Get Mystery Box with random crypto!

#አምቦዩኒቨርሲቲ አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ የሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም | MHSS STUDENT LEARNING SYSTEM

#አምቦዩኒቨርሲቲ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የተመደቡ የሪሜዲያል (የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም) ተማሪዎችን የሚቀበልበት የመግቢያ ቀን መጋቢት 07 እና 08 2015 ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰው ቀናት ብቻ በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ በዋና ካምፓስ ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመደባችሁ አምቦ ከተማ ሃጫሉ ሁንደሳ ካምፓስ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ ጥሪ እያደረገ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨረሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ሁሉም ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-
- ከ8 –12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒ፡
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሳርትፍኬት ዋናውና ኮፒ፡
- 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ ብዛት 8:
- አንሶላ፡ ብርድልብስ፡ ትራስልብስ እና የስፖርት ትጥቅ::

ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት