Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ቀን አለ አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ ለጻድቃን የሚያበራ(2) ጌታ በዚያ ቀን ይመጣል በክብርም | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

አንድ ቀን አለ
አንድ ቀን አለ የሚያስፈራ
ለጻድቃን የሚያበራ(2)
ጌታ በዚያ ቀን ይመጣል
በክብርም ይቀመጣል(2)
አብረው ከእርሱ ጋር ይመጣሉ
ቅዱሳን መላዕክት ሁሉ(2)
ጌታ በዚያ ቀን ይመጣል
በዙፋን ይቀመጣል (2)
የምሕረት አዋጅ ይጠበቃል
ነፍስ ሁሉ ይጨነቃል(2)
ኃጥአን ሁሉ ያለቅሳሉ
በግራው ይቆማሉ(2)
ቅዱስ ቃሉን ሰምተው ያመኑ
የፀኑ በኪዳኑ(2)
አብረው ከእርሱ ጋር ይቆማሉ
ከኃዘን ይሠወራሉ(2)
መሐሪ ጌታ ፈጣሪያችን
ይድረስህ ልመናችን (2)
በዚያ ግሩም ቀን እባክህ
አቁመን በቀኝህ(2)

@mezmurzhohte