Get Mystery Box with random crypto!

ተነግሮ የማያልቅ ተነግሮ የማያልቅ ነው ጸጋህ/2/ በጸሎት የተጋህ የሐይማኖት ፍሬ ተክለ-ሃይማኖ | መዝሙረ ዳዊት

ተነግሮ የማያልቅ

ተነግሮ የማያልቅ ነው ጸጋህ/2/
በጸሎት የተጋህ የሐይማኖት ፍሬ
ተክለ-ሃይማኖት የእምነቱ ገበሬ /2/

  
በወንጌል ብርሀን ሕዝቡን የመራኸው
የኃጢአቱን ባህር ከፍለህ ያሻገርከው
ኢትዮጰያዊው ሙሴ በመስቀልህ ባርከን
ፍሬ እንድናፈራ ንጹሕ ዘር አድርገን /2/

አዝ-----------

ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት
ወንጌል ያስተማርከን ለክርስቶስ መንግስት
ፀበልህ እንዲምረን ውረድ አባታችን
በእጣንህ መአዛ ይፈወስ ደዌአችን /2/

አዝ-----------

ለማጠን የበቃህ የሥላሴን መንበር
ሰይጣን ከቶም አይደርስ በሄድክበት ሀገር
ለህሙማን ሁሉ የሆንካቸው ፈውስ
ጠብቀን ተክልዬ በሥጋም በነፍስ/2/

አዝ-----------        

በጣሙን የበዛ ትሩፋት ምግባርህ
ፀሎትህን ያልተውክ ቢቆረጥ አንድ እግርህ
ምዕራፈ ቅዱሳን የወንጌል ገበሬ
እኛንም አድነን ከዚህ አለም አውሬ /2/

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥    
@mezmurochh     ✥
   ✥    
@mezmurochh     ✥
   ✥    
@mezmurochh     ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥