Get Mystery Box with random crypto!

የአይኔ እንግዳ በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይየተመሰረተ ክፍል 20 የነባ | 💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

የአይኔ እንግዳ


በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይየተመሰረተ


ክፍል 20



የነባን አይኑን ማየትም ሆነ ድምፁን ደግሜ ላለመስማት ወሰንኩኝ ።

ረፍት ተሰማኝ ከእንቅልፌ የነቃሁት ወደ 5ሰአት አካባቢ ነበር ጥሩ እንቅልፍ ስለተኝው ደስየሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው።

ሳምንቱን በእንደዚአይነት ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ሆኜ አሳለፍኩት። ዛሬ ቀኑ ሀሙስ ነው አይገርምም ነባን ካየሁት ሳምንት እኮ ሞላኝ ላለፉት ቀናቶች ቃል በገባሁት መሰረት ስለሱ ማሰብ እሱን ማየትም ሆነ ድምጽን መስማትን ሳላስብ ከነጭራሹ ከጭንቅላቴ ነባን አስወጥቼው በቃ ለዚህ ነበር ነባ ነባ ያልኩት ለነገሩ አይደለም መረሳት ሌለም ሌላም ነገር ይገባዋል ይሄ የማይረባ።


ቀኑን ሙሉ ደስበሚል ስሜት ውስጥ ሆኜ አሳለፍኩ ወደ 11ሰአት አካባቢ ተልኬ ከቤት ወጣው ከሳምንት በኋላ ውጩን አየሁት። ከሀሙስ በኋላ ወይም ነባን ለመጨረሻ ቀን ካገኘሁት በኋላ ከቤት ወጥቼ አላውቅም ምክንያቱም ከቤት ከወጣው ሰፈር ውስጥ አገኘዋለው ብዬ ስለፈራሁ።


የፈሩት ይደርሳል አይደል የሚባለው የተላኩበት ደርሼ ስመለስ ነባን ከ ጀማሪዎቹ ጋር አየሁት ከሩቁ ነበር የለየሁት እሱም አይቶኝ ስሐነበር እርምጃውን ገቶ ቀስእያለ እኔን መጠበቅ ጀመረ እንደ እኔ ደግሞ በጣም የሚራመድ ሰው የለም ያው ለመካበድ ሳይሆን በጣም ነው የምራመደው ለዛነበር እርምጃውን የገታልኝ እኔ ግን ልክ ሳየው አለአ በጣም ተበሳጨው ሄደሽ እነቂው እነቂው አኝ የዛን እለቱ ንዴቴ አገረሸብኝ።



ተናድጄ በፍጥነት ሄጄ ልንገረው አጠገብ ስጀርስ ቀና ብሎ ሲያየኝ አይን ሐአይን ተገጣጠምን ልክ አይኑን ሳየው ንዴቴ የት እንደገባ አላውቅም የድሮው ስሜቴ አገርሽቶብኝ ቁጭ ከዛ ጭራሽ ሰላም አልኩትና እግሬ አውጪኝ ወደ ቤቴ ።

ቤት እንደገባው ስለሱ አልጋላይ በደረቴ ተኝቼ በደስታ ማለም ጀመርኩኝ።እናንተዬዋ የኔስ ለጉድ ነው ያሁሉ ንዴቴ ቆይ የትገባ አላውቅም ብቻ ለጤና ያድርግልሽ በሉኝ።

የሄለን በርሔን የህልሜ ጓደኛ የሚለውን ዘፈን በቀስታ ከፍቼ እያዳመጥኩ ስለሱ ማሰቤን ቀጠልኩ አይገርምምግን እነደዛ ስሆን የነበርኩ ልጁ ገና ለገና አይኑን ስላየው ብቻ እንዲ የምሆንለት ደሞ ለዚህም ነው አዳኜም ገዳዬም የምለው።

አሁን ወደ ድሮዬ ተመልሻለው ነባን ወደ መናፈቅ ። ማክሰኞም ሮብም ሀሙስ አርብም ከቤት ሳልወጣ እሱ በማሰብ ብቻ አለፊ።ዛሬ ቅዳሜነው ኮሮና በጣም እየተስፋፋ ስለመጣ ማስክ ማድረግ ግዴታ እንደሆነና ያላደረገሰው እንዲታሰር ትእዛዝ ወቶ ነበር። እኔ ደግሞ ማስክ መድረግ ስለሚያፍነኝ አላደርግም ብዬ ነበረ መስክ አድርገሽ እቃ ግዚ ተብዬ ተላኩ እንቢ ብዬ ገገምኩ ስልባቸው ሀሳቤን ማስቀየር ቀላል እንዳልሆን ስለሚያውቁ እሺ ቶሎ ተመለሺ አሉኝና ሄድኩ።



የተላኩበት ቦታ በኔ አካሄድ 3ደቂቃ ብቻ ነበር የሚፈጀው እኔ ግን ነፂን ካገኘኋት ብዬ በነሱ በኩል ካለ አንድ ሱቅ ገዛውና ስመለስ አገኘኋት ሳያት የተሰማኝን ደስታ ልገልፀው አልችልም ለካ ነባ ነባ እያልኩኝ ስለነበር ነው እንጂ ከሚባለው በላይ ናፍቃኝ ነበር። ለ1ሰአት ያክል ስናወራ ቆየን ግን አልታወቀንም ነበር ከዛ ቤት ስሄድ ነባ ከጀማዎቹጋር ሆኖ አየሁት ከዛ ባላየ ቅደደው ወደቤት ነባ ሲያፏጭ ባልሰማ ብዬው ወደ ቤቴገባ። ቤት ስገባ የታሰርኩ መስሌአቸው ነው መሰለኝ ሊፈልጉኝ ወተው ነበር።ከዛደውዬ ቤት መሆኔን ስነግራቸው መጣን አሉኝ ልክሲመጡ አምላክ እስራኤል እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ነበር ፈጣሪዬ ፅናቱን ስጠኝ አልኩኝ በውስጤ ።

የትነበርሽ የተላክሽበት ቦታ ሄደን አልመጣችም ተባልን የትነበርሽ???!!!
እርፍ ቁጣም አለው አለቀልኝ ፈጣሪዬ የዛሬን ብቻ የዛን ብቻ አልኩኝ በውስጤ
መልሽልን የት ነበር
አይደለም እኮ ከፂ ጋር ነበርኩኝ ከፈለጋችሁ ጠይቋት ስላቸው ጊዜ
ወዲውኑ አመኑኝ ግን ከስድብ አልተረፍኩም ሰው ይጨነቃል ብለሽ አታስቢም እኛ ስንቱን መጥፎ ነገር አስብን ለስለስ ያለሙዚቃ አንድንም አልሰማዋቸውም ምክንያቱም ስለ ነባ እያሰብኩኝ ስለነበር የኔጌታ ስሜን ጠርቶ ላለማስጠቆር ብሌ ሲያፏጭ ደክሞት ይሆን የኔ ውድ ኡኡኡኡኡፍ ስወደው እኮ።


አሁን ሙዚቃቸውን ጨርሰዋል መሰለኝ ወደ መኝታቤት ገብቼ ተኛው ከዛ ምሳሽን ብይ ተብዬ ተጠራው ከዛ በላውና ፊልም ማየት ጀመርኩ አይተሽ ስትጨርሺ ሾርባ ስሪ ማሚ አለችኝ። እሺ አሁን እሰራለው ብዬ ተነሳው ።በባህሪዬ ስራ አለብኝ ብዬ ማሰብ አልፈልግም ሰርቼ መገላገልን ነው ምፈልገው እየሰራው እንዳለው ይሄ እብድ ነባ በሴት ድምፅ አድርጎ ኑሀ አለች ብሌ ጮሆ ተጣራና ልክ ጊቢሲከፈት እኔ እንዳልሆንኩ ሲያውቅ እሮጦ ሄደ ደሞ bro ውጭላይ ስለነበር ወንድ መሆኑን እና እኔ አለመሆኔን ሲያውቅ መሮጢን አውቋል በቃ ኑሀ አሁን መሞቻሽ ደርሷል ንሰሀ ጊቢ አልኩኝ ለራሴ አልኩኝ ለራሴ

ኑለሚን


ክፍል 21ይቀጥላል
•═••• መንታ ልቦች •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌