Get Mystery Box with random crypto!

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአ | MHSS STUDENT LEARNING SYSTEM

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት መጋቢት 8 እና 9 /2015ዓ.ም. እንድትመዝገቡ እንገልፃለን።

፨ምዝገባ የምታካሂዱባቸው ግቢዎች

1ኛ. በማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ፣

2ኛ. በተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) ትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ

፨ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች እና የግል መገልገያ ቁሳቁሶች

1ኛ. የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት እንዲሁም ከ9ኛ --12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፣

2ኛ. አምስት የቅርብ ጊዜ ሦስት በአራት (3*4) ጉርድ ፎቶ ፣

3ኛ. ብርድልብስ፣አንሶላና የትራስ ጨርቅ መያዝ እንደሚጠበቅባችሁ እናሳውቃለን።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት