Get Mystery Box with random crypto!

ከመላዕክት ጋር ሲገለጥ በሰማይ ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ በግርማው ሲመጣ | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

ከመላዕክት ጋር ሲገለጥ በሰማይ
ፀንተን እንጠብቀው ክብሩን ሁሉ እንድናይ
በግርማው ሲመጣ በአስደንጋጭ ሁኔታ
ወዮልሽ ነፍሴ ሆይ ወዮ የዛንለታ
ኧኸ ምስጋና ይድረስህ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
ሃሌ ሃሌሉያ የሠራዊት ጌታ(2)
ሰማይና ምድር ከፊቱ ሲሸሹ
መግቢያ አጥቶ ይጮሀል ትልቁም ትንሹ
ጻድቃን ሲደሰቱ የኃጥአን ፈንታ
ሆኖ ጠበቃቸው ለቅሶና ዋይታ
ስለማይታወቅ አምላክ አመጣጥህ
በሃይማኖት አፅናን ተግተን እንጠብቅህ
ጠላት እንዳይገዛን በእርሱ እንዳንረታ
እግዚአብሔር አድነን ሁንልን መከታ

@mezmurzhohte