Get Mystery Box with random crypto!

Mehreteab Assefa

የቴሌግራም ቻናል አርማ mihretab_asefa — Mehreteab Assefa M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mihretab_asefa — Mehreteab Assefa
የሰርጥ አድራሻ: @mihretab_asefa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.83K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-09 22:47:01
ደብረ ብርሃን የተዋህዶውን አርበኛ ብጹዕ አቡነ ኤፍሬምን እንዲህ ሸኝታለች።
በእውነት በረከታቸው ይደርብን።

ቅዳሜ ደግሞ ቅዱስ ፓትርያርካችንን በመስቀል አደባባይ ተገኝተን በመሸኘት በረከት እንድንቀበል እግዚአብሔር ይርዳን።
2.9K viewsedited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 14:38:49
የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሽኝት መርኃ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ፡፡

የቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የጸሎትና ሽኝት መርኃ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናወነ።

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከተለያዩ ገዳማትነ እና አድባራት የመጡ ካህናትና ምዕመናን መገኘታቸውን የቤተክርስቲያኒቷ የመገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ዘገባ ያመለክታል።

የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በገዳሙ ካህናትና ዲያቆናት መከናወኑ ተገልጿል።

የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር ነገ በደብረ ብርሃን ከተማ በደብረ ብረሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈጸም ይኾናል።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ የካቲት 27/2014 ዓ.ም በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው የሚታወስ ነው።
ቅድስት በረከታቸው በሁላችንም ላይ ትደር
2.7K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 21:27:48 የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለተሚማ አረጋግጠዋል።

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

“ቃለ እግዚአብሔርን እየተናገርኹ ብሞት ደስታዬ ነው፤” የሚሉት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ በዕርግና ዕድሜአቸው እንኳ፣ በየወረዳው እየተንቀሳቀሱ ለስብከተ ወንጌል ባሳዩት ትጋት ይታወቃሉ፡፡

በተለይም፣ ባለፉት ዓመታት ቁልፍ የዕቅበተ እምነት ትኩረት በኾነው በፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተጋድሎ ረገድ፣ የኑፋቄው ወኪል ሰባክያንና ዘማርያን ነን ባዮች ሀገረ ስብከቱን እንዳይዳፈሩ፣ በሰጡት ጥብቅ አባታዊ አመራርና ባደረጉት የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ይታወሳሉ፡፡

በራስ አገዝ ልማትም በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ታሪካዊውን የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዐደባባይ ይዞታ በማስከበር፣ እንደ ጻድቃኔ ማርያም እና ሸንኮራ ዮሐንስ ያሉ ታላላቅ አድባራትን በማስተባበር ያሠሩትና የከተማው መገለጫ ለመኾን የበቃው ዘመናዊ ኹለ ገብ ሕንፃ በአብነት ይጠቀስላቸዋል፡፡

ከኹሉም በላይ ደግሞ፣ በጸሎታቸውና በአባትነታቸው፣ በተመደቡባቸው አህጉረ ስብከት አገልጋዮችና ምእመናን የተወደዱ አንጋፋ አባት ነበሩ – አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፡፡
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
2.6K viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 21:05:51
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አረጋዊው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ብፁዕነታቸው በአዲስ አበባ ገሱንድ የሕክምና ማዕከል የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው የቆዬ ቢሆንም በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ቅድስት በረከታቸው በሁላችንም ላይ ትደር።
2.8K viewsedited  18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 11:52:54 ሀ/ በጋይንት አውራጃ በታች ጋይንት ወረዳ በምትገኘው በታላቋ ደብር ቤተ ልሔም ከአንድ በጎ አድራጊ ርዳታ በመጠየቅ በናፍጣ የሚሠራ አንድ የሞተር ወፍጮ አቋቁመው ለካህናቱና ድጓ ለሚያደርሱ ተማሪዎች ደመወዛቸውን እንዲችሉ ጥረዋል፡፡
ለ/ በደብረ ታቦር አውራጃ በእስቴ ወረዳ ሊጋባ ቅዱስ ሚካኤል በተባለው ቤተ ክርስቲያን አካባቢ አንድ የሞተር ወፍጮ በጎ አድራጊዎችን በመጠየቅ እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ አገልጋይ ካህናትም የወር ደመወዝተኛ እንዲኾኑ አድርገዋል፡፡
ሐ/ ጥንታውያን መጻሕፍት ለትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ ባደረጉት ጥረት፡- ጠቢበ ጠቢባን፣ ሙሉ ሲኖዶስ፣ የቅዳሴ አንድምታ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰናቸውን ውሳኔዎች በሙሉ በብራና እንዲጻፉ አድርገዋል፡፡ በጭልጋ፣ በሊቦ፣ በደብረ ታቦር፣ በጋይንት አውራጃዎችና በእስቴ ወረዳ የችግኝ ጣቢያዎች አቋቁመው በየዓመቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ችግኞች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሰበካና ለሕዝባውያን ድርጅቶች እንዲከፋፈሉ በማድረጋቸው የተራቆቱ መሬቶች በዛፎች እንዲዋቡ ጥረዋል፡፡
መ/ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በማስፈቀድ በማኅደረ ማርያም የሐዲሳት፣ የድጓና የቅዳሴ ት/ቤት አሠርተው ለመምህራኑ ከ50 እስከ 200 ብር ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣ ለደቀ መዛሙርቱ ድጎማ እንዲሰጣቸው አድርገዋል፡፡
ሠ/ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ቂርቆስ ገዳም በብር 8ሺሕ835 እንዲታደስ አድርገዋል፡፡ በጣና ለሬማ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ብር 4ሺሕ ረድተዋል፡፡ የደረሞ ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን ብር 21ሺሕ 114 በማውጣት አሳድሰዋል፡፡ እንዲሁም ጥንታዊውን የግርቢ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብር 8ሺሕ860 ብር እንዲታደስ አድርገዋል፡፡ በአዘዞ በሰሚ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ካህናቱ ማሠልጠኛ የሚወስደው መንገድ በምግብ ለሥራ መርሐ ግብር እንዲሠራ አድርገዋል፡፡
በጎንደር መንበረ መንግሥት ጥበበ እድና የአዳሪ ቤቱ ዙሪያ ርዳታ በመጠየቅ ከ9ሺሕ በላይ በማወጣት እንዲሠራ አድርገዋል፡፡ በጎንደር ጉባኤ ቤትና የዶክተር አየለ ዓለሙ የመቃብር ቤት የአራቱ ጉባኤያት ሥዕል እንዲሠራበት አድርገዋል፡፡ በሊቦ አውራጃ በቆላ እብናት ለአምራቾች የኅብረት ሥራ ማኅበር ብር 15 ሺሕ ረድተዋል፡፡ በጎንደር ከተማ በአዘዞ አባ ሳሙኤል በመጠለያ ለሚረዱ ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ጋራ በመተባበር የኤልክትሪክ ምጣድ ርዳታ አድርገዋል፡፡ በዳባት ወረዳ የሚገኘውን የደፍቂ ቅዱስ ሚካኤልን በብር 5ሺሕ፣ ቆማ ፋሲለደስን በብር 5ሺሕ አሳድሰዋል፡፡ ለአምስትያ ገዳም ብር 4ሺሕ፣ ለጣርክ ማርያም ብር 7ሺሕ ረድተዋል፡፡
ዐደባባይ ኢየሱስም በብር 40ሺሕ እንዲታደስ አድርገዋል፤ የድምፅ ማጉያም አስገብተውለታል፡፡ በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ለቸንከር ተክለ ሃይማኖት ርዳታ በመጠየቅ ብር 764ሺሕ አበርክተዋል፡፡ በዚያው በጎንደር ዙሪያ ከማክሰኝት እስከ አርባያ ለመንገድ ሥራ ብር 30ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ አድርገዋል፡፡ ከእብናት እስከ ጎሐላ ለመንገድ ሥራ የብር 6ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ አድርገዋል፡፡
በስሜን አውራጃ ለሚገኙ ጥንታውያን ገዳማት፤ ለቤተ ሚናስ ዋልድባ ከብር 10ሺሕ በላይ፤ ለጣዕመ ክርስቶስ ብር 10ሺሕ፣ ለሰቋር ዋልድባ ብር 4ሺሕ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ(የዓይነት) ርዳታ አድርገዋል፡፡
በጎርጎራ ገዳም በደሴተ ጣና ለሚገኙ ገዳማት፤ ለማን እንዳባ ገዳም ብር 1ሺሕ880፤ ለብርጊዳ ማርያም ገዳም ብር 1ሺሕ ለበሬ መግዣ እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡
ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ርዳታ ሰጪ ድርጀቶች በመጠየቅ አቅም በፈቀደ መጠን በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት የቆዳ፣ የሽመና፣ የሹራብ ሥራ፣ የልብስ ስፌት፣ የወፍጮ ቤትና የዳቦ ቤት እንዲቋቋምና አገልግሎት እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም ለስብከተ ወንጌል፣ ለሰንበት ት/ቤትና ለሕዝብም መሰብሰቢያ የሚያገለግሉ አዳራሾች በየአብያተ ክርስቲያናቱ አካባቢ አሠርተዋል፡፡ ሕዝቡ ንጹሕ ውኃ ማግኘት እንዲችል የውኃ ጉድጓድ በማስቆፈር ለዚሁ የሚያገለግል ሞተርና ቧምቧ እንዲያገኙ የበኩላቸውን ጥረዋል፡፡
ለሀገረ ስብከቱ ያስገኟቸው ሽልማቶች፤
የሰበካ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ደንብ በትክክል እንዲፈጸም በማድረጋቸውና ሰበካ ጉባኤን በሚገባ በማደራጀታቸው፣በየዓመቱ በሚደረገው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ የሥራ ግምገማ በተደረሰበት ውጤት የጎንደር ሀገረ ስብከት ቅድሚያ ቦታ እንዲይዝ አድርገዋል፡፡
በዚህም መሠረት፡- ከ16ቱ አህጉረ ስብከት፣ ከ1975 እስከ 1977 ዓ.ም. በተከታታይ እንዲሁም በ1979 ዓ.ም. አንደኛ፤ በ1978 ዓ.ም. ኹለተኛ በመኾን በውጤታማነት እንዲሸለም አድርገዋል፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ከዚህ በላይ ጠቅለል ባለ መልክ በተዘረዘረው ዓይነት ተልእኳቸውን በትክክል የተወጡ አባት ከመኾናቸውም በላይ በ1979 ዓ.ም. በተደረገው የብሔራዊ ሸንጎ አባላት ምርጫ በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ምርጫ ጣቢያ ደንቢያ ከመረጠው 26ሺሕ127 ሕዝብ መካከል 17ሺሕ249 ድምፅ በማግኘት ተመርጠው ሕዝብን አገልግለዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ የበላዮቻቸውን መካሪ፣ የበታቾቻቸውን አክባሪ፣ በሥራ ታታሪ፣ መንፈሳዊ አባትነታቸውና ትሑት ሰብእናቸው አርኣያነት ያለው ቁጥብ አባት ናቸው፡፡
2.9K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ