Get Mystery Box with random crypto!

ጉባኤ አቅሌስያ     የእግዚአብሔር ፍቅር የበዛላችሁ የሊቀ መላእክቱ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ሆይ | መዝሙረ ዳዊት

ጉባኤ አቅሌስያ

    የእግዚአብሔር ፍቅር የበዛላችሁ የሊቀ መላእክቱ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ሆይ እነሆ በጎ ስራ በመስራት እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ጊዜ ደረሰ።

    በማዕከላዊ ጎንደር በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከፍተኛ የሆነ የህልውና ችግር አጋጥሞታል።
    
      ስለክርስቶስ ስም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ገዳማውያን አበው መነኮሳት እና መነኮሳይት ከማይታየው ፣ ከማይዳሰሰውና ከማይጨበጠው ጠላታችን ጋር በፆም በፀሎት  ሲዋጉልን በአለም ከሚገጥማቸው ችግር ደግሞ ልናግዛቸው የመንፈስ ልጆቻችሁ አለን ልንላቸው ይገባናል።

     ስለሆነም ገዳሙ ከቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማህበር ጋር በመተባበር ግንቦት 6 ቀን  2015 ዓ.ም ታላቅ የሆነ ጉባኤ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮኒቨርስቲ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ አዘጋጅቷል።
   

    በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል

    1- መምህር ጳውሎስ መልከዐ-ሥላሴ
    2- መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየዉ
    3-መምህር አንተነ አበበ እና ሌሎች መምህራን

    እንዲሁም  በዝማሬ
      1- ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
      2- ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሰ እና ሌሎችም የሚቀርብ ሲሆን

የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችም በተለያዩ አርቲስቶች
    1-አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ እና ሌሎችም ይቀርባል


ኑ የወንጌል ማዕድ እየተቋደስን ስለኛ የተራቡ ገዳማውያንን አለን እንበላቸው።

ለበለጠ መረጃ:-0986348964 ወይም 0912779749

ገዳሙን ድጋፍ ማረግ ለምትፈልጉ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ሙት አንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል ገዳም 

ወዳጄ ሆይ የቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና የህወታቸው ኑሮ ለሁሉም መልካም ምሳሌና አርአያ ሊሆን ይችላል ።