Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ News🎤🎤📺📻

የቴሌግራም ቻናል አርማ merjanews — መረጃ News🎤🎤📺📻
የቴሌግራም ቻናል አርማ merjanews — መረጃ News🎤🎤📺📻
የሰርጥ አድራሻ: @merjanews
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስና ፈጣን መረጃዎችን ከ ዜናዎች ጋር እናቀርባለን
ለሀሳብ አስተያየት፦ https://t.me/Babafiker

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-11 11:56:47 በአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ በኢሰመኮ የተደረገው ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል!

“በቀዳሚነት በጦርነቱ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች እና ኃይሎች በአባላቶቻቸው እና አመራሮቻቸው ለተፈጸሙ ከባድ የመብት ጥሰቶች ኃላፊነት መውሰድ እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ግዴታቸውን መወጣት ለፍትሕ፣ ለእውነት፣ ለተጎጂዎችና ለተጎጂዎች ቤተሰቦች የማይታለፍ እርምጃ መሆኑን በድጋሚ ሊታወስ ይገባል"--- ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር

ከሪፖርቱ በጥቂቱ: "ኢሰመኮ ምርመራ ባደረገባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች በተለይም እና በዋነኝነት በትግራይ ኃይሎች ቢያንስ 346 ሲቪል ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ተገድለዋል። በተመሳሳይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸው ስፍራዎች በነበሩ የመንግሥት አስተዳደር ኃላፊዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ ያሏቸው ሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ግድያን ፈጽመዋል። በሌላ በኩል የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሺያዎችም፤ የትግራይ ኃይሎች እና የኦነግ ሸኔ አባላት ወይም ደጋፊ ናቸው በሚል የጠረጠሯቸው ሰዎች ላይ ሕገወጥና ከዳኝነት ውጪ የሆኑ ግድያዎችን ፈጽመዋል፣ የአካል ጉዳትም አድርሰዋል። "

ሙሉ ሪፖርቱን ለማንበብ: https://ehrc.org/am/%E1%8A%A0%E1%8D%8B%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8E%E1%89%BD%E1%8D%A1-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8B%A8%E1%8A%A0/

@merjanews
138 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 09:37:08 የሳዑዲ እና የኢምሬትስ መሪዎች ከባይደን ጋር ለመነጋገር የቀረበውን ጥሪ ውድቅ አደረጉ

ዋይት ሀውስ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣በሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መሪዎች መካከል ውይይት እንዲደረግ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ሳይሳካለት መቅረቱን ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል። አሜሪካ ለዩክሬን አለም አቀፍ ድጋፍን ለመገንባት እና የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት ወደ ሪያድ እና አቡዳቢ ጥሪ ብታደርግም ምላሽ አላገኘችም።

የመካከለኛው ምስራቅ እና የአሜሪካ ባለስልጣናት ለጋዜጣው እንደተናገሩት የሳውዲው አልጋ ወራሽ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ባለፉት ሳምንታት ከባይደን ጋር ለመነጋገር የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።የሳውዲ ባለስልጣናት እንደገለፁት ሳውዲ በየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ለምታደርገው ጣልቃገብነት ፣ለኒውክሌር መርሃ ግብሯ እና በአሜሪካ ውስጥ ልዑል መሀመድ ህጋዊ ያለመከሰስ መብት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ ብለዋል።

ልዑል በ2018 የዋሽንግተን ፖስት አምደኛ እና የሳዑዲ መንግስት ተቺውን ጀማል ኻሾጊን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ ክስ ቀርቦባቸዋል። ባይደን በፕሬዝዳንትነት የምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ሳዑዲ አረቢያ በሰብአዊ መብት ረገጣ ድርጊቷ “ዋጋ እንድትከፍል” ለማድረግ ቃል በመግባት መግባታቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በቅርቡ በኢራን የሚደገፉ የሁቲ ታጣቂዎች በየመን በሚገኙት በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ሳውዲ አረቢያ ጦር ላይ ላደረሱት የሚሳኤል ጥቃት የአሜሪካ ምላሽ  አጥጋቢ አይደለም በሚል የሳዑዲ ስጋት በመጋራት የአሜሪካን የእንወያይ ጥሪ ውድቅ አድርጋለች።

@merjanews
109 views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 09:24:45 በከባድ ራስ ምታት ለ20 ዓመታት ያህል ሲሰቃይ የነበረዉ ወጣት በልጅነቱ መናገር የፈራዉ ጥይት በራስ ቅሉ ዉስጥ እንደነበር ተነገረ

ዢኦ ቼን የተባለዉ የ28 አመቱ ቻይናዊዉ ወጣት በራስ ምታት ለዓመታት ሲሰቃይ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ህመሙ እየጠነከሩ ይመጣል። ቼን ህመሙ የተከሰተው በሳምንቱ ቀናት በቂ እንቅልፍ በማጣቴ ነው ብሎ አስቦ የነበረ ቢሆንም ብዙ መተኛት መፍትሄ አላመጣለትም፡፡

በሼንዘን ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደረገለት የኤምአርአይ ምርመራ በዢኦ ቼን ራስ ቅል በግራ በኩል አንድ እንግዳ ነገር ይገኛል። በተደረገዉ ምርመራ ጥይት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ስለ ሁኔታዉ ያስታዉስ እንደሆነ ለቼን በቀረበለት ጥያቄ መሰረት የ8 አመት ልጅ እያለው እኔ እና ወንድሜ በቤት ውስጥ በሽጉጥ ስንጫወት ድንገት ተተኩሶ በጥይት መመታቱን ተናግሯል።

እኔ እና ወንድሜ በወላጆቻችን እንዳንሰደብ ፈርተን ነበር፤ ብዙ ደም ስላልፈሰሰኝና ቁስሉም በፀጉሬ ተሸፍኖ ስለነበር ቤተሰቦቼ ሳያዩት እኔ በጊዜ ሂደት ረሳሁት ሲል ተናግሯል፡፡በተደረገለት ህክምና ጥይቱ የወጣ ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡

@merjanews
141 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 20:32:51 ከጋና ወደ አሜሪካ ይበር በነበረ አውሮፕላን ዉስጥ አንዲት ነፍሰጡር ልጇን በሰላም ተገላገለች

ከጋና ወደ አሜሪካ ይበር በነበረ አዉሮፕላን ዉስጥ በድንገት አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት በሰላም መገላገሏን ተከትሎ በዙሪያዋ ባሉት ሰዎች ከፍተኛ ድንጋጤ እና ከዛም ጭብጨባ እንደተከተለ ተነግሯል፡፡ስሟ ያልተገለጸዉ ይህችዉ እናት በበረራ ላይ ወንድ ልጅ ያለጊዜው የታቀፈች ሲሆን ዋሽንግተን ዲሲ አዉሮፕላኑ ሲያርፉ ተጨማሪ የህክምና አገልግሎት አግኝታለች፡፡

በአዉሮፕላን ዉስጥ የጤና ባለሙያ ካለ በሚል የቀረበዉን የእርዳታ ጥያቄን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ በልምምድ ላይ የነበረዉ ጋናዊ ዶክተር እና መንገደኛ የአዉሮፕላኑን የቢዝነስ ክፍል ወደ ጊዜያዊ ማዋለጃ በመቀየር ስራዉን ይጀምራል፡፡ዶ/ር ስቴፈን አንሳህ-አዶ በአዉሮፕላን ዉስጥ ስለነበረዉ ሀኔታ ሲያስረዳ እኔ እና የበረራ መስተንግዶ ሰራተኞች ጋር በመሆን እናት ቆንጆ ወንድ ልጇን እንድትታቀፍ በቅታለች ሲል ተናግሯል፡፡

ከአክራ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በነበረዉ በረራ ላይ የነበረችዉ መንገደኛ ምጥዋ ለ45 ደቂቃ ያህል እንደፈጀ ተነግሯል።

@merjanews
112 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 17:05:46 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ !

ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በሀምሌ 11ቀን 2013 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፍርድ ቤት ቀርበው እ.ኤ. አ በ2014 ዓ/ም በተደረገ በዝቅተኛ ወለድ ስምምነት ኢትዮጲያ ከፖላንድ መንግስት ባገኘችው 50 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እዛው ፖላንድ ሀገር ለሚገኙ የዕርሻ መሳሪያ መለዋወጪያ ኩባንያዎች መከፈሉን እና ገንዘቡ ወደ ሀገር ውስጥ አለመምጣቱን በማብራራት የመከላከያ የምስክርነት ቃላቸው ተሰምቶ ነበር።

በዚሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት የቀድሞ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።

ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።

@merjanews
112 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 21:29:45
#እንድታውቁት

ነገ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@merjanews
141 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 18:37:41 የሰሞኑ ጉንፋን ጉዳይ!

ሰሞኑን ወረርሽ በሚመስል መልኩ በርካቶች በዚህ ህመም ተይዘዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልም ለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ጠቃሚ መረጃን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይዞ ወጥቷል።የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡

-ብርድ ብርድ ማለት
-የመገጣጠሚያ ህመም
-የጀርባ ህመም
-የጡንቻ ህመም
-ምግብ ፍላጎት መቀነስ
-ኃይለኛ ራስ ምታት
-ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል?

ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው ::ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው:: ስለዚህ ምን እናድርግ?

የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
-ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
-የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
-ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
-ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
-መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

-ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
-ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
-ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
-ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
-የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
-ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
-ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል ::

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

-ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
-ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
-ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
-በቂ እረፍት ማድረግ
-የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ

እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

[በዶ/ር ፋሲል መንበረ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም]

@merjanews
156 views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-10 12:26:19
143 views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-10 12:09:45
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።

@merjanews
148 views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 12:48:17 ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላውን ሙሉ በሙሉ አነሳ።

ለባለፉት አራት ወራት ተግባራዊ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ አስታወቀ።

ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ክልከላው የተጣለው "የኢኮኖሚ አሻጥርን" ለመከላከል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተግባራዊ ተድርጎ የነበረው በትይዩ እና በህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ ነበር።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@merjanews
139 views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ