Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​ °••በዝናብ ቅጠሪኝ••° አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበ | 💞መንታ ልቦች💞

​​​​​​​​ °••በዝናብ ቅጠሪኝ••°

አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ
ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ
ውዴ፦
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ
ሳለቅስ እንዳታዪኝ
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።

━━━━⸙መንታ ልቦች⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃


       
,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

@menta_liboch12,,,,@menta_liboch12
━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━