Get Mystery Box with random crypto!

​✞ አድነኝ አምላኬ አድነኝ አምላኬ አድነኝ አድነኝ ጌታዬ አድነኝ አልቋል ከምድር ላይ ደግ ሰው | መዝሙረ ዳዊት

​✞ አድነኝ አምላኬ

አድነኝ አምላኬ አድነኝ
አድነኝ ጌታዬ አድነኝ
አልቋል ከምድር ላይ ደግ ሰው
እንባዬን ከአይኔ ላይ አብሰው/፪/

       ፍቅር ከሰው ልጆች ቀዝቅዞ
       ትዉልዱ በበደል ተይዞ
       ወዳጅ በወዳጁ ጨከነ
       ወዉደዱ የሽንገላ ሆነ/፪/

        አዝ_____

ሆኖበት ክብሩ በነውሩ
ተጣሰ የፍቅር ድንበሩ
ደርቦ የማይሞቀዉ ሆነ
ደስታዉ ከእጁ ላይ ተነነ/፪/

አዝ____

        ለቃልህ መታዘዝ ዘነጋ
        ተክዞ መሽቶ እየነጋ
        ለክፉ አሳልፎ ሰጠ
        ወንድሙን በነዋይ ለወጠ/፪/

         አዝ____

ትንኝን ያጠራል ከሰው ላይ
በራሱ ምሶሶዉን ሳያያይ
ይሆናል የወንድሙ ፈራጅ
ተይዞ በእግዚአብሄር እጅ/፪/

አዝ____

     ተሰዶ ሲኖር በባእድ
     ሲገባው ሁሉም ሊዋደድ
     አንዱበአንዱ ላይ ይነሳል
     አካሉን ቀኝ እጁን ይንቃል
     ወንድሙን እህቱን ይንቃል

                  ሊቀ-መዘምራን
              ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

    ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

      ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
       ✥     @mezmurochh    ✥
       ✥     @mezmurochh    ✥
       ✥     @mezmurochh    ✥
       ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

      ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥