Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በክርስቶስ ልጆቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን! | ምን እንጠይቅሎ?

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በክርስቶስ ልጆቼ ሰላም ለእናንተ ይሁን!
አንድ አባት ልጆቹን ሲመክር እንዲህ አለ። "ክፉ ሀሳብና ስለ ጊዜያዊ ስኬቶች ወይም ኃላፊነቶች አብዝቶ የሚጨነቅ ሰው በነፍሱ ለስንፍና ይዳረጋል። ለነፍሱ የሚጠቅመውን ለማድረግ ቸልተኛ ይሆናል። እንዲህ ዓይነት ሰው ካያችሁ በነፍሱ የታመመ መሆኑን አውቃችሁ እዘኑለት። ሥርዓተ አምልኮን በመከታተል ጠንካራ የሆኑ አማኞች ላይም ወደ ክርስቶስ ፍቅር ለመድረስ ወሳኝ በሆኑ የሕይወት ልምምዶች ላይ ሰንፈው ልታዩዋቸው ትችላላችሁ። ስንፍና በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተጠላ ነው፤ ኃጢአትም ነው። ከዚያም በላይ "ከዚህ በላይ ከእኔ ምን ይፈለጋል?" የሚል ትዕቢትም ነው::
ለምሳሌ ማታ ወደ መኝታችሁ ስትሄዱ በራችሁን መዝጋትን በቸልተኝነት ልትተውትና ለምን አለዘጋችሁትም? ተብላችሁ ስትጠየቁ ደከመኝ ወይም ረሳሁት ልትሉ አትችሉም። በእውነቱ ሕይወትን አደጋ ላይ ጥሎ ደከመኝ ወይም ረሳሁት ማለት ምን ዓይነት መልስ ነው። ይህን መልስ በሰጡን ሰዎች ላይ ምን ያህል ጊዜ እንደተቆጣን አስቡ። ኃላፊነታቸውን በዘነጉ አገልጋዮቻችን ላይ ወይም የሚጠበቅባቸውን ከማድረግ በጨዋታ ተታለው በረሱ ልጆቻችን ላይ ስንት ጊዜ ተቆጥተን ወይም ቀጥተናቸው ይሆን? የእነርሱን ስንፍና መታገሥ የማንችል ከሆነ እኛስ ለስንፍናችን ከጌታ ዘንድ ርኅራኄን ለምን እንጠብቃለን? እኔኮ ኃጢአት አልሠራሁም ሰነፍሁ እንጂ ብንል ''አንተ ሀኬተኛ ባሪያ ... " ተብሎ ወደ ጨለማ እንዲጣል ከተፈረደበት ባሪያ በምን እንለያለን?
ቸልተኛ፣ ዝንጉና ሰነፍ በሆንን መጠን መከራችን በዚያው ልክ ይሆናል። ጥንቁቅ፣ ትጉህና ለክርስቶስ ፍቅር የምንሳሳ በሆነ መጠን ደግሞ ደስታችንም እንዲሁ ይበዛል። ልጆቼ ከሰነፍ ኃጢአተኛ ይሻላል። ኃጢአተኛ የንስሐ ተስፋ አለው፡፡ ለሰነፍ ተሰፋው ምንድር ነው?"
በክርስቶስ አገልጋያችሁ!
@ktamerat @ktamerat @ktamerat @ktamerat