Get Mystery Box with random crypto!

✞ በስባረ አፅሙ በስባረ አፅሙ በገድለ ድካሙ  በፀናበት በአስቦ ገዳሙ  ስድስት ክንፍ አገኘ  | መዝሙረ ዳዊት

✞ በስባረ አፅሙ

በስባረ አፅሙ በገድለ ድካሙ 
በፀናበት በአስቦ ገዳሙ 
ስድስት ክንፍ አገኘ  
ተክለሃይማኖት ምድራዊ መልዐክ ተሰኘ 
 
ትናገር ደብረ አስቦ የተጋደለባት  
ተክልዬ በአንድ እግሩ ቆሞ የፀለየባት 
በመላዕክት ከተማ ህብረት የፈጠረ 
ከካህናተ ሰማይ መንበሩን ያጠነ 
 
አዝ___
 
ቅዳሴ ቀድሷል ሚካኤል ተራድቶት 
ወንጌልን መስርቷል በፅላልሽ ዳሞት 
ተክለሃይማኖት ፃድቁ አዲስ ሐዋርያ 
ሞገሷ ነህ አንተ ለኢትዮጵያ 
 
አዝ___
 
የመንፈስ ልጆችህ አእላፍ ሆነዋል 
በፀሎትህ ታምነው ቤትህን ሞልተዋል 
የላመ የጣመ መና በሌለበት 
ዳቤው ንፍሮው ውሃው ውበት 
 
አዝ___
 
እፁብ ነው ድንቅ ነው የተሰጠህ ፀጋ 
ቋጠሮ ቢፈታ ከአንተ የተጠጋ 
የፃድቅ ሰው ፀሎት ምልጃው ይፈውሳል 
ተክልዬን ያመነ ኧረ ምን ይሆናል

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

    ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥