Get Mystery Box with random crypto!

Mehreteab Assefa

የቴሌግራም ቻናል አርማ mihretab_asefa — Mehreteab Assefa M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mihretab_asefa — Mehreteab Assefa
የሰርጥ አድራሻ: @mihretab_asefa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.83K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-04 21:20:27
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቄለም ወለጋ ሀዋገላን ወረዳ ለምለም ቀበሌ በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተሰምቷል

በቄለም ወለጋ ዞን ሀዋ ገለን ወረዳ ፤ ለምለም ቀበሌ ዉስጥ መንደር 20 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በዛሬዉ እለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንጹሀን ዜጎች ህይወት እንዳለፈ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዛሬው እለት በጥቃቱ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መገደላቸዉንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። የነበረዉ የሽብር ቡድኑ ሀይል ብዛት የነበረዉ በመሆኑ በአካባቢዉ የሚገኙ የሚሊሻ የጸጥታ ሀይሎች ተጨማሪ ሀይል እስኪመጣ ወደ አካባቢዉ መግባት እንዳልቻሉም ነዋሪዎቹ አንስተዋል።

ነዋሪዎች እንደተናገሩት በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ በዉል ባይታወቅም ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆነ ንጹሀን ተገድለዋል ብለዋል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቁሙት በአከባቢው በነበረው ጥቃት ከ200 በላይ የሚገመቱ ንፁሀን ሰዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል።

በጣም ያማል! ነፍስ ይማር!
808 viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:48:50 የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል!!
======================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት
600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት
700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት
800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት
900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት
1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት
2000. ፳፻ እስራ ምዕት
3000. ፴፻ ሠላሳ ምዕት
4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት
5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት
6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት
7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት
8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት
9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት
10,000. ፻፻ እልፍ
20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ
30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ
40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ
50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ
60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ
70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ
80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ
90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ
100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ
200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ
300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ
400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ
500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ
600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ
700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ
800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ
900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ
1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት
10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት
100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት
1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት
999 viewsedited  14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 19:56:04 የፀሐይ አክሊል በመላ ኢትዮጵያ በመታየቱ ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ይህ ድንቅ ክስተት ዛሬ በሰአሊተ ምሕረት ግቢ ኾኜ ሳለሁ በተመለከትኩ ጊዜ በእጅጉ ደስ ብሎኝ ፎቶ አንሥቼ ከለቀኩ በኋላ ብዙዎች ክስተቱን አስመልክቼ እንድጽፍ ስለጠየቁኝ ጊዜዬን በማጣበብም ቢኾን የተወሰነ ጽፌያለሁ።

እንደ እውነቱ ይህ አስደሳች ቅርጽ በሳይንስ፣ በባሕል፣ በሃማኖት በስፋት ይተነተናል፡፡ በዚህ አክሊል መታየት ዙሪያ የተለያየ እይታ እንደየባሕሉ እንደየሃይማኖቱ እንደየምልከታው ይነገራል፡፡ ሁሉንም በዚህ ላይ ለመተንተን ጊዜ ስለሌለ የተወሰነውን በዐጭሩ ስናይ በሳይንስ ይህ ክስተት አክሊለ ፀሐይ ወይም የ22 ዲግሪ አክሊል በመባል ይታወቃል፡፡

የሚከሰተውም ስድስት ማእዘን የሆኑ በከባቢ አየር ላይ ተንሳፈው የሚገኙ በሚሊየን የሚቆጠሩ የበረዶ ክሪስታሎች ላይ የፀሐይ ብርሃን ሲያልፍ ቀስተ ደመና መስሎ የሚታይ በአማካይ 22 ዲግሪ ራዲየስ ላይ ሠርቶ የሚታይ ቀለበት ነው፡፡

ክብ አክሊል የሚፈጠረው ከእኛ በላይ20 ሺ ጫማ (6 km) በሚርቀው ስስ ሽፋን ባለው ሲሩስ በተባለው ደመና ነው ይላል የዘመናችን ሳይንስ፡፡ ይኸውም በብርሃን መጉበጥና መከፈል ወይም ከበረዶው ክሪስታል ብርቅርቅታ የተነሣ ነው፡፡ እያንዳንዱ የሚታየው እንደየቆመበት ቦታ ሲወሰን ቢሆንም ትኩር ብሎ መመልከት በአልትራ ባዮሌት ጨረር ምክንያት ዐይንን ሊጎዳ ይችላል ይላል ሳይንስ፡፡

የጥንት የሥነ አየር ተመራማሪዎች በጨረቃ ዙሪያ የሚፈጠር አክሊል ካለ ከፍተኛ ዝናብ ይዘንባል ይላሉ፡፡ ምክንያቱም የሲሩስ ደመና ከወጀብ በፊት የሚመጣ ስለኾነ የሚል ምልከታ ነበራቸው፡፡

ወደ ሃይማኖት ሊቃውንት ምልከታ ስንሄድ ደግሞ "ቀስተ ደመናዊ የፀሐይ ቀለበት" ይሉታል፡፡ እነዚህ ጥቃቅን የበረዶ ክሪስታል መስታወት መሰል ቅንጣቶች “በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ” በመባል በራእ 4፡6 ላይ የተጠቀሰውት ነው ይላሉ፡፡ ስሙንም "ባሕረ ማሕው" በማለት ይጠቅሱታል፡፡

አንዳንድ የሃይማኖት መምህራን ደግሞ “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል” (ሉቃ 21፡25) የሚለውን በመያዝ ምልክት በፀሐይ፣ በጨረቃ፣ በከዋክብት መታየታቸው የክፉ ቀን መቃረብ መልእክት ከእግዚአብሔር ሲገለጽ ነው ይላሉ፡፡ ቢሆንም ግን የክፉ ቀን መምጫ መቃረብ የተጠቀሰው አብዛኛውን ከመጨለም ጋር ተያይዞ ያለው ነው እንጂ የፀሐይ አክሊል አይደለም ይላሉ አንዳንድ ምሁራን፡፡ በዚህ ዙሪያ ማዛሮት መጽሐፌን አንብቡ፡፡

እኩሌቶቹ ደግሞ “ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ” (ራእ 10፡1) የሚለውን በመያዝ የመገለጥ ትርጕምን ይሰጡታል፡፡

አንዳንዶች ደግሞ በሕልምም በውንም የምናየው የአክሊሉን ቀለም የሚከበንን መንፈሳዊ ኀይልን ጠቋሚ የሚያደርጉ አሉ፡፡ ይኸውም በጣም ሰፊ ሲሆን በዐጭሩ ለመግለጽ ብሩህ አክሊል በፀሐይ ዙሪያ ከኾነ ንጽሕናንና ከአምላክ ጋር መገናኘትን ይገልጻል ይላሉ፡፡ ሰማያዊ አክሊል ፍቅርን መጠበቅን ወካይ ሲሆን በመላእክት መከበብን ያሳያል ይላሉ፡፡ ቀይ አክሊልን ከቁጣ ጋር፤ ጨለማዊ አክሊልን ከባዶነት ከመንፈሳዊነት መራቆት ጋር ጋር የሚያይዙ አሉ፡፡

በዚህ ዙሪያ ከግሪክ እነ አሪስቶትል (Meteorology III.2, 372a14) በሚል ሥራው።
ከሮማ ፈላስፎች በ2ኛው ክፍለ ዘመን አፑሊዩስ Apologia XV ሥራው።
ሉይስ ሴኔካ Naturales Quaestiones. መጽሐፉ፤ ጸሐፊው ካህኑ ፑሊቸር በ12ኛው ክፍለ ዘመን ላይ Historia Hierosolymitana (1127) መጽሐፉ።
የዮርኩ ኮማንደር ኤድዋርድ ከጦርነት ታሪክና ድል ጋር አያይዞ።
በሮም በ1629 ድጋሚ በ1630 ላይ በታየው የፀሐይ አክሊል ዙሪያ ክሪቶፍ ሼነር Parhelia በሚል መጽሐፉ ብዙ አስገራሚ ነገራትን ጽፈዋል፡፡
በ1661 ላይ ጆርጅ ፌላው “7 ክፍል ያለው የፀሐይ ተአምር” በሚለው በበራሪ ጽሑፉ ላይ ዘርዝሮ የጊዜውን የፀሐይ አክሊል ክስተት ሲጽፍ በቀጣዩ ዓመት ላይ ዮሀኔስ ሄቬሉስ Mercurius in Sole visus Gedani በሚል መጽሐፉ ላይ አስፍሮታል፡፡
በ1790 በተከሰተው በሴንት ፕተርስበርግ ሩሲያ በተከሰተው ጆሀን ቶቢያስ ጽፏል፡፡
በ1843 በኒው ፋውንድ ላንድ በተከሰተው፤ በ1876-77 በነበረው ጦርነት ጊዜ በተከሰተው የፀሐይ አክሊል፤
በ2020 ፌቡሯሪ 14 በኢነር ሞንጎሊያ ቻይና በተከሰተው ብዙ ተጽፈዋል፡፡

ሁሉንም ለመጻፍ ጊዜ ስለሌለ ነባር የአሜሪካ ሕዝቦችና ሕንዳውያን የሚሉትን ብቻ ላስቀምጥ፡፡ እነዚህ ጥንታውያን ሕዝቦች ይህንን “የለውጥ ምልክት” “ጥምዝ ቀስተ ደመና” ይሉታል፡፡ ይህንን አክሊል ቅርጽ አስመልክቶ የጥንት አሜሪካና ሕንዳውያን ትንቢት ነበራቸው ይህም "Ancient American Indian Prophecy" በመባል ሲታወቅ ታላቅ ለውጥ በምድር ላይ ለመምጣቱ ምልክት ይላሉ፤ በጥቂቱ ስናየው “ኹሉም ነገዶች፣ ሕዝቦች ያላቸውን ልዪነት በመተው ምድርንና ነዋሪዎቿን ለመፈወስ በሕብረት ለአንድነት የሚቆሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ሰላምን ለማምጣት እንደ ክብ ቀስተ ደመና በምድር ሁሉ ይመላለሳሉ፡፡ ሁሉም እኩል የሚሆኑበት፣ ሕፃናት የሚጠበቁበት፣ አረጋውያን የሚከበሩበት፣ ጦርነት በሽታ የሚያበቃትን የምድር መፈወሻ ጊዜ የጥበብ ጊዜ መቃረብን ያመለክታል፡፡” ይላሉ፡፡ በቡዲዝም እይታ አክሊል የመልካም ዕድል ምልክት ይሉታል፡፡

በመሆኑም ክቡራን ተመልካቾቻችን ይህን ያህል በዐጭሩ ከሳይንሱም፣ ከባህልም ይህን ያህል ካሰፈርኩ በዝርዝር ስለ ሥነ ፈለክ ለማወቅ አንድሮሜዳና ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ፡፡

በሙሉ የጸደይ ጨረቃ በ8ኛ ወር ሚያዝያ በ8ኛው ቀን 8 ሰዓት ስለ ሰማይ ምስጢር የሚተነትነው ማዛሮት መጽሐፌን ለመመረቅ በዕለቱ ተገኝተው ብዙ ያልተሰሙ ምስጢራትን ይስሙ።
5.7K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 19:56:01
3.6K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 12:14:07
"ዛሬ ክርስቶስ ሞተ ብለን ለቅሶ ልንደርስ አልመጣንም
ክርስቶስ የሞተበትን /የሞተለትን ምክንያት ለምን እንደሳትነው ልንወያይ/ ልንመካከር
ነው"
"ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ ዓመት እስከ ዓመት ስቅለት ነው"
"ክርስቶስ የሞተለት ሰው አሁን በኢትዮጵያ በየቀኑ እየተገደለ ነው። አሁንም ክርስቶስ
እየተሰቀለ ነው ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ ዓመት እሰከዓመት ስቅለት ነው።"
#ብፁዕ_አቡነ_ኤርምያስ
3.3K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 21:41:19
የብርሃን ማዕበል በጅጅጋ
3.7K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 21:20:35 አትስጉን፣አትፍሩን፣እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጥልን በክርስቶስ መስቀል ገለን፣ሰላምን ለዓለም የምናውጅ እንጂ የሰላም ሥጋት አይደለንም።በነገው የቅዱስ አባታችን የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ በመስቀል አደባባይ የምንገኝበት ምክንያት ፣ 1ኛ የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሳቢ፣ የመንጋውና የቅድስት ቤተክርስቲያናችን መሪ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሆኑት ታላቁ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሥጋ ስለተለዩን ሀዘናችንን ለመግለጽ ነው። 2ኛ ቅዱስ አባታችን ታላቅ የበረከት አባት ስለሆኑ የቅዱስነታቸውን በረከት ለመቀበል ነው።ምክንያቱም እግዚአብሔር የቅዱሳኑን አጽም ስለሚጠብቅ፣በኤልሳዕ አጽም ሙት ያነሳና ተአምር ያሳየ እግዚአብሔር፣ ዛሬም በቅዱስ አባታችን አጽም ፣ለህዝባችንና ለሀገራችን ተአምር ይሰራል፣የኢትዮጵያንም ትንሳኤ ያረጋግጥልናል ብለን ስለ ምናምን ነው።የድንግል ልጅ ምን ይሳነውና?????????? 3ኛ ኦርቶዶክሳውያን ምን ያህል ክብረ ክህነትንና አባትን አክባሪ መሆናችንን ለዓለም ለማሳየት ነው።ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ እንዲል ቅዱስ ወንጌላችን። ስለዚህ ይህንንና ይህንን በመሳሰለው የተቀደሰ ዓላማ ነገ መጋቢት 3/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ተገኝተን ቅዱስ አባታችንን ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ እንሸኛለን። ይኸው ነው እንግዲህ ዓላማችን።እረኛው ሲለያቸው በጎች ይጮሀሉ። በጎቹ እረኛቸውን መቀማታቸው ሳያንስ፣ይባስ ብሎ ጩኸታቸውን መቀማት(ቀ ጠበቅ ብሎ ይነብብ) ግን የለባቸውም።የተዋህዶ እረኛ መርቆርዮስ ፣ሲጠብቃቸውና ሲንከባከባቸው ከኖረውና መንጋው ከሆኑት ከምዕመናን ሲለይ፣ጩኸት አለ፣መደናገጥ አለ፣ሀዘን አለ። ስለዚህ ሀዘናችን ይከበር። የጩኸቱ ምክንያት የእረኛው ከበጎች መለየት ብቻ ነውና ለጩኸቱ ምክንያት አይፈለግለት። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ውሻ፣በንጉሡ ላይ ተንኮል አስቦ በመጣ እንግዳ ላይ ትጮሀለች የሚባል ነገር አለና።አንድ ምንም ክፋትና ተንኮል በንጉሱ ላይ ያላሰቡ ልበ ቀና ሰው ወደ ንጉሡ ሲመጡ አይታ፣ያቺ ልማደኛ ውሻ እኒህ ሰው ላይ እየዘለለች መጮህ ስትጀምር፣በነገሩ ግራ የተጋቡት እንግዳም "" ኸረ ጃንሆይ ይቺ ውሻ ሰው ያላሰበውን ታሳስባለች "" አሉ ይባላል። ስለዚህ ዛሬም አደራ የምንላችሁ ነገር ያላሰብነውን አታሳስቡን ነው።አላማችን ከላይ የገለጽኩት አንድ እና አንድ ነው።እርሱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።በእውነት የዱስነታቸው በረከት ይደርብን። ምሕረተአብ አሰፋ መጋቢት 3/2014/ዓ/ም
4.4K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 21:20:21
3.5K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 16:35:36 የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በጥንታዊው የደብረ ብርሃን ቅድስተ ሥላሴ ተፈፅሟል።

ከሥርዓተ ቀብር በፊት ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የጸሎተ ፍትሐት መርሐ-ግብር ተካሂዶ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ በትግራይ እና በአርሲ ሀገረ ስብከቶች ቅድስት ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል። ብጹዕነታቸው በ97 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።
ቅድስት በረከታቸው በሁላችንም ላይ ትደር
3.5K viewsedited  13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 16:34:49
3.0K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ