Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ከዛሬ መጋቢት 1/2015 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ማለዳ ማለዳ | መረጃ ቲቪ🇪🇹

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ከዛሬ መጋቢት 1/2015 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ማለዳ ማለዳ ካሉኝ ጓደኞቼ መካከል 5ሺ ጓደኞቼ ስሙን ጽፈው እግዚአብሔር ይመስገን ካላሉኝ በቀር ወደ ሌላ አጀንዳ አልገባም ማለቴ ይታወሳል። የአመስጋኙን ቁጥርም ከ3ሺ በቀጥታ ወደ 5ሺ ከፍ ያደረግኩት 3ሺው ስላላዋጣኝ ነበር። እያየን ቀስ እያልኩ እጨምራለሁ ብዬ እንጂ ከቦታውም ስለማይመጣ 5ሺውም እንደማያዋጣኝ ራሳችሁ ምስክር ናችሁ።

"…ሰሞኑን የአመስጋኙ ቁጥር እየበዛ በመሄዱ እግዚአብሔር የሚለውን ስም ላለማየት ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እኔ ሳላባርራቸው በራሳቸው ፈቃድ ፔጄን ለቀው ውልቅ ስላሉ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ግብይቴማ ብዙዎች ደንግጠው ይጠፋሉ ብዬም አስቤ ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው።

• በ3 ሰዓታት ውስጥ 30ሺ ሰዎች አይተውኝ።
• በ3 ሰዓታት ውስጥ 5ሺ ሰዎች አመስግነዋል።
• መስመር ላይ 12,437 ሰዎች የነበሩ ሲሆን ለክብራቸው፣ ለስማቸው፣ ለማእረጋቸው፣ ለሥልጣናቸው፣ ለዝናቸው፣ ለሃብታቸው ሳይጨነቁ በደስታ እግዚአብሔር ይመስገን ብለው በዓለሙ ሁሉ ፊት የእግዚአብሔርን ስም ጠርተው ያመሰገኑት ግን በቁጥር 5,256 ጓደኞቼ ብቻ ናቸው። ይሄ የአመስጋኝ ቁጥር በአሜሪካና ካናዳ እንቅልፍ ላይ ያሉትን አይጨምርም። እነሱም ገና ሲነጋላቸው ስሙን ያመሰግናሉና።

"…ለአንዳንዶች ሲያዩት ሞኝነት፣ ቂልነት ቢመስልም ለእኔና ለአመስጋኝ ጓደኞቼ ግን በዚህ በሰይጣናዊ አጋንንታዊና ዲያብሎስ በነገሠበት ዓለም የእግዚአብሔርን ስም ጮኽ ብሎ ጠርቶ ማመስገን እንደ ቀላል እንደተራም ነገር አንቆጥረውም። መባረክ መመረጥም ነው እንጂ። 5ሺ ሰው ሳይወድ በግዱ እያፋሸከ፣ እየተንጠራራ እየተነጫነጨም ቢሆን ወይም ደስስ እያለው ፈጣሪን እንዲያመሰግን ማስገደድስ ቀላል ይመስላችኋል እንዴ? ቴርሞ ሜትሪዻ በር…

•ድርጅቱ…!