Get Mystery Box with random crypto!

ስላም ለሰኮናከ ዘተሴሬ በደም አመ እግርከ ተሰብረ በብዙኃ ቀዊም ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ | መዝሙረ ዳዊት

ስላም ለሰኮናከ ዘተሴሬ በደም አመ እግርከ ተሰብረ በብዙኃ ቀዊም ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ ኢዮብ ዘትዕግሥትከ ፍጹም ለደቂቅከ እለ ውስተ ኵሉ ዓለም ከመ ባረኮሙ ኖኀ ለያፌት ወሴም

   መልክአ ተክለሃይማኖት

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለሐዲስ ሐዋርያ ለመምህረ ትሩፋት አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓል  አደረሳችሁ አደረስን

ጥር ፳፬(24) ወስብረተ እግሩ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ማርያም እስክንድራዊት ወአባ አብሳዲ ወሲፉ ሰማዕት ወአባ መርሐ ክርስቶስ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እስመ መምህር ህግ ይሁብ በረከተ
ወየሁውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያሰተርኢ አምላክ አማልክት በጽዮን

✤ ትርጉም ✤

የህግ መምህር በረከትን ይሰጣልና
ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል

              መዝ ፹፫-፮
                     83   6

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፭ ቁ ፩-፲፯
            5    1   17

የቅዳሴ ምንባባት

ቲቶ ም ፪ ቁ ፩-፱
፩ ጴጥ ም ፫ ቁ ፩-፭
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ካህናቲከ ይለበሱ ጽድቁ
ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ
በእንተ ዳዊት ገብርከ

ትርጉም

ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው
ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ

            መዝ ፻፴፩-፱
                   131   9

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፲፰ ቁ ፩-፱
           18    1   9

❖ ቅዳሴ ❖

ዘባስልዮስ

" አቤቱ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን ቅዱስ ስምህን ለሚወዱ ያዘጋጀህ አምላክ ምን ትደንቅ "
            ቅዳሴ ባስልዮስ
               ም ፩ ቁ ፻፴፪
                    1     132

❖ ማሳሰቢያ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ጥር ፳፬ ቀን የሚከበረው የአንድ እግራቸው አገዳ ከመቆም ብዛትና የተሰበረበት ቀን አንድ እግራቸው አገዳ የተሰበረው ጥር ፬ ቀን ነው ግን አባቶች በሠሩት ሥርዓት በዓላቸው በሚከበሩበት ዕለት በ፳፬ እንዲሆን በማድረጋቸው ጥር ፳፬ ቀን ይከበራል
 
በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ በረከት በዓለ ፀጋ ያድርግልን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን እናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክትን አያሳጣን ከአባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸው ይደርብን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ዝማሬ ዳዊት ቅዳሴ መላዕክት ዕጣነ አሮን መልክአ ተክለሃይማኖት የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለአበው ቅዱሳን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ለቅዱስ ደቅስዮስ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለአባ ኪሮስ ለአቡነ አቢብ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለአባ ሳሙኤል ዘቀልሞን ለገብረክርቶስ መርዓዊ ለአቡነ ሃብተማርያም ለቅዱስ ላሊበላ ለአባ ጽጌድንግል ለአባ ገብረማርያም ዘደብረ ሐንታ ለአባ ገብረኢየሱስ ዘመጓዬና ለቅዱስ ቴዎድጦስ ዘእንቆራ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ለአበው ቅዱሳን ሁሉ የተለመነች እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ሁላችንም ለንስሐ ያብቃን አቤቱ ባሪያህ የሚሆነው ሳዕለ ሥላሴን አስበው ወጣትነታችን አምላክ መርቆሬዎስ ይጠብቅልን ክህነት ያላችሁን አምላክ ተክለሃይማኖት ክህነታችሁን ይጠብቅላችሁ ውዳሴዋን ቅዳሴዋን አይሳታጎልብን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥