#ምንም__የለኝም_ደሃ_ነኝ_አትበሉ ! ፦አንብቡት አንድ ደሃ ወደ አንድ ገዳም ሄዶ በዚያ ያገኛቸውን መነኩሴ አባት ለምን በጣም ደሃ ሆንኩ ብሎ ? ጠየቃቸው ። እሳቸውም የምትሰጠው ብዙ አለህ እኮ ግን አላወቅከውምን ? ብለው በጥያቄ መለሱለት ። ደሃውም የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም አላቸው ። እኚህ አባትም ከማንም የማያንስ የምትሰጠው ብዙ ነገር አለህ ተመልከት ፦ #ፊትህ ፦ ይስቃል ፥ ይደሰታል ለደስተኞች ፈገግታህን ትሰጣለህ ታካፍላለህ! #አፍህ ፦ ውብ የሆኑ ቃላትን ትናገርበታለህ ፥ ታመሰግንበታለህ ፥ ሰዎችን ታበረታታለህ ፥ ትመክራለህ ፥ ታፅናናበታለህ!! #ልብህ ፦ ለመልካምነት ፥ ለእውነትናና ለትህትናን ልብህ ክፍት ነው! #ዓይንህ ፦ ዓይንህ ጎስቋላና ችግረኞችን በፍቅርና በደግነት ትመለከታለች!! በሀዘን ለተዋጠው ዕንባን ትሰጣለች! #ሰውነትህ ፦ አቅም ያነሳቸውንና ጉልበት የሌላቸውን ታግዛቸዋለች ። ተመልከት ይሄን ሁሉ መስጠት ከቻልክ አንተ ደሃ አይደለህም..!! #ተወዳጆች ያለንን ብናውቅ ፈጣሪ ያስቀረብን አንዳች የለም ከሁሉም በላይ አንድያ ልጁን ሰጥቷል ከዚህ በላይ ደግነት የለም!! ስለዚህ እናንተ ደሃ አይደላችሁም ፈጣሪ ያላችሁ ባለጠጎች እንጂ! ፨ እውነት ነው አምላኬ ሆይ ለኔ የሰጠህኝ እጅግ ብዙ ነውና በጣም አድርጌ አመሰግንሀለሁ ክብርና ምስጋና አምልኮና ውዳሴ ለአንተ ለሀያሉ ሰማይና ምድርን ለፈጠርከው ይሁን አሜን የፈጣሪ በርከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ═════════❁✿❁ ═════════ 1.3K viewsmelat..., 17:35