Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ አምና ይኼኔ ከመቀሌ እስከ ወልደያ፣ ከነፋስ መዉጪያ እስከ ቆቦ ጦርነት ላይ ነበረች።ከመስ | Ethio 360 / Mereja.com / ኢትዮ

ኢትዮጵያ አምና ይኼኔ ከመቀሌ እስከ ወልደያ፣ ከነፋስ መዉጪያ እስከ ቆቦ ጦርነት ላይ ነበረች።ከመስከረም እስከ ሕዳር ደብረ ብርሐን ደጃፍ የደረሰዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት (ሕወሓት) ጦር ጥቃት በፌደራል መንግስት፣ በአማራና በአፋር ክልሎች ኃይላት አፀፋ ጥቃት ከተቀለበሰ በኋላ ግን ተፋላሚ ኃይላት ለሰብአዊነት ያሉትን ተኩስ አቁም ሲያዉጁ የሰላም ጭላንጭል የፈነጠቀ መስሎ ነበር።የአዲስ አበባና የመቀሌ ገዢዎች ከዉጊያዉ ቀነስ፣ አሸባሪና ፋሺስት ከሚል ፕሮፓጋንዳቸዉ ቆጠብ ብለዉ የድርድር ዝግጅት፣ የተደራዳሪዎች ሹመት፣የአደራዳሪዎች ማንነትን እያነሱ ሲጥሉ ለ30 ዘመናትt መከራ ሲግቱት የኖሩት ሕዝባቸዉ በርግጥ አምኗቸዉ ነበር። ኢትዮጵያ፤ የፖለቲካ ባሕል አልባ-ፖለቲከኞች ሐገር !!! የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ባሕልን አዳብረዉ ይሆን?

https://mereja.com/amharic/v2/750903