Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ moeethiopia — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ moeethiopia — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @moeethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 318
የሰርጥ መግለጫ

ቀዳሚ የተማሪዎች የመረጃ ምንጭ 🇪🇹
Share and Support us

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-02 21:26:31
ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተገለፀ
------------------------------------

ትምህርት ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት በሚያስቻለቸው ጉዳይ ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለው ትውልድን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ በአዲሱ የአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርትም ሆነ በአዲሱ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ዲዛይን ላይ የሙያና የተግባር ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብረሃኑ ባለፉት ጊዜያት ሙያዊ ክህሎትና ተግባር በሚጠይቁ ሥራዎች ላይ በሀገር ደረጃ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት እንደነበር ገልፀው ይህንን ችግር በመቅረፍ ለቀጣይ ሁለንተናዊ የሀገር እድገት የሚበጅ እውቀትና ሙያዊ ክህሎትን አጣምሮ የያዘ ችሎታ ያለቸውን ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው እንደ ሀገር ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎች የሚፈለገውን ብቃትና ችሎታ ይዘው እንዲወጡ ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
@MoeEthiopia
@MoeEthiopia
606 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:39:31 የተረጋገጠ

ከሁለተኛው  ዙር ፈተና መጠናቀቅ  በኋላ ከሁለት ሳምንት  በኋላ  ህዳር መጨረሻ  ወይም  ታህሳስ  መጀመሪያ  ዉጤት  ለመግለጽ  ዝግጅት  ተጀምሯል ።

ሁለተኛው  ዙር ፈተና የምወስዱት የተማሪዎች ብዛት 1300 ገደማ  ነዉ
እና በሁለተኛው  ዙር በ ኦሮሚያ  ክልል በጸጥታ  ስጋት ያልተፈተኑ ከ 56000 በላይ
@MOEETHIOPIA
@MOEETHIOPIA
669 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 18:37:55
" ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።"

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ወይም 98 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱና በተለያዩ አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ12 ሺህ በላይ ፈተናውን አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ #እንደማይችሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን #በግል መፈተን ይችላሉ ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።
@MoeEthiopia
@MoeEthiopia
629 viewsedited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ