Get Mystery Box with random crypto!

#ድል_አለ_በስምህ በስልክ የተቀዳ ድል አለ በስምህ ድል አለ በቃልህ /2/ ተራራው ይናዳል | መርጌታ ሚካኤል የበሀል ህክምና

#ድል_አለ_በስምህ
በስልክ የተቀዳ

ድል አለ በስምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔዓለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውሀ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው
#አዝ
በእልልታ ቢፈርስ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
#አዝ
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውሀ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ስለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
#አዝ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur