Get Mystery Box with random crypto!

ሚናራ ቲቪ ~ 🅜𝕚𝕟𝕒𝕣𝕒 𝕥𝕧

የቴሌግራም ቻናል አርማ minara_tv — ሚናራ ቲቪ ~ 🅜𝕚𝕟𝕒𝕣𝕒 𝕥𝕧
የቴሌግራም ቻናል አርማ minara_tv — ሚናራ ቲቪ ~ 🅜𝕚𝕟𝕒𝕣𝕒 𝕥𝕧
የሰርጥ አድራሻ: @minara_tv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.95K
የሰርጥ መግለጫ

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»
ለማንኛውም አስተያየትና ጥቆማ ከታቺ ያድርሱን
☞ @minaratv_bot

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-02 13:19:39 አረበኛ ቋንቋ ትምህርት አዲስ ለምትመዘገቡ እና ቁርአን መቅራት ለምትፈልጉ

አረበኛ ትምርቱን መውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች @Efraz_arabicbot የሚለውን በመጫን ተመዝገቡ።

ያለን ቦታ ትንሺ በመሆኑ ቀድመው የሚመጡ ተማሪዎቺን ብቻ የምናስተናግድ ይሆናል!

➢ ለአዲስ ተማሪዎቺ ከጥር 24 እስከ 30 ፈጥናችሁ በመመዝገብ መማር ትችላላችሁ !


በተጨማሪም ቁርአን መቅራት የምትፈልጉም መመዝገብ ትችላላችሁ ።

ይህን መልካም እድል ለወዳጂዎ ሼር በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ ጀዛከሏህ ኸይር ፡፡

ለመመዝገብ ከታች ያለውን ቦት ይጠቀሙ



@Efraz_arabicbot
@Efraz_arabicbot



ለበለጠ መረጃ የማስታወቂያ ቻናላቺንን ላይ ይቀላለቀሉ

https://t.me/arabic_schoolonly
245 views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 08:19:06 አይ ጉድ አሉ እማማ !

አንድ አፋር ለሥራ አዲስ አበባ መጥቶ
የሆነ ክርስቲያን የሥራ ባልደረባው ቤት
ለዚያራ ሄዶ ግድግዳ ላይ የሆነ ፎቶ
ተሰቅሎ አይቶ, መቸም የዚህ የጥቁር
ጓደኛው እናትም ዘመድም አልመስልህ
ቢለው

አፋሩ ፦ ያ የማን ፎቶ ነው
ጓደኛው ፦ የማርያም
አፋሩ ፦ ዘመዳችሁ ናት
ደገኛው ፦ ኧረ አይደለም የእግዚአብሔር
እናት ናት
አፋሩ ፦ አሁን በሕይወት አለች?
ጓደኛው ፦ አይ የለችም ሞታለች
አፋሩ ፦ ማን ገደላት
ጓደኛው ፦ እግዚአብሔር
አፋሩ ፦ እኮ ልጇ! ገደላት ?
ጓደኛው ፦ አፈር ብላ

ሰዎየው ግን ገረመኝ ወጋቸው ቀላል ክክክ !

https://t.me/FKR_ESKE_JENET
320 views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 22:42:13 ጥሩ_ ትዳር _ትፈልጋለህ??!

ከፈለክ ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ ይዘንላቸው) ልጃቸው ሲያገባ የለገሱት ምክር እኔም አንተንም ስለሚመለክት ጆሮህን አውሰኝ! !

☞ ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ
ለመያዝ ሞክር፦

“①- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት

②- ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል

③- ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

④- ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ

⑤- ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

⑥- ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

⑦- ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ ሰው ሁንላት።

⑧- ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

⑨- ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል በዚህን
ወቅት አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ጾም) ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። በዚህን ጊዜ እዘንላት ትእዛዝ አታብዛባት።

⑩- ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት እዘንላት በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት ምርጥ የሂዎት አጋርህ ትሆናለች።

https://t.me/FKR_ESKE_JENET
671 views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 22:52:22
ጣውላነት ይቅርብን

ጣውላ ከሰሰ አሉ
አንድ ቀን ለሚስማር
"ሰንጥቆኛል" ብሎ
ምንም ሳልናገር

ሚስማርም መለሰ
አንገቱን በመስበር
"መዶሻውን ብታይ
ከላይ ሲወረወር
አይደለም ልትከሰኝ
ባዘንክልኝ ነበር"

እኛንም አንዳንዴ
ሰዎችን ከምንወቅስ
ቀድመን ብንረዳ
ለምን እንደ ምንወቅስ


https://t.me/FKR_ESKE_JENET
548 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 23:43:49 ልባዊ ምክር ለሴቶች

በዚህ ሰአት ወንዶች የፉክክር ሜዳቸው ያደርጉሻል። ከልብ የሚወድሽ ሰው ሂወቱ ነሽ። ሊያጣሽ አይፈልግም !!! ብዙ ነገር ይሆንልሻል ! ባንቺ የሚመፎካከሩ ሰወች ግን ጨዋታው ካበቃ በኋላ ጥለውሽ ዞር ይላሉ ሰለዚህ ኡክታየ ለሂወትሽ የሚበጅሽን ስላንች ብዙ የሚሆንልሽን ሰው ዋጋ ክፈይለት ያኔ ሂወትሽ ያማረ ይሆናል።

ቆም ብለሽ የሚጠቅምሽን ለይ ኡክቲየ!

https://t.me/FKR_ESKE_JENET
958 views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 09:46:36 ሚናራ ቲቢ በቲክቶክ መጣ



http://tiktok.com/@minara_tv


1.1K views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 09:27:23 https://vm.tiktok.com/ZMYdXHrU3/
980 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 20:33:28 ፍቅር የካፊሮቺ አለም ብቻ አይደለም

ፍቅር በኢስላም ውስጥ እንዴት እንደሚኖር ና ላሳይህ ተከተለኝ

ሮማንቲክ ፍቅር በነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ህይወት ውስጥ ተመልከት !



"ከምፅዋት ሁሉ በላጩ ባል ከሚስቱ አፍ ላይ የሚያስቀምጣት ጉርሻ ነች" በሚለው ነብያዊ ሀዲስ መደመም አቁመን በፊልም ላይ አንድ ተዋናይ ሚስቱን ሲያጎርሳት ስንመለከት መደመማችን ያሳዝናል።


<<በፍቅረኛሞች>> መሃል አበባ መለዋወጥ የምዕራባዊያን ባህል ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች "አበባ በስጦታ መልክ የቀረበለት ሰው የሚያውድ መዓዛና ለመያዝ ቀላል በመሆኑ ሳይመልስ በክብር ይቀበለው" የሚለውን ነብያዊ ትውፊት ዘንግተዋል::


ነብዩ ሙሐመድ ሰለለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓኢሻ ጋር በነበሩበት ወቅት ውሃ ለመጠጣት ሲፈልጉ እርሷ በጠጣችበት ኩባያ ነበር የሚጠጡት። በኩባያው መጠጣት ብቻ ሳይሆን ዓኢሻ የጠጣችበትን ቦታ አነጣጥረው በመመልከት በጠጣችበት የኩባያው ጫፍ ለይተው ይጠጡ ነበር። ( ስለ ጉንፋን የሚያስብ የዋህ አይጠፋም እኮ - ባክህ ፍቅር ከጉንፋን በላይ ነው )


ነብዩ ሙሐመድ ሰለለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሞቱት በሙዕሚኖች እናት በሆኑት ዓኢሻ ክፍል ውስጥ ነበር። ግንባራቸውን ለፈጣሪያቸው ደፍተው መሞት የሚችሉበት ሁኔታ ቢኖርም የርሳቸው ምርጫ የነበረው የመጨረሻ ህልፈታቸው በዓኢሻ እቅፍ ውስጥ ሆነው እንዲቋጭ ነበር። ምኞታቸው ሰመረ። በዓኢሻ እቅፍ ውስጥ እስትንፋሳቸው ተቋረጠ።

ምዕራብዋያን ለሚስቱን ወንበር ሲየዘጋጂላትና የመኪና በር ሲከፍትላት አይተህ ይሆናል አትገረም ነብያችን ደግሞ ጉልበታቸውን አንበርክከው ሚስታቸውን ፈረስ ላይ ያወጡ ነበር ፡፡
ሰለ ማን መሰለህ የማወራው የሰው ልጆቺ ምርጥ ነብዩ ﷺ ነውኮ የሰው ልጆቺ ምርጥ የሆኑት ነብያችን ጉልበት አስረግጠው ነው ፈረስ የሚያስጋልቡት ፡፡

ለዛም ነው ፍቅር ከኢስላም ተማሩ የምንለው ፡፡ የኩፋር ፍቅር አስከ መቃብር ነው ፡፡ የኛስ ወዳጄ ...ፍቅራቺን እስከ ጀነት ነው ፡፡ አየኸ ልዩነታቺን ሰማይና ምድር አይገልጸውም ፡፡

<<ፍቅር እስከ ጀነት>> ይሉሀል ይህ ነው።

ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: -
" ከባለቤትህ አፍ ውስጥ ያኖርካት ጉርሻ ሳትቀር ምንዳ ያላት ቢሆን እንጂ ፈፅሞ ልግስናን አለገስክም"
በደመቀ ቀይ ቀለም ተነክሮ በማህበራዊ ድረ ገፆች ከሚለቀቀው የልብ ቅርፅ ምስል በላይ የፍቅርን ምልክት ከላይ በተወሳው ነብያዊ ህይወት ማየት ትችላለህ። እንግዲህ ይህ ነው እውነተኛው ሮማንቲክ የፍቅር ዓለም።

እኛ ሙስሊሞች ሞዴላችን ምእራባዉያን ሳይሆኑ 1400 አመት በፊት ለኛ ስልጣኔ ትተዉልን የሄዱትን ነብዩ ﷺ ነዉ፡፡

➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
ሼር በማድረግ አዳርሱ ባረከሏህ ፊኩም!
ፍቅር እስከ ጀነትን ይቀላቀሉ
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
https://t.me/FKR_ESKE_JENET
853 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 14:16:42ዝምታ

ዝምታም ድምፅ አለው
ሰምቶ ላዳመጠው
አርቆ ላጤነው
የብልህ ዝምታ
ትርጉሙ ሲፈታ
በሚገባው ቦታ
ፋይዳው ሲያመዝን
ዝምታ ማውራትን
ሳይደረድር ቃላት
ሀሳቡን ሲረዱት
ዝምምምምምም… ያለም አንደበት
ከልብ ብትሰሙት
ቁምነገር አለበት

══ •⊰✿ ✿⊱• ═

https://t.me/FKR_ESKE_JENET
1.1K views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 19:26:06 ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው

አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያችን - ﷺ - የቲም ነበሩ። እናታቸውን በ6አመታቸው አጥተዋል ፤ ርቧቸው ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረዋል ፤ ሌላም ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። ታዲያ አሏህ ጠልቷቸው ነው ብለህ ታስባለህን? በጭራሽ.
°
እንደውም በተቃራኒው እንደሚወድህ አመላካች ነው። ነብያችን - ﷺ - ይህን ስላሉ ፦ [ አሏህ ህዝቦችን ከወደደ ይፈትናቸዋል። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 23623). በሌላም ሐዲስ ላይ [ ከሰዎች ሁሉ በላእ የሚበረታባቸው ነብያቶች ናቸው ከዛም ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው። ] (ሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 144).
°
አማኝ በሆነ ሰው ላይ ፈተና መብዛቱ አሏህ ለሱ መልካምን ነገር እንዳሰበለትም አመላካች ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ አንድን ሙስሊም ከድካምም ይሁን ከበሽታ ከጭንቅም ይሁን ከሓዘን ከችግርም ይሁን ከጭንቀት ሙሲባ አይደርስበትም ከምትወጋው የሆነች እሾህም ብትሆን አሏህ በሷ አማካኝነት ከወንጀሉ ቢያፀዳው እንጂ። ] (ሶሒሁል ቡኻሪ ፥ 5641). አሏህ ፈተናን ታግሰው እሱ ከሚወዳቸው ባሪያዎቹ ያድርገን።

https://t.me/AbdulKereem_AlHanani
6.9K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ