Get Mystery Box with random crypto!

ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድ መ | ትምህርት ሚኒስቴር

ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ
------------------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት በሚያስቻለቸው ጉዳይ ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ በአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትም ሆነ በአዲሱ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ዲዛይን ላይ የሙያና የተግባር ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብረሃኑ ባለፉት ጊዜያት ሙያዊ ክህሎትና ተግባር በሚጠይቁ ሥራዎች ላይ በሀገር ደረጃ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት እንደነበር ገልፀው ይህንን ችግር በመቅረፍ ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት የሚበጅ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለቸውን ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው እንደ ሀገር ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎች የሚፈለገውን ብቃትና ችሎታ ይዘው እንዲወጡ ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
@MoeEthiopia
@MoeEthiopia