Get Mystery Box with random crypto!

#አምላከ_ተክለሃይማኖት_ማረን አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2× አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2× ስለ | መርጌታ ሚካኤል የበሀል ህክምና

#አምላከ_ተክለሃይማኖት_ማረን

አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን

#አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት

#አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት


#አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት


#አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት

#ዲያቆን_ዘማሪ_ኤፍሬም_ፀጋዬ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur