Get Mystery Box with random crypto!

ዝም ብለህ እደግ! አንዳንዴ ካንተ ጋር የማይሔዱ፣ ከሃሳብህ የማይስማሙ፣ ህልምህ የማያሳምናቸው፣ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ዝም ብለህ እደግ!

አንዳንዴ ካንተ ጋር የማይሔዱ፣ ከሃሳብህ የማይስማሙ፣ ህልምህ የማያሳምናቸው፣ ተስፋህ የማይታያቸውን ሰዎችን መራቅ፣ መነጠል፣ መለየትና እነርሱን መግፋት ላያስፈልግህ ይችላል። እግረመንገድህን ህይወትህን ለመቀየር፣ እራስህን ለማሻሻል፣ ማንነትህን ለማሳየት፣ በልክህ ለመኖር በምታደርገው ጥረት በሁኔታዎች መሃል ዙሪያህን እየቀየርክ፣ ውሎህን እያስተካከልክ፣ አመለካከትህን እያሳደክ ትመጣለህ። ይህም ተግባርህ ምንም ቢያደርጉህ፣ ምንም ቢያደርጉብህ ዝም ብለህ ማደግህ ብቻ እነርሱን ወደኋላ ያስቀራቸዋል፤ ፍጥነትህ ከእነርሱ ይነጥልሃል፤ ውሎህ በብዙ ርቀት እንድትቀድማቸው ያደርግሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዝም ብለህ እደግ፤ ዝም ብለህ ተመደግ፤ ድምፅህን አጥፍተህ እራስህ ላይ ስራ፤ ጠንክረህ መለወጥህን ቀጥል። ሊተውህ ወይም ልትተዋቸው ያልቻልካቸው የቅርብ ሰዎች ቢኖሩና በእርግጥ የሚገቡህ፣ የሚያስቡልህና የሚጠቅሙህ ከሆኑ በኑሮህ መቀየርህ፣ በህይወትህ ከፍ ማለትህ፣ በብዙ ዘርፍ ማደግህ ሊጎረብጣቸውና ግንኙነታችሁን ሊያበላሸው አይችልም። ነገር ግን ዝቅ ስላልክ፣ ደረጃህን ስላሳነስክ፣ ወርደህ አቀርቅረህ ስለሰራህ ከሰው በታች የሚያዩህ፣ እራስህን በመሆንህ፣ ትክክለኛ ማንነትህን በመግለጥህ፣ በምርጫህ በማደግህ አይናቸው የሚቀላ፣ የሚቀኑብህና የሚናደዱብህ ከሆኑ ለእራስህ በመታመን የለውጥ ጉዞህን መቀጠሉ ብቸኛው አማራጭህ ነው።

አዎ! ወዳጅ ቢሔድ ወዳጅ ይተካል፤ በህይወትህ የሚገጥሙህ ሰዎች በሙሉ የእድሜ ልክ አይደሉም። አላማህን ከያዝክ ካንተ ጋር የሚስማሙ፣ የሚጠቅሙህ፣ አንተም ደስ ብሎህ የምትጠቅማቸው ሰዎች ይመጣሉ። በክፉ ቀን ከደረሱልህ፣ ስትወድቅ ካነሱህ፣ ስትፈልጋቸው ከሚደርሱልህ ሰዎች የትኛውም እድገትህ ላይለይህ ይችላል። ከሚያሴሩብህና በጀርባህ ከሚወጉህ ሰዎች ግን እድገትህ በሚገባ ይነጥልሃል፤ እለት እለት መቀየርህ መንገዳችሁን ይለየዋል። አንድ ቀን ትቺት የማትሰማበት፣ ለነቀፋ ጆሮ የማትሰጥበት፣ ለተቃውሞ የማትመለስበት ጊዜ ይመጣል። ያም ሰዓት በእርግጥም በእራስህ የምትተማመንበት፣ በእድገትህ የምትኮራበትና የእራስህን አቅጣጫ የያዝክበት ሰዓት ነው። ዝም ብለህ እደግ፣ ዝም ብለህ ተቀየር፣ ማራገፍ ያለብህን ሸክምም በሂደት እያራገፍክ ተጓዝ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q