Get Mystery Box with random crypto!

መጽሐፍ ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafbet — መጽሐፍ ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafbet — መጽሐፍ ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @metsihafbet
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.13K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አስተያየት @book_comment
👇👇👇👇👇👇join @metsihafbet👈

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 21:49:44 #they_dont_care_about_us
#The_people_must_stop_the_war

... ተመልከት ከንጉሡ ጀምሮ የፖለቲካ እሳት ድሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎችን አቃጥሎ አያውቅም።ከላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫወት... እዚህ አገር ተምሮ እና ተንደላቆ የሚኖረው ብዙኃኑ "ግፋ በለው!" ሲል የኖረ ነው። መንግሥቱ ኃ/ ማርያም ያንን ሁሉ የድሃ ልጅ ማግዶ እሱ ዛሬ የት ነው!? "ዙንባብዌ" ተንደላቆ ይኖራል። የኦነግ መሪዎችን ተመልከት ...…ወያኔዎችን ተመልከት ...ምን ሆኑ ? ኢትዮጵያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ወጣቱ ነው የሚማገደው ! ሚስኪን ወጣቶች! በፖሮፓጋንዳ ያበደ አለማስተዋል ነው። ወጣት አልዋጋም ካለ ....መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገኛቸው! እንዲች ብለው #ስንጥር አያነሱም። ምድረ ደም መጣጭ! ስንት ጓዶቻችን በርሃ ላይ ቀሩ ! ስንት 'ጂኒየሶች!' እንኳን ጦርነቱ የፖለቲካ ወሬው ያደንዝሃል። ከዚህ ከበከተ እንቶፈንቶ ራቅ ! ተማር ! ተማር ! ተማር ! አሁንም ተማር ! ማንም መሃይም መተኮስ ይችላል ! መግደል ጀብዱ አይደለም÷ ጅብም ሰው ይገድላል። ታይፎይድም ÷ወባም ሰው ይገድላሉ! ዓላማ የሌለው ሞት ; አገር ሸርፎ ከመሸጥ እኩል ነው። ለምንድን ነው የምትሞተው !? ለምንድነው ወጣት የሚሞተው !? ...ሊታረድ እንደሚነዳ በሬ የማይረባ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ ይወስዱታል። ወጣቱም ብልጥ የሆነ ÷ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ ÷ የመጠቀ አድርጎ ራሱን ያያል ÷ ሲስተሙ ነው እንደዚያ የሚያደርግህ። ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ ....አለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው።ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ። ፈሳሽ ውሃ ነው ÷ ቅርፅ የለውም ። አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን ይመስላል ÷ እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን ....ሁላችንም ብርጭቆዎች ነን ። በስልጣን ከፍ ያሉት እያጋጩ 'ችርስ' የሚባባሉብን"

#አሌክስ አብርሃም
ከዕለታት ግማሽ ቀን ገፅ 132-133
1.6K viewsmelat..., 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:35:16 #ምንም__የለኝም_ደሃ_ነኝ_አትበሉ !
፦አንብቡት
አንድ ደሃ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በዚያ ያገኛቸውን መነኩሴ አባት ለምን በጣም ደሃ ሆንኩ ብሎ ? ጠየቃቸው ። እሳቸውም የምትሰጠው ብዙ አለህ እኮ ግን አላወቅከውምን ? ብለው በጥያቄ መለሱለት ። ደሃውም የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም አላቸው ። እኚህ አባትም ከማንም የማያንስ የምትሰጠው ብዙ ነገር አለህ ተመልከት ፦

#ፊትህ ፦ ይስቃል ፥ ይደሰታል ለደስተኞች ፈገግታህን ትሰጣለህ ታካፍላለህ!

#አፍህ ፦ ውብ የሆኑ ቃላትን ትናገርበታለህ ፥ ታመሰግንበታለህ ፥ ሰዎችን ታበረታታለህ ፥ ትመክራለህ ፥ ታፅናናበታለህ!!

#ልብህ ፦ ለመልካምነት ፥ ለእውነትናና ለትህትናን ልብህ ክፍት ነው!

#ዓይንህ ፦ ዓይንህ ጎስቋላና ችግረኞችን በፍቅርና በደግነት ትመለከታለች!! በሀዘን ለተዋጠው ዕንባን ትሰጣለች!

#ሰውነትህ ፦ አቅም ያነሳቸውንና ጉልበት የሌላቸውን ታግዛቸዋለች ። ተመልከት ይሄን ሁሉ መስጠት ከቻልክ አንተ ደሃ አይደለህም..!!

#ተወዳጆች ያለንን ብናውቅ ፈጣሪ ያስቀረብን አንዳች የለም ከሁሉም በላይ አንድያ ልጁን ሰጥቷል ከዚህ በላይ ደግነት የለም!! ስለዚህ እናንተ ደሃ አይደላችሁም ፈጣሪ ያላችሁ ባለጠጎች እንጂ!

፨ እውነት ነው አምላኬ ሆይ ለኔ የሰጠህኝ እጅግ ብዙ ነውና በጣም አድርጌ አመሰግንሀለሁ
ክብርና ምስጋና አምልኮና ውዳሴ ለአንተ ለሀያሉ ሰማይና ምድርን ለፈጠርከው ይሁን አሜን
የፈጣሪ በርከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
═════════❁✿❁ ═════════
1.3K viewsmelat..., 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:38:59 ጦርነትን ማስቀረት!
--------------------------
ከልምድ የተቀመረ ድንቅ ንግግር ነው ።
"የጥሩ ስለላ ትልቁ ጥቅም ጦርነትን ማሸነፍ ሳይሆን ውጊያን ማስቀረት ነው " ቴኔት የአሜሪካው የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ሲሆኑ በ2004 የኢራቁን ጦርነት " ሙሉ በሙሉ ተሳስተናል " ካሉ በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰው ለጦርነት የፈሰሰውን ትሪሊዮን ዶላርና የሚሊዮን ዜጎችን እልቂት ባሰቡ ጊዜ ይህን ወርቃማ ዓረፍተ ነገር ተናገሩ ።
------
ጦርነት እጅግም አስቀያሚ የሰው ልጅ የድንቁርናና የክፋት መገለጫ ነው ። ከጦርነት ማንም ምንም አያተርፍም ። ሚሊየኖችን እንደቀልድ የሚቀጥፍ ፣ ሕጻናትን ያላሳዳጊ ፣ አዛዎንትን ያለ ጧሪ የሚያስቀር ፣ ግዙፍ ከተማን ወደ ምድረ በዳነት የሚቀይር አንዲትን ሃገር ወደ ኋላ የሚጎትት የደደቦች ጨዋታ ነው ። ጦርነትስ ካለ ሰውን ቀፍድዶ ከያዘው ከተፈጥሮ ህጎች ጋር ነበር ....
ምድራችን እኮ እጅግ ሰቅጣጭ ፣ አስቀያሚና ዘግናኝ የጦርነቶች እልቂትን አስተናግዳለች ። ለምሳሌ ያህል ከክርስቶስ ልደት በፊት ፐርሺያውያን ፣ግሪካውያን ከሌሎች ግዛቶች ጋር ያካሄዱትን አስቀያሚ ጦርነት ትተን ከዚያ ወዲህ ታላላቅ እልቂቶችን ብንመለከት ።
-------
ለምሳሌ ያህል
--- ከ264 -146 B C ሮምና ካርቴጅ ባካሄዱት ጦርነት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አልቋል።
--- ዊ ፣ሹ እና ው የተባሉ ጎሳዎች ባደረጉት ጦርነት ወደ 38 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል ። አይገርምም !
--- በቻይናና በእስልምና ሃገሮች መካከል በተደረገ ጦርነት ወደ 22 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል ።የሃይማኖት ጦርነት በሉት ።
--- በሞንጎልና በኢራሽን ግዛት መካከል በተደረገ ጦርነት ወደ 34.6 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል ። ሚሊዮኖች እያልኩ ነው
---በስፔንና በሜክሲኮ ፣ በፔሩና በሚያ ግዛቶች በተደረገ መራራ ጦርነት ወደ 34 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል።
---በኘሮቴስታንትና በካቶሊክ ጦርነት ወደ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ።
--- በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዘረኝነት ጦርነት ወደ 1.7 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ።
------------
---በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወደ 24 ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል
--- በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወደ 69 ሚሊዮን ሕዝብ ወደ አፈርነት ተቀይሯል ።
--- ከ1950-1953 ዓ.ም በሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ ጦርነት ከ3 ሚሊዮን እስከ 5 ሚሊዮን ህዝብአልቋል ።
--- በሁለቱ ቬትናሞች ጦርነት እስከ 1.7ሚሊዮን ህዝብ ሞቷል ።
---- በባንግላዲሽና በፓኪስታን በ1971 ዓ.ም በተደረገ ጦርነት እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል ።
--- በሰሜንና ደቡብ ሱዳን በተደረገ ጦርነት እስከ 1.4 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል
ጦርነት ሚሊዮኖችን ወደ አለመኖር ከመቀየሩም በላይ የአንዲትን ሃገር ትውልድ እድል በዜሮ ያባዛል ።
---------
እኔ የተደራጀ የጦር መሣሪያና የሰለጠነ ወታደር አለኝ እያሉ የጦርነት አታሞ መምታት ጅልነት ነው ። የተደራጀ ሃይል ስላለህ አሸናፊ አትሆንም.... ጀግንነትስ ካለ ጦርሜዳ አንድም ሰው ሳይሞት መማረክ ስትችል ነው ።ሰው እያደገ ሲሄድ ጦርነቱንም አየቀየረ ይሄዳል ።
ኢትዮጵያችን ከራሷም ሆነ ከአለም አቀፉ ቀፋፋ ታሪክ መማር ካልቻለች በርግጥም ለሚመጣውም ትውልድ የዓለም ጭራነትን ታወርሳለች።
1.5K viewsmelat..., 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 00:52:30
1.6K viewsmelat..., 21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 00:52:10 Pictures speak louder than words #
Look at your self r u member of this generation who uses social media as pill
Hell,no...look at my post and share me ur ideas they got deep meaning for real
1.6K viewsmelat..., 21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:44:22 የትግርኛ ዘፈኖች ወደ አማርኛ ይተርጎምላችሁ??
እስኪ ቻናሉን እዩት እና comment ጀባ በሉኝ

https://youtube.com/channel/UCXU-D60aE-Yxem4bIZk3_TQ
1.7K viewsmelat..., 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 13:52:34 እናና

እረኛ ፥ እሆናለሁ ፣
በግ ፥ እጠብቃለሁ ፣
ብለሽ ፥ እንዳልነበር ፣
በግ ፥ አበቃሽ ላፈር ?
እንዳብዬ ፥ አስተዋይ ፣
መቼም ፥ አይኔ ባያይ ፣
ፍቅር፥ ሲናፍቀን ፣
እንባ እንዴት፥ አያንቀን ?
ዘመን ቢጎል ካምናው ፥ ዘንድሮ ቢከፋም ፣
ሐገር ብትመነምን ፥ ደግሰው አይጠፋም ፣
ነብስ ንጹህ ስትሆን ፥ ትዘራለች ፍቅር ፣
እንኳን ደጉ ቀርቶ ፥ ክፉም ይላል ይቅር ፣
ቸርነት እምዬ ፥ እናንዬ አማራ ፣
መስለው እዬታዮኝ ፥ እምባዬ እንዴት ያብራ ፣
ጥጋቡ ይሉት በግ ፥ ወግቶኛል እያለች ፣
በባረቀ ሃሳብ ፥ ያች እንቡጥ ተቀጨች ፣
ባይለው ነው እንጂ ፥ ትረፊ ባይላት ፣
በጉ ወንፈል ያውቃል ፥ እንኳንስ ሊገላት ፣
ቀልብ የታጣ ጊዜ ፥ ሀገር ይታመማል ፣
የባረቀ እያለ ፥ እንዴት ቀንድ ይታማል ?
ወግ ጥሰው ቢንቋት ፥ አልፋለች ግዴለም ፣
ጫንቃዋ ያዘለው ፥ ጅራፍ ብቻ አይደለም ፣
እንዳረገው ፍቅር ፥ አብነትን ያ ደም ፣
ምናለ እውን ሆኖ ፥ ለሐገር ቢደገም !

እናና
ዳን አበባው ንጋቱ
ነሐሴ 2014 ዓ.ም
2.7K viewsmelat..., 10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:13:55
የመዝጊያ መልዕክት ከእረኛየ!!!
2.1K viewsYibiopiA, 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:13:55 እረኛዬን ያየ
2.0K viewsYibiopiA, 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:20:09 ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡

ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን።

በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።

በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።

አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

አስተውሉ
በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!

መልካም ምሽት
2.5K viewsmelat..., 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ