Get Mystery Box with random crypto!

ኃይልህ ሲገለጽ ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(2) አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ አቤት ቀርነ መ | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

ኃይልህ ሲገለጽ
ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(2)
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
አቤት ቀርነ መለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ
አቤት መላዕክት ሰማይን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ ድምፅ ሲሰማ ከራማ
አቤት ሰባት ነፋሳት ተከፍተው
ምድርን ሲያውኳት ቀስፈው
ሲታዘዝ የ ባሕር ሞገድ
ምድሪቷ ሲከድናት ለፍርድ
አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሠሩ ቡሩካን
በምድር የሠሩ ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት



@mezmurzhohte