Get Mystery Box with random crypto!

@mensurabdulkeniofficial

የቴሌግራም ቻናል አርማ mensurabdulkeniofficial — @mensurabdulkeniofficial
ርዕሶች ከሰርጥ:
Heineken
Ucl
Cheerstotherealhardcorefans
የሰርጥ አድራሻ: @mensurabdulkeniofficial
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 226.38K
የሰርጥ መግለጫ

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-04-09 19:58:06
12.6K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:53:47
13.2K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:47:51 የአርሰናል የተስፋ ምድር ጉዞ

ባለፉት ዓመታት በብዙ የሜዳ እና የሜዳ ውጪ ትርምስ እና ሽግግር ውስጥ ያለፉት መድፈኞቹ አሁን ተረጋግተዋል። ከረዥም ጊዜ ወዲህም ወደትልልቅ ድሎች የቀረቡ መስለዋል። ዓምና ፕሪምየር ሊጉን ለማሸነፍ የተፎካከሩት እና ዘንድሮም ከዚያም በተሻለ ጥንካሬ እየተፋለሙ የሚገኙት የሚኬል አርቴታ ልጆች በቻምፒዮንስ ሊጉም ሩብ ፍፃሜ ደርሰው ታላላቆቹን ለመገዳደር ተዘጋጅተዋል።

የአርሰናል የቻምፒየንስ ሊግ ታሪክ በአያዎ የተሞላ ነው። መድፈኞቹ በአርሴን ቬንገር ዘመን ከ1998/99 እስከ 2016/17 ሳያቋርጡ ለ19 የውድድር ዘመናት ሲሳተፉ፣ በዚህ የሚልቋቸው የውድድሩ ኃያል ሬያል ማድሪድ ብቻ ነበሩ። ሰሜን ለንደናዊያኑ ከ2000/01 ጀምሮ ለ17 ተከታታይ የውድድር ዘመን ከመጀመሪያው ምድብ ማጣሪያ በማለፍም ብቸኛ የአውሮፓ ቡድን ነበሩ። ነገር ግን እነዚህ አስደናቂ ጉዞዎች በዋንጫ አልታጀቡም። ለፍፃሜ የደረሱትም አንድ ጊዜ ብቻ ነበር። 'ቻምፒዮንስ ሊግን ያላሸነፈ ትልቁ ክለብ'ም አስብሏቸዋል። ኋላ ላይ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብተው መሳተፍም አቅቷቸው ከስድስት የውድድር ዘመናት በኋላ መመለሳቸው ነው።

ወጣቶቹ መድፈኞች ወደትልቁ የአውሮፓ ውድድር መመለስ ግን የተገመተውን ያክል አልፈተናቸውም። በሰፊ ድል ጀምረው፣ ምድባቸውን በበላይነት አጠናቀው፣ የአውሮፓ መድረክ ደንበኞቹ ፖርቶን በትግል ረትተው ከመጨረሻዎቹ ስምንቶች መካከል ሆነዋል። የአውሮፓ ተሳትፎ የመጨረሻ ዓመቶቻቸው ቀንደኛ የስቃይ ምንጫቸውን የመበቀል እድልም አግኝተዋል። ለህልመኞቹ ኤዱ፣ አርቴታ እና ልጆቹ ግን ባቫሪያኑን መርታት በቂ አይደለም። በክለቡ ታሪክ የትኛውም ትውልድ ያላሳካውን ለማድረግም ተስፋ አድርገዋል።
14.7K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:47:49
12.9K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:38:54
15.0K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:28:21 የከዋክብቱ የመጀመሪያ ትልቅ የቻምፒዮንስ ሊግ ምሽት

አርሰናል ከቻምፒዮንስ ሊግ ለዓመታት የራቀበት ጉዞ በመድረኩ የእንግድነት ስሜትን እንዳይፈጥርበት ተሰግቷል። እንደ ክለብ ብቻ ሳይሆን የቡድኑም ቁልፍ ተጫዋቾች ለአውሮፓው ግዙፍ ውድድር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ባይተዋር ናቸው።

ከኋላው መስመር ማገር ዊሊያም ሳሊባ እንጀምር። ፈረንሳያዊው በቻምፒዮንስ ሊጉም ሆነ ኢሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ አያውቅም። ሃገሩ በትልልቅ ውድድሮች ከፍ ባለ ስኬት ላይ ብትገኝም እስካሁን የዲዲዬ ዴሾ የመጀመሪያ ምርጫ መሆን አልቻለም።

ማርቲን ኦዴጋርድ በአውሮፓ ግዙፍ ክለብ ሪያል ማድሪድ ቢያልፍም በታዳጊነት እድሜ የተጣለበት ተስፋ ትክክለኝነት የታየው ወደእንግሊዝ ካመራበት ዝውውር በኋላ ነው። ሃገሩ ኖርዌይ ደግሞ ከ አህጉራዊ ውድድሮች ተሳትፎ ርቃለች።

የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ቡካዮ ሳካ ከሁለቱ በተሻለ ከገዘፉ ጨዋታዎች ጋር ይተዋወቃል። ግን ደግሞ እንግሊዝ ፍፃሜ በደረሰችበት የአውሮፓ ዋንጫ ከተጠባባቂ ወንበር የሚነሳ ተጫዋች ነበር። በካታሩ ዓለም ዋንጫ ደግሞ ሶስቱ አናብስት ብዙ ርቀት አልተጓዙም።

እነዚህን የልምድ ክፍተቶች ለመድፈን አምና ዌስትሃም ዩናይትድን ለኮንፈረንስ ሊግ ሻምፒዮንነት ያበቃው ዴክላን ራይስ ፣ ቼልሲን የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ያደረገው ካይ ሃቨርትዝና በዛ የፍፃሜ ጨዋታ ለማንችስተር ሲቲ የተጫወተው ጋብሪኤል ዤሱስ ትልቅ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል። የልምድ እጦት አርሰናልን ዋጋ ያስከፍል ይሆን?
17.4K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:28:19
15.3K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:28:15
15.3K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 18:54:38 የቻምፒየንስ ሊግ ክብርን የመጠበቅ ፈተና

1992 የአውሮፓ ግዙፍ ውድድር ኢሮፒያን ካፕ የሚለውን መጠሪያ አሽቀንጥሮ በቻምፒዮንስ ሊግ ከተተካበት ጊዜ አንስቶ አንድ ቡድን ብቻ የሻምፒዮንነት ክብሩን አስጠብቋል። በዚነዲን ዚዳን አሰልጣኝነት ከ2016 እስከ 2018 ከሪያል ማድሪድ ውጪ በአውሮፓ የነገሰ አልነበረም። በቀሪዎቹ ዓመታት ግን ሻምፒዮን ቡድኖች ክብራቸውን በቀጣዩ ዓመት መድገም አልቻሉም።

ሪያል ማድሪድ ዛሬ የሚፋለመውን ማንችስተር ሲቲ ከዚህ ስኬት ሊገታ ይችላል። የሶስትዮሽ ድልን በባርሴሎና ቆይታውም ያሳካው ፔፕ ጓርዲዮላ እንከን አልባ ዓመትን በድጋሚ እንደማይጠብቅ ደጋግሞ ተናግሯል። ቡድናቸው ግን በኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ቼልሲን ይገጥማል። አሁንም በፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ይገኛል።

በቻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ ባለፈው ዓመት በአራት ጎሎች ልዩነት ያሸነፉት ቡድን ከፊታቸው ቆሟል።

የእንግሊዞቹ ሊቨርፑልና ኖቲንግሃም ፎረስትን ጨምሮ በዘመነ ኢሮፒያን ካፕ በስምንት ቡድኖች የተፃፈው የስኬት ታሪክ የፉክክር ጨዋታዎች ብዛትና የጠንካራ ተፎካካሪዎች መጠን በጨመረበት ዘመናዊ እግር ኳስ ከባድ ፈተና ሆኗል። ፔፕ ጓርዲዮላ ከባርሴሎና ጋር ቻምፒዮንስ ሊግን ባሸነፈባቸው ሁለት አጋጣሚዎች መሃል የግማሽ ፍፃሜ ተሳትፎዎች ነበሩት። በማንችስተር ሲቲ ግን ሶስት የሩብ ፍፃሜዎችን ተሸንፏል። የካታላኑ ሰው ለተከታታይ የቻምፒዮንስ ሊግ ክብሮች የስፔንን ዋና ከተማ ቡድን በድጋሚ ማለፍ ይጠበቅበታል።
19.9K viewsedited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 18:54:35
18.4K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ