Get Mystery Box with random crypto!

አውቀህ ተሰቃይ! ልታድግ የምትችልበት ብቸኛው ጊዜ ምቾት የሌለህ፣ ስቃይህ የበዛ፣ የመረረህና ፈተ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

አውቀህ ተሰቃይ!

ልታድግ የምትችልበት ብቸኛው ጊዜ ምቾት የሌለህ፣ ስቃይህ የበዛ፣ የመረረህና ፈተና ውስጥ በወደክበት ጊዜ ነው። አንድ አስደጋጭ አጋጣሚ ሲፈጠር የሚመጣልህን ሃይልና ጉልበት አስታውስ። በህይወት ፈተናም ይህ ጉልበት በብዙ እጥፍ ውስጥህ ተቀምጧል። እድገትን ከፈለክ ውስጥህ ሊረበሽ ይገባል፤ ለውጥን ከተመኘህ ሁኔታህ መናወጥ አለበት፤ ምቾት ከማጣት፣ ከእራስ ጋር ከመታገል ጋር ፍቅር ሊይዝህ ይገባል። ረጅሙን ጊዜ በመኝታ እያሳለፍክ፣ የበለጠውን ሰዓት በመዝናናትና ዶፓሚንህን ለመመገብ እየተጠቀምከው፣ ብዙ ሰዓት በቀልድና ጫወታ ላይ እያሳለፍክ፣ ምቾት እስኪያሰክርህ እየጠበክ ለውጥን መናፈቅ፤ እድገትን መመኘት ቅዠት ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ምቾትህን አሳልፈህ ስጥ፤ መደላደለህን መሱዓት አድርገው፤ ጥለሀው ውጣ፤ እለት እለት ምቾት የሚነሳህና የሚጎረብጥህ ሁኔታ ውስጥ እራስህን አስገባ፤ ለእራስህ ስትል፣ እድገትህን መርጠህ አውቀህ ተሰቃይ፤ ገብቶህ ዋጋ ክፈል፤ እየመረረህ እራስህን አድን። ማንም ተመችቶት ስኬታማ የሆነ እንዳይመስልህ። የስኬት ጉዞ መራርና ፈታኝ ባይሆን ብዙ ስኬታማ ሰዎችን ታገኝ ነበር። ነገር ግን አይደለም፤ ስኬት ብዙ ሰው የሚጠላውን ምቾት ማጣት፤ ምቾት ማጣትን በእራሱ የመውደድን ሃይል፣ አስደሳቹን ስቃይ የመምረጥን ብርታ ይፈልጋል። ጠቃሚና ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ሳለ አንተ ግን ምቾት ስላልሰጠህና ፋታ ስለነሳህ ብቻ ደጋግመህ እያቆምክ ምቾትህን የምትጠብቅ ከሆነ የጉዞህ ማብቂያ ቅርብ እንደሚሆን አትጠራጠር።

አዎ! አትክልት ለማደግ ውሃና ፀሃይ ይፈልጋል፤ ላንተም እድገት ምቾት ማጣትና ፈተና እንደ ውሃና የፀሃይ ብረሃን እጅግ ወሳኝ ነው። ምቾት በእርግጥም ደስ ይላል፤ እረፍት አለው በዛው ልክ ግን እያሳነሰ፣ እያደከመ፣ ልፍስፍስና በቀላሉ ተሰባሪ እያደረገ ይመጣል። እድገትን ከፈለክ ፈተና፣ ስቃይ፣ መከራ የግድ ነው።  የማትወደውን ስራ መስራትህ ስቃይ ከሆነ የምትወደውን ለመፈለግ እንደ ብርታት ተጠቀመው፤ የማይጠቅምህ ስፍራ መገኘትህ ሰላም ከነሳህ ሌላ ቦታ ለመቀየር ያንን ሁኔታ እንደ ሃይል ተጠቀመው። በአሁን ሰዓት ያለኝ ይበቃኛል፤ ማደግ አልፈልግም፤ የዛሬ ገቢዬ ህይወቴን ለመምራት እጅግ በቂ ነው ብሎ በምቾት የሚናገር ሰው አይኖርም። ምክንያቱም መሬት ላይ ያለው ሁኔታ በእራሱ ይህን ለማለት አይፈቅድምና ነው። በየእለቱ ችግር ወዳንተ እየተጠጋ ነውና ቁጭ ብለህ ከምታየው ተነስተህ ሳይደርስብህ ሔደህ ተጋፈጠው፤ ምቾትህን ለእድገትህ መሱዓት አድርገው።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q