Get Mystery Box with random crypto!

#Addis_Ababa_Education_Bureau የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲ | 43 All University

#Addis_Ababa_Education_Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀው የሬዲዮ ትምህርት የስክሪፕት ቀረጻን እያከናወነ ነው።

ቀረጻው በቅርቡ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ሥራ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 900 ስክሪፕቶች ተዘጋጅተው በቀረጻ ላይ እንደሚገኙ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክተር በለጠ ንጉሴ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ለ2015 የትምህርት ዘመን አንደኛ መንፈቅ ዓመት የሚያገለግሉ 450 የሚሆኑ ስክሪፕቶች ቀረጻ ላይ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

75 የሬዲዮ ትምህርት ቀረጻ ፕሮግራም አዘጋጆች፣ ቴክኒሺያኖች እና ተማሪዎች በቀረጻው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ቢሮው ገልጿል።

አዲሱ የአንደኛ ደረጃ ስርዓተ ትምህርት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) በ2014 ዓ.ም የሙከራ ትግበራ ተካሂዶ በ2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይታወቃል።

Share&forward
Join

@merejamnch
@merejamnch

cross promotion መስራት የምትፈልጉ

Contact with me


@Gashtiman25