስገዳይ፣ ደንቆሮና አዋቂ ተቀላቅለው የሚፈሱባት ትቦ።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ #ክላሽ ተደግፈው ተኳሽ የሚያወግዙ ድንዙዞችም ይበዙበታል። ዋናው ጉዳይ ግን ሌላ ነው።
ማን የፈጠረውን ችግር ነው የምናወግዘው
ማውገዝ እንዴት ያለውን መፍትሄ ሊያመጣ ነው
ለመፍትሄው ማን ይስራልን ዝርዝሩና ጥያቄው ብዙ ነው።
ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ የምንሳተፍበት እንጂ በማውገዝ ድንኳን ውስጥ የምንወሸቅበት አይደለም። መጀመሬ ነው። ከመሰሉኝ መፍትሄዎች ጋር እመላለሳለሁኝ። ጥያቄውንና መፍትሄውን ጀምሩት። በማውገዝ ድንኳን ውስጥ አንወሸቅ! ንግዱንም እንጠየፈው። በወገናችን ሰላም ከመስራት ለሰላማችን እንስራ።
317 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 10:44:52
#በኡኡታ እንዳትጠፋ #በእልልታ አትለምልም
▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብም ስለምችል፣ ክላሽ ከያዘው ገዳይ በላይና በበለጠ ሀላፊነት የሚሻውን ብዕር የጨበጥኩ መሆኔን ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። ከርሳም ብዕር እልፍ ገዳዮችን እንደምታፈራና እያፈራች እንደሆነም በአይኔ እያየሁ ነው። ጥንቃቄና ሰው መሆን ካልታከለበት ሁለታችንም ገዳይ እሳት ነው ጨብጠን የምንዞረው። ስለዚህ እልልታ አያሰክረኝም። ኡኡታም አያስበረግገኝም። ሀሳብ ገዳይ ከሰው ገዳይም እንደሚከፋ አውቃለሁና እኩል እጠየፋቸዋለሁኝ።

ወገኖቼ ልመርቃችሁ። አባቴ ያወረሰኝ ውድ ሀብት ነውና በሆዳችሁ አትውደቁ! ለላይክም ሆነ ለዩቲዩብ ዶላር አትንበርከኩ። ለወገን በሚቀርብ መፍትሔ የምትበረግጉ አውሬ አያድርጋችሁ። የሚፈጠፈጡብን ታላላቆቻችንም ልቦና ይስጣቸው። ታናናሾቻቸው የምናፍርባቸው ሳይሆን መከታ የምናደርጋቸው ይሁኑልን።
በተረፈ ለብሽሽቅ ጊዜ የለኝም። እኔን የሚያስጨንቀኝ "ወገኔ እንዳይሞት ምን ላዋጣ?" የሚለው እንጂ በየቀኑ ሰው እየሞተ ከንቱ እልልታ መለቃቀም አይደለም። በወገን ሞት ከመበሻሸቅ የከፋ ግፈኝነት የለም። ደናቁርት እንዲከስሙ ብርሀኑን አዋጡ። ደናቁርት ችግራችን ሳይገባቸው የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ አንጠብቅ። የሚበረግጉትን ትተን ለሰዎች በሰውኛ እንቀጥላለን።
295 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 11:25:21
395 views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ