LINK IN ጃም

የቴሌግራም ቻናል አርማ link_in1 — LINK IN ጃም L
የቴሌግራም ቻናል አርማ link_in1 — LINK IN ጃም
የሰርጥ አድራሻ: @link_in1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

@link_in1 @link_in1 አሳታፊ የሆኑ ጥያቄዎቻችንን በመመለስ ያሸንፉ እንዲሁም ድንቃድን መረጃዎችን ከመዝናኛው አለም ያልተሰሙ ወቅታዊ ዘገባዎች አዳዲስ የሐገር ውስጥና የባሕር ማዶ ነጠላ
ሙዚቃዎችን ና አልበሞችን
Win by answering our participatory questions as well Unheard and up-to-date information from the entertainment

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-29 21:49:08
ወንድሙን 30 ሜትር ገደል ወስጥ ገፍትሮ የገደለው ግለሰብ በ12 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሸይ ቤንች ወረዳ ባታ ቀበሌ ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት የገዛ ወንድሙን በዱላ በመደብደብና 30 ሜትር ገደል ዉስጥ ገፍትሮ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።

ፖሊስ ተጠርጣሪዉን በቁጥጥር ስር በማድረግ ባደረገዉ ምርመራ ከግል ተበዳይ የሆነዉ ወንድሙ ጋር በነበረዉ ፀብ ምክንያት በአከባቢዉ ባህል መሠረት ጉዳያቸዉ በሽማግልና ታይቶ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለታላቅ ወንድሙን እንዲክስ ብይን በሽማግሌዎች ይወሰንበታል።

ተከሳሽ ዉሳኔዉን ተቀብሎ እያለ ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም ገበያ አምሽቶ እየተመለሰ ያለዉን ወንድሙን መንገድ በመጠበቅ በያዘዉ ዱላ ከኃላዉ በመምታት መሬት ከጣለዉ በኃላ 30 ሜትር ገደል ዉስጥ ገፍትሮ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

የወረዳው ፖሊስ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን ሙሉ አበበ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በተከሳሽ የእምነት ቃልና በህክምና ማስረጃ አደራጅቶ ለዐቃቤ ህግ መላኩን ገልፀዋል። ዐቃቤ ህግም ተከሳሽ ደምሴ ሶኪያን በቂም በቀል ተነሳስቶ በፈፀመዉ የወንጀል ድርጊትግለሰቡን በግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት ያቀርበዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል። በዚሁ መሠረት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ደምሴ ሶኪያ በ12 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
758 viewsJOHN , 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 17:49:00
ህንዳዊው የፕላስቲክ የቀዶ ህክምና ዶከተር የ37 ሸህ ህጻናትን ፈገግታ በመመለሱ “ጀግና” ተሰኘ።

ዶከተሩ አብዛኛውን ጊዜውን የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን በቀዶ ህክምና የማስተካከል ስራ ላይ ነው የሚያሳልፈው የተባለ ሲሆን፤ ሁሉንም የቀዶ ጥገና ህክምናዎች በነጻ ማከናወኑም ተነግሯል።

ዶክተር ሱብዶህ ኩማር፤ የልጅነት ጊዜውን በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሳለፈ ሲሆን፤ ይህም የሰዎችን ችግር እንዲረዳ እንዳደረገው ይናገራል።

ዶከተሩ እነዚህ ህጻናት የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት የጀመረው ጥረት በኋላ ላይ በርካታ ትላልቅ ድርጅቶችን ስቦ በእነሱ ድጋፍ ስራውን መጀመሩንም አስታውቋል።

በዚህም ከከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ 37 ሺህ ህጻናትን የማስተካከል ቀዶ ህክምና በነጻ ማከናወን አንደቻለም ተነግሯል።

የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ህፃናት በአግባቡ ወተት የመጠጣት ችግር የሚያጋጥማቸው ሲሆን እድሜያቸው ከፍ ሲልም በሌሎች መገለል ችግር ይጠቅማቸዋል።

ይህ ችግር በቀዶ ህክምና የሚስተካከል ሲሆን ይህ ህክምና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ዋጋው የማይቀመስ ሆኖ በርካቶች ሲቸገሩም ይስተዋላል ሲል አል አይን ዘግቧል።
561 viewsJOHN , 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 13:04:50 የመጋቢት 17 ቀን 2014 የዓለም ዜና

• የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር እርቅ እንዲያወርድ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ-መንበር ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይኸን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ የኦፌኮ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ሲጀምር ነው።
• የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ መስተዳድር ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት የደረሱበትን ግጭት የማቆም ውሳኔ ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም ሥምምነት እንዲያሸጋግሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጥሪ አቀረቡ።
• ግብጽ 31 ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎች ያለባቸውን ሥጋት ችላ በማለት በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለሷ ከባድ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነቀፈ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሌሎች 50 ኤርትራውያን ወደ አገራቸው በግዳጅ ሊመለሱ በግብጽ በእስር ላይ እንደሚገኙ ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
• የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) በማሊ ላይ የጣለው ማዕቀብ ባለበት እንደሚቀጥል አስታወቀ። በጋና ሲካሔድ የነበረው የኤኮዋስ ስብሰባ ትላንት ሲጠናቀቅ በጊኒ እና በቡርኪና ፋሶ በመፈንቅለ-መንግሥት ሥልጣን ለያዙ ሹማምንት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
• የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከዩክሬን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በፖላንድ ፊት ለፊት ተገናኝተው ተነጋገሩ። የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድሚትሮ ኩሌባ "ወታደራዊ ስምምነታችን እንዴት ሊያድግ እንደሚችል ከአሜሪካ ተጨማሪ ቃል ኪዳኖች አግኝተናል" ሲሉ ከስብሰባው በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
471 viewsJOHN , 10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 10:39:25
ከ43 ሰው በላይ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የሰው ሕይወት ጠፍቷል።

ከደሴ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 11442 አማ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በ16/07/14 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ገደማ ረዳቱንና ሾፌሩን ጨምሮ ከ43 በላይ ሰዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ ሳለ በደረሰ አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ።

የትራፊክ አደጋው የደረሰው ላሊበላን አለፍ ብሎ ሰኞ ገበያ ከምትባል አካባቢ እንደሆነ የላሊበላ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችን ጠቅሶ ዋግኽምራ ኮሚውኬሽን ገልጿል።

በአደጋው አንድ ህጻን ልጅ ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተሳፋሪዎች ሕወታቸው ሲያልፍ፣ እስካሁን በተገኘ መረጃ 37 ተሳፋሪዎች ደግሞ ቆስለው በላሊበላ ሆስፒታል ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተገልጿል።

ተሽከርካሪው የትራፊክ አደጋው ደርሶ ተገለባብጦ ካረፈ በኋላ መቃጠሉን ገልጸው የቃጠሎ ምክኒያትም ከሰው ጋር የተጫነ ቤንዚል አብሮ በመኪናው ውስጥ መኖሩ እንደሆነ ተጠቁሟል።
448 viewsJOHN , edited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 10:39:25
382 viewsJOHN , 07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 16:49:27
በድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ሀሳብ አመንጪነት በተዘጋጀ የእራት ግብዣ በተገኘው ገቢ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ሊገነባ ነው

በድሬደዋ ከተማ በቀጣዮቹ 15 ቀናት ለሚገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል በናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር እና በድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን የድሬድዋ ከተማ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ማዕከሉ ግንባታ እንዲጀመር ለማድረግ የከተማዋ ከንቲባ ከዲር ጁሃር አንድ እራት በአስር ሺ ብር በማዘጋጀት በነዋሪዎች እና በውጪ ከሚኖሩ የድሬደዋ ተወላጆች ገንዘብ እንዲሰባሰብ አድርገዋል፡፡

የናሽናል ሲሚንቶ የማእከሉን ግንባታ ሙሉ በሙሉ በ5.5 ሚሊየን ብር ለመገንባት እንዲሁም ሌሎች ባለሀብቶች የኩላሊት እጥበት ማሽን በመግዛት እና ባለሙያዎችን ቱርክ ድረስ ሄደው እንዲሰለጡኑ እድል መመቻቸቱን የድሬደዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ የኩላሊት እጥበት ማእከሉ የሚገነባው በሳቢያን ጄነራል ሆስፒታል ውስጥ እንደሆነ እና በመንግስት ድጋፍ እና ክትትል እንሚደረግበት ወይዘሮ ለምለም አስረድተዋል፡፡

የኩላሊት እጥበት ማዕከል ህንፃ እጅግ በፈጠነና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ በ45 ቀናት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅና የናሽናል ሲሚኒቶ ሀላፊዎች መናገራቸውን እና የዚህ ማዕከል ህንፃ መገንባት የኩላሊት እጥበት የሚደረግላቸ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያወጡትን ከፍተኛ ክፍያ የሚያስቀር በመሆኑ ለግንባታው መፋጠን የበጎ ፍቃድ ሥራዎች ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች ሊረባረቡ እንደሚገባ ወይዘሮ ለምለም ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም አኳ ኡኖ የተጣራ ውሃ ማምረቻ ድርጅት ለኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ሁለት ነርሶችን ከኩላሊት እጥበት ጋር ተያይዞ ቱርክ ሃገር ሄደው እንዲማሩ ሙሉ ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል መግባቱ ተነግሯል፡፡
496 viewsJOHN , 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 15:24:41
ሰበር ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ

አቶ ተወልደ ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ለኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ተናግረዋል፡፡

ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም አቶ ተወልድ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
አቶ ተወልደ አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 አመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡

ምንጭ- ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
434 viewsJOHN , 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 16:59:50 በምሥራቅ ሸዋ ቡልቡላ ከተማ በሚሊሻ ምርቃት ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ቢያንስ አራት ሰዎች ሞቱ

በአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ቡልቡላ ከተማ ከ200 በላይ የሚሊሻ አባላት በተመረቁበት ወቅት በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የ12 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተጠናቅቆ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከመድረኩ ከተሸኙ በኋላ ሕዝቡና የሚሊሻ አባላት በደስታ እየጨፈሩ እያለ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ከሞቱን ውጭም 35 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣኑ ገልፀዋል።

አቶ ሙሐመድ አክለውም ፍንዳታውን በማድረስ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከምረቃ ፕሮግራሙ በፊት አነስተኛ ፕሮግራሞች እንደነበሩ ያስታወሱት ኃላፊው፣ ዋናው የምረቃ ፕሮግራም ከመጀመሩ በፊት ጥብቅ ፍተሻ እንደነበር በመግለጽ፣ የቦንብ ፍንዳታው የደረሰው ተቀብሮ ይሆን ተወርውሮ እየተጣራ ነው ብለዋል።

በፍንዳታው ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ ያገኙ ተጎጂዎች አብዛኛዎቹ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ገልፀው፣ ስድስት ሰዎች ግን እስካሁን ድረስ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

"ይህንን ቦንብ ያፈነዳው ጠላት" ነው ሲሉ የገለፁት ባለሥልጣኑ ፍንዳታውን ያደረሰው ማን እነደሆነ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል። ለቦንብ ፍንዳታው እስካሁን ድረስ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

በዚህ ቦንብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች በትናንትናው ዕለት የቀብር ሥነ ስርዓታቸው መፈፀሙን ተናግረዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
464 viewsJOHN , 13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 19:24:05
በሳውዲ አረቢያ በእሥር እና በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሰላሳ አምስት ሺህ ያህሉ ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸው ተገለፀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው 100 ሺህ ዜጎችን ከሳውዲ ለምምለስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በእሥር ላይ የሚገኙም ሆነ በውጪ ያሉት እንዲመለሱ ይደረጋል።
የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው መግለጫቸው የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ስላለው የጤና አገልግሎት ችግር መናገራቸው ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ዳይሬክተሩ ችግሩ በአማራም፣በአፋርም መኖሩን ቢናገሩ ተገቢ ነበር የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ የገቡት ሩሲያ እና ዩክሬን ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚያደርጉት ጥረት ገለልተኛ አቋም ስለመያዟ እና ሁለቱ አገሮች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ቢፈቱ ይሻላል፣ ለዓለምም የሚበጀው ይህ ነው በሚል አቋሟን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ግልጽ ማድረጓ በመግለጫው ተጠቅሷል።
528 viewsJOHN , 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 16:15:32
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዲሲፕሊን ምክንያት 146 አመራሮችንና አባላትን ማሰናበቱን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት የተለያዩ የዲሲፕሊን ጥፋት የተገኘባቸውን 146 የፖሊስ አመራሮችንና አባሎችን በፖሊስ ማባረሩን ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡

አመራሮቹና አባለቱ የተሰናበቱት በሰራዊቱ ህግና ደንብ መሰረት መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ ኮሚሽኑ፣ ይሄንን አይነት እርምጃ ሊወስድ የቻለው በስነምግባርና በአቅም ከተማዋን የሚመጥን የፖሊስ ሀይል ለማደራጀት መሆኑን ገልጿል፡፡

ፖሊስ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በተለያየ ደረጃ የፖሊስ አባል የነበሩና በአስተዳደር ችግሮች ሳቢያ ከሰራዊቱ ወጥተው የነበሩ ከ400 በላይ የቀድሞ አባላትን፣ በድጋሚ ወደ ሠራዊቱ መቀላቀሉን አስታውቋል፡፡

ወደ ስራ ገበታቸው የተመለሱት የቀድሞ የፖሊስ አባላት፣ በሰራዊቱ ውስጥ የነበረው አሰራር ቅሬታ ስላሳደረባቸው “መስራት አንፈልግም” በማለት ወጥተው የነበሩ መሆናቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል፡፡

ኮማደር ፋሲካ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የስድስት ወር ሥራ አፈፃፀምን አፈጻጸምን በሚመለከት እንዳብራሩት፣ በተለያየ መልኩ የተሰማሩ የፖሊስ አባላትን ስነምግባርን ለማሻሻልና ያለ አድልዎ እንዲሰሩ ለማስቻል የሪፎርም ስራዎችን እየተሠራ ነው፡፡

ሪፖርተር
446 viewsJOHN , 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ