Get Mystery Box with random crypto!

ያበደው ፍቅሬ ክፍል ሀያ የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ | 💞መንታ ልቦች💞

ያበደው ፍቅሬ


ክፍል ሀያ

የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ ያለውን የሚያስፋራ አውሬ አውጥቶት ሊበላችሁ እየገሰገሰ ሲመጣ ምን ይሰማችኋል። ትሸሻላችሁ ወይስ ቆማችሁ ትበላላችሁ። እኔ ግን ብዙ ነገሬ እስከሚያልቅ ቆሜ ነበር የተበላሁት

የልቤ ንጉስ ብዬ የፍቅር ማማ ላይ የሰቀልኩት ሰው ልክ የዛን ቀን ትክክለኛ ማንነቱን አየሁት። ማንኛውም ሰው ሲናደድ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሱ ግን ከዛ የተለየ ነበር። ነገሮችን ለመስማትም ለመረዳትም ፈቃደኛ አልነበረም ያነበበው ደብዳቤ ሳይቀር ቢኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀልኝ እየነገረው እሱ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ፍቅረኛሞች ነበራችሁ ብሎ ደመደመ።

።።። ።።። ።።።።

"ጯ ጯ" ይህ በማፈቅረው ሰው የተመታሁት የጥፊ ድምፅ ነው። የቦክስን ድምፅ ደግሞ በቃል መግለፅ ይከብዳል እንጂ እኔን እንደመታኝ ቢኒ ዘሎ ተነስቶ ያቀመሰውን ቦክስ ከዛም አንዴ ቢኒ አንዲ ዮኒ ገላጋይ እስኪመጣ የተደባደቡትን በቃል እገልፅላችሁ ነበር።

ከድብድቡ በኋላ ሁለቱንም ሰው ይዟቸው

"አንተ ውሻ አላፈቅራትም ብለህ ያጣበስከኝ ፍቅረኛህን ነበር አይደል?(ደም ያዘለ ምራቅ ከአፉ እየተፋ) አትረባም ወንድ አይደለህም እሺ... ቀሚስ ልበስ"

ቢኒ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው ከድብድቡ በኋላ እሱንም ሰዎች ቢይዙትም ለመወራጨትም ሆነ ለመሳደብ አልሞከረም የንዴት ትንፋሽ እየተነፈሰ ዝምም ብሎ ዳር ላይ ቆሜ አንዴ እሱን አንዴ ዮኒን እያፈራረቅሁ የማየውን እኔን ያየኛል

"እባካችሁ ልቀቁኝ ምንም አይፈጠርም እሷን ግን ሊጎዳት ይችላል። ሚስቱ ናት ግን እባካችሁ እንዳይጎዳት አድርጉ" አወራሩ ያሳዝን ነበር። ለቀቁትና ወደኔ መጣ

"ይሄ ውሻ ሚስቴ አጠገብ እንዳይደርስ እንዳትነካት አትጠጋት"
ብዙም ሳይቀርበኝ ቆመ

"ከሳምንት በኋላ እበራለሁ እስከዛ ግን ችግር ካለ ደውይልኝ እዛ ስሄድ ደግሞ እኔ እደውልልሻለሁ" አለኝና መልሴን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ከመናፈሻው ወጣ

።።።። ።።።።። ።።።። ።። ።።።
ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ። ዮኒ ደግሞ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ ይለፈልፋል

"ንገሪኝ እስኪ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?" መልሴን ሳይጠብቅ ደግሞ

"የትናዬት ልክ ነበረች አይደል" ለመናገር አፌን እንደከፈትኩ

"ዝምምም በይ ምንም አትናገሪ ባትነግሪኝም አውቄዋለሁ። ግን ከመች ጀምሮ ነው ፍቅረኛ የሆናችሁት አንደኛ አመት እያለሽ"

"ኧረ እኔ ከቢኒ ጋር"
" ዝምም በይ አትንገሪኝ መገመት አይከብደኝም" ለመናገር መሞከሬን አቆምኩና ንዴቱ ሲበርድለት እነግረዋለሁ ብዬ አሰብኩ ግን በፍፁም ያሰብኩት አልሆነም። በውስጡ ያመነበትን የመከዳት፣ የመቀደምና የመሸወድ ስሜት ከውስጡ እንዳስወግድለት እድል ሊሰጠኝ አልቻለም። በራሱ ጭንቃላት ታሪክ ፈጠረና በፈጠረው ታሪክ ደግሞ አመነበት። ሩት ከቢኒያም ጋር የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው ፍቅር የጀመረችው። እኔ ላይ ተመካክረው ነው የተጫወቱብኝ ይህን እና ሌሎች ነገሮችን በጭንቅላቱ ውስጥ ሞላቸው የሚያውቀውን እውነት ሳይቀር ካደ። ከዛ በኋላማ ያሳለፍኩትን እንዴት ልገልፀው እችላለሁ በአጠቃላይ ህይወቴ ሲኦል ሆነ።

ተመስገን ይህን ሰሞን በፍቅር የተሞላ ጊዜ አሳለፍን ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላ ታሪክ ይፈጠራል። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ለሱ ያለኝ ፍቅር እንደድሮው ነበር። ትቼው እንኳን ለመሄድ አቅም አልነበረኝም። በእርግጥ ትቼው ብሄድ ከሱ የተሻለ ደሞዝ ያለኝ ራሴንም ሆነ ልጄን እና እናቴን ቀጥ አድርጌ ማስተዳደር የምችል ሰው ነበርኩ። ግን አፈቅረዋለሁ አንድ ቀን እውነቱን ለመረዳት እንደሚሞክርም አምናለሁ። እምነቴ ከምንም በላይ ለሱ ያለኝ ፍቅር በደልን ችዬ እንድኖር አደረገኝ።

።።።። ።።።። ።። ።።።።።።

ይህ ከተፈጠረ ከአመት በኋላ እናቴ በፀና ታማ ሆስፒታል ገባች። እኔ የምሰራበት ሆስፒታል ነበር። እንደማትተርፍ እያወቅሁ ብዙ ጣርኩ ግን ልመልሳት አልቻልኩም። እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ....


ይቀጥላል....
@fun_ethio1
@menta_liboch12
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት