Get Mystery Box with random crypto!

ዓለምን ዞሬ ዓለምን ዞሬ አየሁት ሁሉን በተራ ቀመስኩት ፈጽሞ የለም(2)ሰላም እንደ ልጅሽ ቤ | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

ዓለምን ዞሬ
ዓለምን ዞሬ አየሁት ሁሉን በተራ ቀመስኩት
ፈጽሞ የለም(2)ሰላም እንደ ልጅሽ ቤት
ሀብት ንብረቴን ጨረስኩና ጉልበቴ ሁሉ ደከመና
ጐስቋላ ሆንኩኝ(2)ደካማ የሌለው ጤና
ስቃ አሳስቃ ተቀብላ መልኳን አስውባ ተኳኩላ
ዛሬ ጣለችኝ (2)ይህች ዓለም አይረባም ብላ
የትናንትና ወዳጆቼ ዛሬ ሲሆኑ ጠላቶቼ
ባክኜ ቀረሁ(2) በዓለም ላይ ተንከራትቼ
የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ ፍቅሩ ምሕረቱ ትዝ ሲለኝ
ሁሉንም ትቼ(2) ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ
ልጁም እንድባል ባይገባኝ ባርያው እሆን ዘንድ ቢፈቅድልኝ
ጐስቋላው ልጁ ደካማው ልጁ ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ
እናቴ አንቺን ንቄ ትቼ የአባቴን ቤት እረስቼ
ተሰቃየሁኝ ተንከራተትኩኝ ልደሰት በዓለም ገብቼ
አባቴ ሲያየኝ ተደስቶ ጐረቤቶቹን ሁሉ ጠርቶ
ሠርጉን ደገሰ(2)የበደልኩትን እረስቶ
እስካሁን ድረስ በድያለሁ ዓለም ደህና ሁኚ አብቅቻለሁ
ወደ አባቴ ቤት(2)ዳግመኛ ተመልሻለሁ(3)



@mezmurzhohte