Get Mystery Box with random crypto!

✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞☞ ☞ እባካችሁ አንብቡና በጣም ለምትወዱት ሰው ሼር አድርጉት (ጾመ ፍልሰታ) | ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)

✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞☞
☞ እባካችሁ አንብቡና በጣም ለምትወዱት ሰው ሼር አድርጉት

(ጾመ ፍልሰታ) የፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር።

የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ነው።

በቤተ ክርስቲያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው።

ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው፤ በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል።
ከ8ወር በኋላ በነሐሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል። በዚህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፤ በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር? አላቸው። ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ "አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነስታ አርጋለች።'' ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን ሰበኗን (መቀነቷን) አሳያቸው። ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታተኑ። በዓመቱም ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቀርብናል? ብለው ከነሐሴ 1 ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በነሐሴ14 ቀንም ጌታችን ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው። ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ16 ተነስታለች። በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህችን ጊዜ ትፆማለች።
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
<< ወለወላዲተ ድንግል >>
<< ወለመስቀሉ ክቡር >>
@Mitinkimem
@Mitinkimem
@Mitinkimem