Get Mystery Box with random crypto!

'ማነዉ ...' እስኪ እዉነት የሞባይል ጠጋኝ ሆኖ እነዚህን ነገሮች ያላደረገ እጅ ያዉጣ እኛኮ | 🇲oвιle 🇹єϲниιϲιαиѕ

"ማነዉ ..."

እስኪ እዉነት የሞባይል ጠጋኝ ሆኖ እነዚህን ነገሮች ያላደረገ እጅ ያዉጣ እኛኮ ተንኮላችን ሴይጣንን እራሱ ያስቀናል ወይኔ ግፍችን እስኪ ከግፍችን ትንሽዬዋን ልዘርዝራት ያዉ መቼም በትዝታ ይዢያችሁ እንደምሄድ ተስፋ አደርጋለዉ።

ይሄኔኮ አዳሜ የሰራዉን ግፍ እያሰበ እየሳቀ ፣ እየተፀፀተ ብዙ ብዙ ብቻ እና ወደ ጉዳይህ ግባ አትሉኝም እንዴ

... ቆንጅዬ ሴት መታ ቻርጀር ለመግዛት፤ ባለ 200ብሩን ቻርጀር ለስለስ ባለ ድምፅ 50ብር ነዉ የያዝኩት ስትለህ ፤ ችግር የለዉም ውሰጂዉ አላልኩም ነዉ ምትለኝ

የkeypad ስልክ ቦርዱ ማይሰራ መቶልህ ስክሪኑን አዉጥቼ በማይሰራ ስክሪን አልቀየርኩትም ነዉ የምትለኝ አንተ አሁን እያነበብክ ያለሀዉ ልጅ አዎ አንተ ... ዛሬ እራሱ ያረከዉን የማላቅ እንዳይመስልህ

battery ቀስቅሼ 300ብር አልተቀበልኩም ካልከኝ ገና systeሙ ዉስጥ አልገባህም ነዉ የምልህ ደሞ ይሄንንም ሀፂያት ነዉ የሚልኮ አይጠፋም፤ እንደዛማ ካደረክ አንተ አራዳ ነህ ማንንም አትስማ አራዳ ደሞ ሰዉን የሚጎዳ አይደለም እንደዛ እንዳትረዱብኝ ብዬ ነዉ

አቦ ስንት ስንት አለ እኔ እጄን ባይደክመኝ ሙሉ መፅሀፍ ነበር የምፅፈው ባይሆን ሌሎቹን ገጠመኝ እስኪ በ @yd_mobtech ላይ አካፍሉኝ አሪፉን ደግሞ በቻናሉ ላይ አጋራችኋለዉ።

አቦ ብዙ አወራዉ መሰለኝ ግን ስራችንን ስንሰራ ብዙ መጨናነቅ የለብንም ባይ ነኝ ።በተለይ mobile technician ስትሆን እራስህን ፈታ አድርገህ መስራት ያለብህ ስራ ነዉ። ካልሆነ በአንድ ነገር እራሱ ሙድህ ከተከነፈ ወይ በሆነ ነገር ተናደህ ከነበረ የባሰ ታበላሻለህ እንጂ ምንም አትሰራም ስክሪን connector የሚበጠሰዉ እኮ ... ስለዚህ ጥለ ወተህ ሙድህ ሲመለስ ብትሰራ ይሻልሀል። ቻናላችንም ሁሌ ስለ ሞባይል ብቻ ከሚያወራ ፈታ ይበል በሚለዉ ነዉ። የኔ የ YD አመለካከት ነዉ እና እዉነታዉም ጭምር።

(ግፍ አልሰራዉም የምትል እስኪ)
በተረፈ ግን ቻናሉ ሼር እየተደረገ አይደለም ቅር ያሰኛል በጣም

@mob_techs
@mob_techs