Get Mystery Box with random crypto!

#ሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥ | መሰንቆ ለኢትዮጵያ🇪🇹

#ሁሉም_ነገር_ለበጎ_ነው



አንድ ንጉስ ከአሽከሩ ጋር ለአደን ወደ ጫካ ያመራል። ዙርያውን ወጥመድ በማጥመድ ላይ ሳሉ አንደኛው ወጥመድ የንጉሱን እጅ ላይ አርፎ እጁን ያሳጠዋል። ንጉሱም በመጮህ ላይ ሳለ አሽከሩ የደማውን እጁን በጨርቅ እየጠቀለለ "ንጉስ ሆይ አይዞህ ለበጎ ነው ይለዋል" ንጉሱም እጅግ ይበሳጭና የእኔ እጅ መቆረጥን ለበጎ ነው ትላለህ ብሎ ያሳስረዋል።

ከብዙ ቀን ቆይታ በኋላ ንጉሱ ለብቻው ወደ አደን ሲሄድ ሰው ገድለው ለአማልክቶቻቸው መስዋዕት የሚያቀርቡ ሽፍቶች ይይዙታል። ሊሰውትም ሲሉ ንጉሱ እጁ የተቆረጠ ነውና በባህላቸውም መሠረት አካለ ጎዶሎ ሰው ለመስዋዕት አይቀርብምና ይተውታል።

ንጉሱም ወዳሰረው አሽከር ሄዶ "ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ያልከው እውነት ነበር ብሎ ታሪኩን ያጫውተዋል። ባደረገውም ተጸጽቶ "ይቅርታ አድርግልኝ አንተን ማሰሬ ልክ አደለም" ይለዋል

አሽከሩም "ንጉስ ሆይ አንተም እኔን ማሰርህ ለበጎ ነው ባታስረኝ ኖሮ ካንተ ጋር አብሬ እሄድ ነበር። አንተን ሲለቁህ እኔን ደግሞ ሙሉ አካል ነው ብለው ይሰዉኝ ነበር" አለው።


" እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28)

ብናገኝ፣ ብናጣ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ከማማረራችን በፊት የእግዚአብሔርን በጎ ምላሽ እንጠብቅ። እግዚአብሔር ቢዘገይም የሚቀድመው የለም ከችግራችን በላይ እግዚአብሔር ይበልጣል።

@mesenqo_le_ethiopia