Get Mystery Box with random crypto!

የሚካኤል አስጨናቂ እና የዘመኑ ተጋሪ ፀሀፍት ግጥሞች!

የቴሌግራም ቻናል አርማ michaelaschenakipoems — የሚካኤል አስጨናቂ እና የዘመኑ ተጋሪ ፀሀፍት ግጥሞች!
የቴሌግራም ቻናል አርማ michaelaschenakipoems — የሚካኤል አስጨናቂ እና የዘመኑ ተጋሪ ፀሀፍት ግጥሞች!
የሰርጥ አድራሻ: @michaelaschenakipoems
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 736

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-03 21:49:05 መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

(ሚካኤል.አ)
75 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 22:07:02 በማይፀፅት ትናንት ፡ በማይናፍቅ ነገ
መካከል ላይ ፍቅርሽ ፡ ስለተሰነገ፣
አልማትር ወደፊት ፡ አልዞር ወደኋላ
«አ...ሁን!» ነኝ ... «አ...ሁኝ!» ነሽ ፡ ከእንግዲህ በኋላ።
Red 8
85 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 20:34:23 የቤት አህያና የሜዳ አህያ
ሲኖሩ ሲኖሩ ...
መንገድ ሲያሳልጡ
እቃ ከጀርባቸው ሸክፈው ሲያኖሩ፤
ሰለቸና ወጣ የሜዳ አህያ
አህያ ግን ቀረ ከቤት ከገበያ።
እንዲህ በአንዳንድ ቀን
ሲበዛበት አደን ...
ሳሩ እሳት ገብቶት ሲኖር በሰቀቀን
ባልወጣሁ ምናለ?
ብሎ እንባ ይዘራል የሜዳ አህያ
አያውቅም እንዳለ ...
ስሙን የሚያወሳ መንገድ መሻገሪያ።
የሚል አለ ተረት ...
የአንዱ መለየት ነው
የሌላው ነፃነት ፤
ስንት እግር ተራምዷል
በእንባ ቀን ወ'ቶለት።

(ሚካኤል.አ)
132 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 19:04:58
72 views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 20:51:58 ሕልም ... ያለው
ሕልምም ያየው
ከተባለ ባለ ሕልማም
ከጥሪው ነው እንጅ
ከግብሩ አይሟላም !
ሕልም ታይቶት የመራ
በሕልም እንደመራ
ከተባለ መሪ ...
ችግር ይታየናል ከዚህ የቃል ጥሪ!
ስለዚህ ይወጠን ...
ስለዚህ ይታሰስ...
ከዚህኛው መዝገብ እስከዚያኛው ድረስ
ፈልጉ.. . ፈልጉ ...
ይፈለግ እንጅ ቃል ?
ቀለም ቆጥሯል ብለን አዋቂ ነው ያልነው
ለጠንቋይ ይሆናል።

(ሚካኤል.አ)
46 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-20 14:35:26 የልኳንዳ ቤት በር ቡችላ
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰፈራችን ባለው፥ የስጋ ቤት በራፍ
የገዛ ገላየን ፥እየጎተትኩኝ ሳልፍ
ሁልጊዜ የማያት ፥ ሚጢጢ ቡቸላ
ከስጋ ቤቱ በር ፥ ፊትለፊት ቁጭ ብላ
ወደ ሱቁ መስኮት ፥ አንገቷን አስግጋ
ትቁለጨለጫለች፥
ጅራቷን ከፍ አርጋ
እንደ ሰላም ሰንደቅ፥ ታውለበልባለች::

ነጋዴው በጠዋት፥ መስኮቱን ይከፍታል
ያቺን ግልገል ውሻ ፥ የጎሪጥ ያያታል
እንዳልተፈጠረች ወድያው ይረሳታል::
ቢላዋ ሰንዝሮ
ጎድን ከዳቢቱ፥ በየገጹ መትሮ
በግራም በኪሎ
ለየበላተኛው ሲያከፋፍል ውሎ
መስኮቱን ይዘጋል
ቀኑም እንደ ወትሮው ይመሻል ይነጋል::

ከዚያ በማግስቱም
ይቺ መከረኛ፤ የሙት ልጅ ቡችላ
የስጋ ትራፊ፤
ያጥንት ርጋፊ
ቢጥልልኝ ብላ
ትጠባበቃለች፤
ከስጋ ቤት በር ላይ ፥ ትቁለጨለጫለች
ያ ስጋ ቸርቻሪ፥ ባይለግሳት አዝኖ
ከሰው ንፍገት በላይ፥ ተስፋዋ መዝኖ
ምጽዋት ይጠብቃል፤ልቧ መቸ ቦዘኖ፤

እኛም እንደዚህ ነን፥
ሰላምን መጠበቅ፥ ከጦረኛ ዘመን
ከንፉግ ሰው ደጃፍ ፥ እንጀራ መለመን
መቸም የማይደክመን ፥
በገፊ መንደር ውስጥ፥ የሚያቅፈን ፍለጋ
እጅ የምንዘረጋ
ሞኝነት ቢመስልም፥ ለሚያየው በሩቁ፥
ተግቶ መጠበቁ
ከጦር ዘመን ሰላም ፤ ከንፉግ ሰው ሲሳይ
አንዳንድ ቀን አለ፥ ተአምር የሚያሳይ
አንዳንድ ቀን፥ አለ ፥ ተፈጥሮ ሚያስለውጥ
ስራት የሚያናውጥ
በዚህ ምክንያት ነው፥
ሰው ልምዶቹን ትቶ ፥ ህልሞቹን የሚያምነው::
65 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 19:40:45
111 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 08:13:51 [ . . . . . . ]
Henock Bekele

የቅርቡን ጨዋታ ፣ በሳቅ እያከሙ
የሩቁን በሩቁ ፣ ምኑንም ሳይሰሙ
የሕዝቡን ቀዳዳ ፣ ሲቀዱ ሲጠቅሙ
የመንደሩ ሰፊ ፣ ዘንድሮስ ደከሙ።
አዬ!!
.
እያጋቱ ኮሶ ፣ ወለምታ እያቀኑ
የስንቱን ስብራት ፣ በዘበት ያዳኑ
ያበጁትን ክኒን ፣ ለራሳቸው ውጠው
እጆቻቸው ዝለው ፣ ከጀርባቸው ጎብጠው
“ወንድ ልጅ አይደለህ?” ፣ ብለው ያጀገኑ
ተፋልመው ከዘመን ፣ እንደማይሆን ሆኑ።
አዬ!!
.
የተመካሁበት
በዓለም ስፋት ሄጄ ፣ ለመንደሬ ስቀኝ
እንኳንስ ሰው ሁሉ . . .
በሃው ድንጋይ እንኳ ፣ አርጅቶ ጠበቀኝ።

ወረት አይነካውም
“አይለወጥ” ያልኩት ፣ ያመንኩት አለፈ
እንኳን ፈገግታቸው ፣ ጥርሳቸው ረገፈ
አይምሬ ምስለኔ
በአፍላ ሌማቱ ላይ ፣ እግሮቹን ዘርግቶ
ጠበቀኝ ጀግኖቹን ፣ ለሞት አስጠግቶ

ቃልም ጠፋ ዜማ
ዐየሁ ጥበብ ዐየሁ
ደግሞም በዝግታ
ደግሞም በፀጥታ ፣ ልሂቅ የደረሰው።
ምን አለ ሙዚቃ?
የት ይገኛል ግጥም
ጊዜ በላዩ ላይ ፣ እንዳለፈበት ሰው ?
___________________
89 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 17:11:56 ማን ብዬ ልታዘብህ?! (በድሉ ዋቅጅራ)

ማን ብዬ ልታዘብህ፣
ማን ብለህ፣ ጥራኝ አልከኝ?
መቼም አንተን፣
ስም አይጠፋህ፣ መታወቂያ፤
ጥግ አይገድህ፣ መለጠፊያ፡፡

እስስት ሰብእናህ ይለዋወጣል፤
እባብ ገላህ ይገሸለጣል፤
የመሰልከውን፣
እንጂ
የሆነከውን፣
ማን ያውቃል?!

የትናንት ግፍህን ቋት፤
አድማስ ጨርሶ ሳይውጣት፤
ዳግም በዛሬ መንበር፣
አይንህን በጨው አጥበህ፤
ተኩላው የበግ ለምድ ለብሰህ፤
‹‹እኔ ነኝ!›› ያልከው፣
አንተ ማነህ?!

ከቋጠርከኝ ሀረግ ጫፍ ላይ፤
ከታች አንተ፣
ከላይ
ሰማይ፤
ከገደል
እንደበቀለ ቅል፣
ተንጠልጥዬ፤
እንትን እንደንካው እንጨት፣
ተነውሬ - ተገልዬ፤
እንዳለሁ፤
ከምኔው ሰቀቀኔ ገባህ?
ከምኔው ሞቴ፣ እንቅልፍ ነሳህ?
ከምኔው አዳኝነትን ተቀባህ?
ልትከልለኝ፣
ልታድነኝ፣
‹‹የፍቅር›› እጅህን ዘረጋህ?
ከምኔው?!

መቼም አንተ፣ . . .
እስስት ሰብእናህ ይለዋወጣል፤
እባብ ገላህ ይገሸለጣል፤
የመሰልከውን፣
እንጂ፣
የሆነከውን፣
ማን ያውቃል?!

ማንነት አያልቅብህ፤
ማን ብዬ ልተዋወቅህ?
ማን አልክ፣ ዘንድሮ ስምህን?
ትዝብቴን የማከታበት፣
ካደለኝ በቀል መቋጠሪያ፤
ማን አልከኝ፣ ያንተን መጠሪያ?
---------------
152 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 19:14:22 ቅንጥስ አልኩላት እንዳደይ ፅጌ
በልጅ ጉልበቴ በልጅ ማ`ረጌ
ለጉድ ጨስኩላት ከርቤ መስዬ
ተርከፈከፍኩኝ ሆንኩላት ሽቶ
አበራሁላት ዘመኑ መሽቶ
ደቀኩ እንዳፈር ቀናብኝ ጠጠር
የማይሆን ሆንኩኝ
የምትሆን ሆና እስክትፈጠር።
ወደመሆኗ ስትገሰግስ
ምትሳፈረው ሆንኩላት ፈረስ
ብዙም አትቆይም!
ምድር ቢያልፍ ነው እስከዛ ድረስ።
.
#ያዴል ትዛዙ
198 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ