Get Mystery Box with random crypto!

​​#የመልካም_ወጣት_መገኛ Share በማድረግ ለመጥፋት የተዘጋጁ በጎችን ከመንጋው እንዳይለዩ ታደ | መሰንቆ ለኢትዮጵያ🇪🇹

​​#የመልካም_ወጣት_መገኛ

Share በማድረግ ለመጥፋት የተዘጋጁ በጎችን ከመንጋው እንዳይለዩ ታደጓቸው።
መልካም ወጣት ማለት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ወጥተህ መናፍቃን አዳራሽ መክተም አይደለም።

መልካም ወጣት ማለት ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ከአንገትህ ላይ በጥሶ መጣል አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ቅድስት ድንግል ማርያምን መካድ ማለት አይደለም።
መልካም ወጣት ማለት ለሰዎች ይታዩ ዘንድ በምድር ላይ ባለጠግነትንና ዝነኝነትን ማካበት አይደለም፥ በምድር ላይ ሁሉ የከንቱ ከንቱ ነው።

#ይልቁንስ መልካም ወጣት ማለት ወንጌል ነው፦
ወዳጄ ወንጌል ማለት በሽንገላ ከንፈር ኢየሱስ ያድናል ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት ክርስቶስን አምኛለውኝ ብሎ በግላዊ ግብር ለክርስቶስ ያለመታመንም ማለት አይደለም። ወንጌል ማለት መከራ መስቀልን መሸከም ነው። ወንጌል ማለት ክርስቶስ የተጓዘበትን የኩርንችት መንገድ በደስታ መራመድ ነው ። ወንጌል ማለት ለመሀተብህ ትሞታለህ ሲባል ከስጋው ይልቅ ነፍስን አስበልጦ ቀድሞ መሰለፍ ነው። ወንጌል ማለት ስለክርስቶስ ፍቅር ስጋህን እና ምኞትህን ገድለህ ለሞተልህ አምላክ መሰጠት ነው። ወንጌል ማለት ነፍስን መግደል በማይችሉት ፈርዖኖች ፊት በክብር ማሸብሸብ ነው ።

ወንጌል የምታወራው ልብ ወለድ ሳይሆን የምትላላክለት መወደድ ትዕዛዝ እንጅ። ወንጌል ማለት ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን ክብር ላይ ዕጣ ሲጣጣሉባት እንደ 44 ታቦት ብላቴናዎች ቀድሞ የመገኘት ጥሪ ነው። ወንጌል የምትታዘበው እና ከአውደምህረት ላይ የምትወረውረው የማትኖርበት ቃል አይደለም። የምታልፍበት የመከራ ኮረብታ እንጅ ።

ከእዚህ አማናዊ ወንጌል ከሆነው ህዝብ ተማር። በጣም ተማር።
ልጆቻችሁን ወንድም እኅቶቻችሁን "መልካም ወጣት አዳራሽ" የምትልኩ ኦርቶዶክሳውያን ጊዜያዊ መላ ፍለጋ ልጆቻችሁን ለዘለዓለማዊ ሞት አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ እንደሆነ ዕወቁ።
አዎ ልክ ነው ዘፋኙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ሰካራሙ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ሱሰኛው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው፥ አዎ ልክ ነው ተሳዳቢው፥ ተራጋሚው፥ ተደባዳቢው፥ አመጸኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቷ እና ሀይማኖቷ አጥብቀው ያወግዛሉ።

የአባ ዘጋስጫ ሀይማኖት ፥ የአባ ኤፍሬም ሀይማኖት ፥ የቅዱስ ያሬድ ሀይማኖት፥ የቅድስት አፎሚያ ሀይማኖት፥ የአቡነ ተክለ ሀይማኖት፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፥ አቡነ አረጋዊ ሀይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው፥ ትልቅ እምነት እና ከክርስቶስ ቀጥሎ በክርስቶስ መንገድ የሄዱ ቅዱሳን የተጠሩባት ሀይማኖት (1ቆሮ᎐11:1) እኔ ስጠራበት በመጥፎ ስራዬ ላፍር በሀይማኖቴ ግን ልኮራ ይገባል።

ይህ ሰበብ ሊሆነን አይገባም፥ እኔ መልካም ወጣት እንድሆን መናፍቅ መሆን በፍጹም አይጠበቅብኝም!!
ኦርቶዶክሳውያን ሰባክያነ ወንጌል፣ ማኅበረ ቅዱሳንና ሌሎች መንፈሳዊ ማኅበራት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት የመጠበቅ ኃላፊነትና አደራ ከጌታ የተሰጣችሁ ነውና ትውልዱን ከጥፋት ለመጠበቅ ምን መሥራት እንዳለባችሁ አስቡበት።

"ደግሞ ሁለተኛ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው።" (ዮሐ 21:16-17 )

@mesenqo_le_ethiopia