Get Mystery Box with random crypto!

✞ አምላኬ መቅደስህን አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ ሰላምህ እንድሆን | መዝሙረ ዳዊት

✞ አምላኬ መቅደስህን

አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ
ሰላምህ እንድሆን
በቤት በደጄ(ወደ ማደሪያህ ልምጣ ማልጄ)2/
      

እንድሰለጥን በመላእክት ዜማ
የህይወትን ቃል ከአፍህ ልስማ
እንዲቀል ሸክሜ ከትከሻዬ
ወደ ዙፋንህ ልምጣ ጌታዬ

   መልካም በሚሏት በመቅደስህ
   ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ

       አዝ-----

ተመለሠልኝ ደስታ ሠላሜ
ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ
ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ
ወደ ማደሪያህ በመገስገሴ

       አዝ-----

የተማርኩባት የመላዕክት ቅኔ
የተባረከው እድሜ ዘመኔ
የተለወጠው ሞቴ በህይወት
እናፍቃለሁ የእግዚአብሄርን ቤት

       አዝ-----

የሰማይ ዜማ የሚሰማባት
ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት
የጸሎት ስፍራ የአምልኮ ቦታ
ቤተክርስቲያን ውዷ ስጦታ

             ዘማሪ
  ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
    ✥     @mezmurochh    ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥