Get Mystery Box with random crypto!

Metti high school ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ mettihighschool — Metti high school ™ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mettihighschool — Metti high school ™
የሰርጥ አድራሻ: @mettihighschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 194
የሰርጥ መግለጫ

❇ Learning is a key of knowledge
📌 For any comment
contact us ▮
▮ @Mettihighschoolbot

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-22 09:44:45 የትንሹ ሜጢ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 16/2014 ጀምሮ ስለሆነ ሁሉም ተማሪ በት/ቤት በመገኘት ፎርም እንዲሞላ እናሳውቃለን።
የት/ቤቱ ጽ/ቤት
122 views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 08:00:11
ለዩኒቨርሲቲ ፣ ለመሰናዶ ፣እና ወደ ግቢ ለምትገቡ ተማሪዎች ዛሬ ምርጥ ቻናል ላስታውሳችሁ...! ፦

ከsenior ተማሪዎች ስለ ጊብ life
የዩንቨርስቲ ጥሪ
PDF
PPT
past Mid Exams
Past Final Exams

ሌሎችም ትምህርት ነክ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት ድንቅ ቻናል ነው

አሁኑኑ ይቀላቀሉ
https://t.me/poshacademy
https://t.me/poshacademy
199 views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 20:51:13 Metti high school pinned « ዘንድሮ 12 ተኛ ኢንተራንስ ለወሰዳችሁ ተማሪዋች ይህም እንደሚታወቀው የ 12 ክፍል ፈተና መውሰዳችሁ ይታወቃል እናም ከትምህርት ሚኒስቴር ኦርጂናል ዶክመንት ወይም ማለፋችሁን የሚያረጋግጥ የእውቅና ወረቀት እየጠበቃችሁ እንደሆነ ይታወቃል እናም ይህ ዶክመንት ወደ ት/ቤታችን ስለተላከ ፈተና የወሰዳቹበት ጣቢያ ድረስ መታችሁ ዶክመንታችሁን እንድትወስዱ ስንል እናሳስባለን:: የት/ቤቱ ጽ/ቤት…»
17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 20:44:53 የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል።

የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን መረጃዎች እንዲያስተካክሉ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ትላንት ተጠናቋል።

መቼ ተማሪዎች ተመድበው ትምህርት እንደሚጀምሩ ግን እስካሁን አይታወቅም።

በውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ላይ ከተነሳው ቅሬታ ባለፈ ወደዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይገቡ ሌላው ቀርቶ የት እንደሚማሩ ሳያውቁ ለወራት ለመቀመጥ ተገደዋል፤ ይህም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

መንግስት እየተነሱ ላሉ ቅሬታዎች ያለውን ምላሽ በፍጥነት እንዲሰጥና ሌሎች ውጤት የመጣላቸውና ወደ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል ያለባቸውን ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ትምህርት እንዲያስገባ ከወላጆችና ተማሪዎች እየተጠየቀ ይገኛል።

ይህ ዓመት ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት የቀረው ሲሆን እስካሁን ተማሪዎች አልተመደቡም፤ ዩኒቨሲቲዎችም መቼ ጥሪ እንደሚያደርጉ አይታወቅም።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተነሳ ጊዜ አንስቶ በኃላም በሰሜን ኢትዮጵያ የተነሳው ጦርነት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከባድ ሆኖ ቀጥሏል።

በትግራይ ተማሪዎች የ2012ና የ2013 ፈተናን አልወሰዱም የ2014 ስለመውሰዳቸውም አጠራጣሪ ነው።

በሀገር ደረጃም የትምህርት መርሃግብሩ ቀድሞ ወደነበረበት ሊመለስ አልቻለም። ይህ ትውልዱ ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መፍትሄ ያሻዋል።

@mettihighschool
@mettihighschool
394 viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 20:26:57 ዘንድሮ 12 ተኛ ኢንተራንስ ለወሰዳችሁ ተማሪዋች


ይህም እንደሚታወቀው የ 12 ክፍል ፈተና መውሰዳችሁ ይታወቃል እናም ከትምህርት ሚኒስቴር ኦርጂናል ዶክመንት ወይም ማለፋችሁን የሚያረጋግጥ የእውቅና ወረቀት እየጠበቃችሁ እንደሆነ ይታወቃል

እናም ይህ ዶክመንት ወደ ት/ቤታችን ስለተላከ ፈተና የወሰዳቹበት ጣቢያ ድረስ መታችሁ ዶክመንታችሁን እንድትወስዱ ስንል እናሳስባለን::

የት/ቤቱ ጽ/ቤት

@mettihighschool
@mettihighschool
303 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 09:30:53 #MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ምንጭ.-ቲክቫ ሀቪ

@mettihighschool
@mettihighschool
352 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 23:34:15 #inbox_yetalake_Melikt
ትውልድ
-----------------------
ትምህርት ሚንስቴር የ 2013/14 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ላይ #በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ነው የሰራው።

1- ገና ሲጀመር የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና ያለ ምንም #ስርቆት ከተጠናቀቀ ቦሀላ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ማለፊያውን በጣም ዝቅ በማድረግ ወዳቂውን ተማሪ እንደገፍ ማሳለፍ።

2- በ11ኛ ክፍል የት/ት ዘመን 2012 በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ 2ኛው ሴሚስተር #ሳይማሩ ቀርቷል፣ እንዲሁ ተማሪዋቹ ከ8 ወር በላይ ያለ ት/ት ቤታቸው እንዲቀመጡ ተደርጓል። እናም ተማሪዎች በ2013 አ/ም የ11ኛ ክፍልን #ሳይጨርሱ 12ኛ ክፍል እንዲገቡ ተደረገ።

4- ከዛም የመንግስት ት/ት ቤት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲማሩ ግን እንደድሮው በተከታታይ ቀናት አልነበረም፤ በሳምንት #ሶስት ቀናት ነበር የተማሩት፣ በተመሳሳይ የግል ት/ት ቤቶች ግን #ሙሉ ሳምንቱን አንድም ቀን ሳይዘሉ ነበር ሲያስተምሩ የከረሙት።

5- ይህ ታድያ ለአብዛኞቹ የመንግስት ት/ት ቤቶች መፅሀፍትን ለመጨረስ #በቂ ጊዜ አልነበረም። በግል ት/ት ቤቶች ግን መፅሀፍትን በተያዘላችው ጊዜ መጨረስ ችለዋል።

6- እንዲሁም በ2013 በተቀሰቀሰው ጦርነት፥ በጦርነት አካባቢዎች የነበሩ #ተማሪዎች ለጥናት እና ለመማር ማስተማር አስችጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነበር ያሳለፉት።

እንደ ከዚ በፊቱ መንግስት የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት #የኢንትርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ይዘጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን አገልግሎቱ በ #VPN እንዲሰራ ተደርጎ ነበር።

ፈተናዎቹ ሲሰጡ በነበረው መጭበርበር ሙሉ በሚባል ደረጃ ፈተናዎቹ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፃች #ተለቀቁ።
ላንብብ ብሎ ደብተሩን የያዘው ተማሪ እንደ ጅል ጥናቱን ትቶ ስልኩን ይዞ የነበረው እንደ ብልህ ነው የታየው። ፈተናዎች በ #Telegram #tiktok... በስርአት በቀይ እስብርቶ መልሳቸው ተከቦበት ነበር የወጡት። ከዚህም ባለፈ ፈተናዎቹ ከባድ ነበሩ የመንግስት ተማሪዎች በፍፁም #ያልተማሯቸው የ 11ኛ ክፍል 2ኛ ሴሚስተር እና እና የ12ኛ ክፍል ጥያቄዎች ተካተውበት ነበር።

ታድያ ይህን ሁሉ በመረዳት መንግስት ተማሪዎችን መርዳትና መደገፍ ሲገባው ጭራሽ ማለፊያው ታይቶ #በታሪክ የማይታዋቅ ሆኗል።
ከዚህም ይባስ ተብሎ በመጨረሻ ቀን የተሰጠው #የCIVIC ፈተና በቀን ብዛት ወሬው ደርሶት ከተለቀቀው የሰራው ምስኪኑ ተማሪ ስለበዛ #የCIVIC ፈተና እንዳይያዝ ተደረገ።
ማለትም ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ #600 እንዲያዝ ፤ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ #500 እንዲያዝ ሆነ።

አስተውሉ
ማለፊያ ለወንድ በ ተፈጥሮ ሳይንስ #363

ይህ ማለት ፈተናው ከ 700 የሚያዝ ቢሆን ማለፊያ #423 ሊሆን ነው ማለት ነው።

ከዚ በፊት የሚታወቀው የግል ሴክተሩ በደንብ እንዲሰራበት ማለፊያ ዝቅ ሲደረግ ነበር ባሁኑ ግን እንዲያውም #300 ሆኗል።
#የደሀ ልጅ ጎዳና ላይ ይውደቅ የሚል ውሳኔ ተላልፏል። ከአንድ ት/ት ቤት እንዴት ሁሉም ተማሪ ይወድቃል? በአሁኑ የታየው እንግዲ ይሄው ነው ከአንድ ት/ት ቤት አንድም ሰው ማለፍ ያልቻሉባቸው ብዙ የ መንግስት ት/ት ቤቶች ናቸው።

ተማሪ እንዳይማር የሚደረግበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ት/ት ሚኒስቴር በአስቸኳይ ማስተካከያ ያድርግ #ማለፊያ በደንብ ይቀንስ፣ #ለግል መግቢያም ያስተካክል እናም በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች በደንብ ማስተካከያ ይወሰድ።


@Mettihighschoolbot
279 viewsedited  20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 07:11:10 #ASTU #AASTU

በ 2014 ዓ.ም ወደ ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች

ከታች በተዘረዘሩት የመፈተኛ ጣቢያዎች የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ከላይ የተያያዘውን የኤክስ ኤል ፋይል በመክፈት የመፈተኛ ጣቢያችሁን በአድሚሽን ቁጥራችሁ አማካይነት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

1. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
2. አአዩ ጥቁር አንበሳ መፈተኛ ጣቢያ(ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)
3. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
4. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
5. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
6. ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
8. ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
9. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
10. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
11. ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ መፈተኛ ጣቢያ
12. አምቦ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
13. አአዩ አራት ኪሎ መፈተኛ ጣቢያ(አራት ኪሎ)
14. አአዩ FBE campus (6 killo)
15. አአዩ (EIABC) መፈተኛ ጣቢያ( ልደታ ፍርድቤት ጎን)
16. አአዩ አምስት ኪሎ መፈተኛ ጣቢያ(አምስት ኪሎ)
17. አአዩ ኮሜርስ መፈተኛ ጣቢያ(ኮሜርስ)
18. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

@Mettihighschoolbot
202 viewsedited  04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 07:08:36
#MoE

የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦

#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች !

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351

• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300

• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254

• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250

• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250

• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250

(የ2ኛው ዙር ተፈታኞች የመቁረጫ ነጥብ ሙሉ መረጃ ከላይ በምስሉ ተያይዟል ያንብቡ)

መረጃ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiostudent4bot

ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች

@ @Mettihighschoolbot
174 viewsedited  04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 20:37:59 #MoE

ወደመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ልካችኃል።

እኛም ጉዳዩን ችላ አላልነውም።

በዛሬ ዕለት ከመቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን እስካሁን የመቁረጫ ነጥብ እንዳልታወቀና የትንተናው ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቆናል።

መቼ ይፋ ይሆናል ? ለሚለውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄም ሚኒስቴሩ በዚህ ቀን የሚል የተቆረጠ ቀን ባይገልፅም ፤ የትንተና ስራው እየተሰራ በመሆኑ ሲጠናቀቅ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

ውድ የቲክቫህ አባላት አዲስ መረጃ ሲደርሰን ወዲያው የምንልክላችሁ ይሆናል።



https://t.me/mettihighschool
209 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ