Get Mystery Box with random crypto!

#ስለ_ቄደር_ጥምቀት_እና_ለመጠመቅ_የሚያስፈልጉ_መስፈርቶች #መልስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልጅ | ምን እንጠይቅሎ?

#ስለ_ቄደር_ጥምቀት_እና_ለመጠመቅ_የሚያስፈልጉ_መስፈርቶች

#መልስ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልጅነት ጥምቀትን አንድ ጊዜ ትፈጽማለች፡፡ "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት" ኤፌ. 4:5 ከሌላ ቤተ እምነት የነበሩ ሰዎች ቢመለሱ አስተምራ አሳምና ታጠምቃለች፡፡

ቀድሞ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቆ ኋላ ግን ወደ ሌላ እምነት ቢገባ ተናዞ (ንስሐ ገብቶ) በማየ ጸሎት (መጽሐፈ ቄደር ተደግሞለት) ይረጫል እንጂ ድጋሚ አይጠመቅም፡፡ ቄደር የንስሐ እጽበት ነው ፡፡ ያደፈ ልብስ እንደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢአቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡

በዓረብኛ ቀድር ይባላል፡፡ ትርጉሙም እድፍ ርኩስ ማለት ነው፡፡ መጽሐፉ ወደ ግዕዝ ከተተረጎመ በኋላ ቄድር ተብሏል፡፡

በአሕመድ ግራኝ ወረራ ጊዜ በ16ቱ ዓመታት በተቆጣጠረው ቦታ ሁሉ የሚኖር ትልቅም ይሁን ትንሽ ካልሰለመ ለመኖር አይችልም ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ ብዙ ሕዝብ ሰልሟል፡፡ የሰለመውን ሕዝብ እንደገና ወደ ክርስትና ለመመለስ ገላውዴዎስ መጽሐፈ ቄደርን ከዓረብኛ ወደ ግዕዝ አስተርጉመውታል፡፡ ቄደር የንስሐ ጸሎት ማለት ነው፡፡ አንዳንድ መምህራን ቄደርን ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር ያያይዙታል፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሷል፡፡ ስለዚህም ነው የቄደር ጥምቀትን ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር የሚያያይዙት፡፡

በቤተ ክርስቲያን ስደት ከተጀመረ አንስቶ ስደት ፈርተው ከሃይማኖታቸው የወጡትን ሁሉ ለመመለስ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በመጽሐፉ መጀመርያም "መጽሐፈ ቄደር ሃይማኖቱን ለካደ ወይም ላረከሰ ወንድም ይሁን ሴት የወንድ መነኩሴም ይሁን የሴት መነኩሲት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘጋጁት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዚሁ መጽሐፍ ተጠቅማ የጠፉትን በጎቿን መልሳለች፡፡ በመጽሐፉ የሰፈረው ጸሎት ይደገምና ውሃው በተመለሱት ሰዎች ላይ ይረጫል፡፡ ወይም ይጠመቁታል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በወንድም ተክለማርያም
@Mnenteyiklo @Mnenteyiklo