Get Mystery Box with random crypto!

የአይኔ እንግዳ በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረተ ክፍል 19 ከመተኛ | 💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

የአይኔ እንግዳ


በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረተ


ክፍል 19

ከመተኛቴ በፊት ያዘልኩት ስሜት እና በእንቅልፍ አለም ያለውን ሰላም አወዳደርኩ ኡፍፍፍ ባልነቃሁ። ህመሜ ተነሳ ደሞ ለሊቱ ይነጋልኝ ይሆን።


በጭንቀት ልፈነዳ ደረስኩ መተንፈስ አቃተኝ በድጋሚ አይኖቼ በእንባ ተሞሉ
የዛንቀን ስለ ነባ የነገሩኝ ነገሮችን ትዝእያለኝ መጣ ንግግራቸው ሳስታውስ በዛውም ስለኔ ጥንካሬ የነገሩኝን አስታወስኩ ወዲያውኑ ከአይኔ የሚፈሰውን እንባዬን አበስኩኝ ኑሀ ለማን ብለሽ ነው ምታለቅሽው ለዚ ለማይረባ ልጅ ብለሽ ነው ምታለቅሺው ኧረ ወደዛ የሚያለቅስ ያልቅስለት ካሁን በኋላ ከደገመ እኔን አያድርገኝ ከዛሬ በኋላ አይኔ እንዳያየው የእሱነገር በቃኝ።



ኡኡኡኡኡኡኡኡፍ ተመስገን አምላኬ አሁን ወደራሴ ተመለስኩ። ለካ ጥሩ ወይም መጥፎ የሚባል ነገር የለም እራሳችን የምንመለከትበትመነፅር እና ምልከታችን ነው ነገሮችን ጥሩ ወይም መጥፎ የምናደርገው ።

ከመተኛቴ በፊት ያዘልኩት ስሜት እና በእንቅልፍ አለም ያለውን ሰላም አወዳደርኩ ኡፍፍፍ ባልነቃሁ። ህመሜ ተነሳ ደሞ ለሊቱ ይነጋልኝ ይሆን።ነባዬ ትዝይለኝ ጀመር እኔ እኳ ለሱ ያለኝ ቦት እኳ ምንያክል እንደሆነ ለመግለፅ ያዳግተኛል።



ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡፍ ደሞ አሁንም አይኖቼ በእንባተሞሉ የምወድለትን አይኖቹን እያስታወስኩኝ ስቅስቅ ብዬ አነባው የኔ ነባ ነባ የኔ የኔ ነባ ነባ የኔ እያልኩ አለቀስኩለት።ለኔይሄ ይገባኛል ነባ የምርጨካኝነክ ጨካኝነክ ነባ እያልኩ እሱ የሚያየኝ ይመስል ተንሰኩለት።



ወዲያው ስለነባ የነገሩኝ ታወሰኝ ግን ባሁኑ በይበልጥ እያስታወሰኝ ያለው ግን ስለሱ መጥፎነት ሳይሆን ስለራሴ የነገሩኝ እንደሚተማመኑብኝ እና ጠንካራ እንደሆንኩ ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲ ደካማ የሆንሽው አንቺ እኮ ኑሀሚን ነሽ እንዲ በቀላሉ እጅ አትሰጪም ለዚ ለተራ ነገርማስ እንደዚ አትሁኝ ተራነገርማስ አይደለም የክብር ነገር ነው አልኩኝ ለራሴ ።



አሁን በጭለማ ውስጥ የምደምቅበት ሰአት ደረሷላ ።የተፈጠረውን ነገር እዚጋር ትቼው ወደፊት ለመጓዚ ምንም እንዳልፈጠረ ለመሆን። ለራሴ ቃል ከገባው በኋላ ተረጋጋው ወደራሴ ተመለስኩኝ።


ክፍል 20 ይቀጥላል

የነባን አይኑን ማየትም ሆነ ድምፁን ደግሜ ላለመስማት ወሰንኩኝ ።


ኑለሚን

•═••• መንታ ልቦች •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
@MENBOCH