Get Mystery Box with random crypto!

ጾም ታድናለች ነቢዩ ዳንኤል በጾም ስላመነ ከአንበሶች ጒድጓድ ሕይወቱን አዳነ ኤልያስ የወጣ በእሳት | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

ጾም ታድናለች
ነቢዩ ዳንኤል በጾም ስላመነ
ከአንበሶች ጒድጓድ ሕይወቱን አዳነ
ኤልያስ የወጣ በእሳት ሠረገላ
በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ
የነፍስን ቍስል ጾም ታድናለች
የሥጋን ፍላጎት እያደከመች
እስቲ ልብ እናድርግ እናስተውል ደግሞ
ጌታ ለሐዋርያት ያላቸውን ቀድሞ
ይህ ርኩስ መንፈስ ሊወጣ የሚችል
በጾም በጸሎት ነው እንደ ወንጌሉ ቃል



@mezmurzhohte