Get Mystery Box with random crypto!

⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح

የቴሌግራም ቻናል አርማ menhaj_salafiya — ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح
የቴሌግራም ቻናል አርማ menhaj_salafiya — ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح
የሰርጥ አድራሻ: @menhaj_salafiya
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.72K
የሰርጥ መግለጫ

" ሱንና የኑህ መርከብ ናት። የተሳፈረባት ይድናል።
ወደ ኋላ የቀረ ይሰምጣል።" ( ኢማሙ ማሊክ ረሂመሁላህ
Telegram👇
t.me/Sadatcom1
t.me/Kunizewjeten2
t.me/Menhaj_Salafiya
t.me/IbnuMuneworcom
t.me/Muhammedsiragecom

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-02 01:24:25 ከላይ የተለቀቁትን አጫጭር 90 የሚጠጉ ምክሮችን የያዘ የቴሌ ግራም ሊክ ሲሆን ሰዎች ጋር ይደርስ ዘንድ #ጆይና__ሸር በማረግ የበኩላችሁን አስተላልፉት አያስከፍልም መልካምነት ለራስ ነው በአንችና በአንተ ሸር ምክናየት ብዙ ሰዎችን ወደ ሱና ልናመጣ እንችላለን ባረከላሁ ፊኩም !
t.me/Muhammedsiragecom/463
t.me/Muhammedsiragecom/464

የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/Muhammedsirage
t.me/Muhammedsiragecom
529 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 22:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:19:29 1 . አል ቀዋዒዱል ሙስላ
https://t.me/Muhammedsiragecom/7

2 . መሳኢል ጃሂሊያ 1 እስከ 20
https://t.me/Muhammedsiragecom/17

3 . ዓቂደቱ ተውሂድ 1 እስከ 70
https://t.me/Muhammedsiragecom/38

4 . አቂደቱል ዋሲጢያ 1 እስከ 26
https://t.me/Muhammedsiragecom/109

5 . ኡምደቱል አህካም 1__ 31
https://t.me/Muhammedsiragecom/136

6 . ኩን ሰለፍየን አለል ጃዳ
https://t.me/Muhammedsiragecom/168

7 . ሶስቱ መሰረቶች ( الأصول الثلاثة )
https://t.me/Muhammedsiragecom/201

8 . ሚን ኡሱሊ አቂደቲል አህሉል ሱና ወልጀማዓ
https://t.me/Muhammedsiragecom/215

9 . እስልምናን የሚያፈርሱ (نواقض الإسلام )
https://t.me/Muhammedsiragecom/222

10 . ከሽፉ ሹበሃት كشف الشبهات
https://t.me/Muhammedsiragecom/228

11 . ነዋቂዱ አልኢስላም
https://t.me/Muhammedsiragecom/241

12 . ሙቀዲመቱል አጅሩምያ
https://t.me/Muhammedsiragecom/249

13 . ኪታቡ ሲያም ) ( كتاب الصيام)
ዑምደቱል አህካም عمدة الأحكام
https://t.me/Muhammedsiragecom/273

14 መሳኢሉል ጃሂሊያ ከክፍል 1____17
https://t.me/Muhammedsiragecom/295

የድምፅ ፋይሎችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሸር ያርጉት
ባረከላሁ ፊኩም
t.me/Muhammedsiragecom
t.me/Muhammedsiragecom
t.me/Muhammedsiragecom
383 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:14:20 ዋጅብ ሰላትን አጠር ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲባል አሯሩጦ መስገድ ተፈልጎ አይደለም -

አስቸጋሪ ማስረዘም ውስጥ ገብተን አማኞችን አለማስቸገር ነው የተፈለገው ። ተረጋግተን በአግባቡ እንስገድ እናሰግድ ።

ሰላትን በስርአቱ በመስገድ ግዴታችንን እየተወጣን የአምልኮውን ጣእም ለማግኘት እንጣጣር ።
አሏህ ይምራን ።

https://t.me/Muhammedsirage
343 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 23:38:17 ይድረስ ለወይዘሪት አ - ሕ - ባ - ሽ
ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ነው!!
~~ ~~~~
በናንተ ምክኒያት ስንት ኢስላማዊ ተቋም ተዘጋ? ስንቱ ተደበደበ? ስንቱ ታሰረ? ስንቱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ? ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተገታ? ስንትስ ቤተሰብ ተናጋ? ከምንም በላይ ደግሞ በኢስላም ስም ስንት የተበላሸ ዐቂዳ ደካሞች ላይ አሰረፃችሁ? ኢስላምን ስንት አመት ወደ ኋላ ለመጎተት እየተውተረተራችሁ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም - ለካ * ፊ & ር እንኳን፣ ለናንተ ሲቀር፡፡ እናንተማ ከሰል ጠቆረ ውሃ ቀጠነ ብላችሁ የምትከራከሩ ናችሁ፡፡ እናንተ'ኮ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው” የምትሉ ናችሁ፡፡ ሀሰት ካላችሁ ኪታባችሁ ይናገራል፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119)) እንዴት ያለች “ፅድት” ያለች እምነት ነችi የዝንብ ጡሃራ አይነት እንዳትሆን ብቻ። “የዝንብ ጡሃራ ከነጃሳ እኩል ነው” ትል ነበር እህቴ፡፡ አባባሉን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ብቻ ሳስታውስ አጓጉል የሆነ ንፅህና ስታይ ነበር እንዲህ የምትለው፡፡ ግን አ - ሕ - ባ - ሽ “ጡሃሪት” በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ትላለች፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99 - 100 (አዲሱ እትም፡ 131-132))፡፡
እኔን የገረመኝ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው” ማለታቸው አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ “በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል” ማለታቸውም አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ የሚገርመኝም ሁለቱ የተራራቁ ሀሳቦች ከአንድ አካል መውጣታቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት “የውሻ ኩስ አይነጅስም” ያለ ሰው “የትኋን ደም ይነጅሳል” ይላል? ኧረ ተመስጌን በሉ። “ምራቋም ይነጅሳል” ብለው የካ * ፊ & ር መሳለቀያ ቢያደርጉን ምን ይባል ነበር? ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር፡፡
ለነገሩ እንዲያው ቢገርመኝ አነሳሁት እንጂ ከዚህ የከፋ ስንት የዐቂዳ ክፍተት አለባቸው አይደለም ወይ? ለምሳሌ “አላህ አለም ውስጥም የለም፣ ከአለም ውጭም የለም፣ ከአለም ጋር ተያይዞም የለም፣ ተነጣጥሎም የለም” የሚሉት፡፡ ሱብሐነላህ! ሰዎቹ ምን እየሆኑ ነው? ይሄ ምን ማለት ነው? ይሄ ብቻ አይደለም “አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደለም” ይላል ሸይኻቸው አብደላህ አልሀረሪ፡፡ ምነው ስትሉ “ለምሳሌ አላህ መበደል አይችልም” ሲል ይፈላሰፍባችኋል፡፡ እናስ አላህ ስላቃተው ነው እንዴ የማይበድለው? ፍትሃዊ ስለሆነ እንጂ፡፡ ይሄውና በሐዲሠል ቁድሲ ላይ፡- “ባሮቼ ሆይ! እኔ በራሴ ላይ በደልን ክልክል አድርጊያለሁ፤ በናንተም መካከል እንዲሁ ክልክል አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ” ይላል ጌታችን፡፡ ስለዚህ ስለሚችል አይደለም እንዴ በራሱ ላይ ክልክል ያደረገው? ባይችል እንዲህ ይል ነበር? ኧረ እነኚህ ሰዎች በምንኛ ነው የሚያስቡት?
ይሄን ሁሉ እያደረጉ ከማንም በላይ ለኢስላም እየሰሩ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ድንቄምi “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ነውና ነገሩ ይሄው ለጊዜው የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን ከጉልበተኛ ተጠግተው የማይችሉትንም ጭምር እያደረሱ ነው፡፡ “ውጭ ካለ መቶ ጠላት ቤት ውስጥ ያለ አንድ ጠላት የከፋ ነው” ይላሉ ዐረቦች፡፡ ጥፋታችሁ ምንኛ ከፋ?! ይሄ አቋማችሁ ድንገት አንድ ቀን ተሳስታችሁ ካሰባችሁ ያሳፍራችኋል፡፡ ምናልባት ካሰባችሁ።
ኧረ አላህን ፍሩ! ሞት አለ፣ የቀብር ጥያቄ አለ፣ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ፣ ሲራጥ አለ፣….፡፡ ከውስጣችሁ አላህን የሚፈራ የለምንዴ? ለነገሩ ይሄ ቋንቋ መቼ ይገባችኋል? ጨው ቀምሳችኋላ! ምነው “አልገባንም” ብላችሁ ዝም ባላችሁ!!! ገልብጣችሁ መረዳታችሁ ከፋ እንጂ፡፡
ግን ቢገባችሁም ባይገባችሁም ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ትሸነፋላችሁ! እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው! እየጠነቆልኩ አይደለም፡፡ በጥንቆላም በኹራፋትም አላምንም፡፡ ይቺ የናንተ ናት፡፡ እናም እላለሁ፡፡ አይወድቁ አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ሰማያዊ፣ መለኮታዊ መመሪያ አንብቤ ነው ይህን የምለው፡፡ ኢስላምን ሊያጠቃ የመጣ የውስጥም ይሁን የውጭ ጠላት መቼም ቢሆን ቋሚ ድል ሊቀናው አይችልም፡፡ ይሄው አብረን እናንብብ፡-
{ یُرِیدُونَ أَن یُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَیَأۡبَى ٱللَّهُ إِلَّاۤ أَن یُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ (32) هُوَ ٱلَّذِیۤ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِینِ ٱلۡحَقِّ لِیُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّینِ كُلِّهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُشۡرِكُونَ (33) }
((የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡
[አሶፍ፡ 32-33]

ታማኙና እውነተኛው ነብይም ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ “ውርደትና የበታችነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን” ብለዋል።
በርግጥ ብዙ መስዋእትነት ታስከፍሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ዲኑ ብዙ ሊከፈልለት የሚገባ ዲን ነውና ወደ ኋላ አንልም፡፡ በአላህ ፈቃድ ትወድቃላችሁ፡፡ እንዲያውም የሮማን አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ታዲያ አትሰሙም እንጂ ወድቃችሁ መውደቃችሁ ላይቀር መፈራገጥ ባታበዙ መልካም ነበር፡፡ “የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።”
-
ማሳሰቢያ፦
ከላይ ምንጭ እያያዝኩ የጠቀስኳቸውና ሌሎችም የአ - ሕ - ባ - ሽ ጥፋቶች የኋላ እትሞች ላይ ከፊሎቹን ገፅ በመቀየር ከፊሎቹን ደግሞ ከነ ጭራሹ በማውጣት አስወግደዋል። ታዲያ ካጠፉ ለምን ይነሳል? እንዳይባል "ስህተት ነበር ታርሟል" በማለት ፋንታ ሽምጥጥ አድርገው "ተዋሽቶብን ነው" እያሉ ነው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10 / 2005)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
307 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 00:47:11 አድስ ሙሓደራ


➧የሴት ልጂ ድርሻ በኢስላም!

በኡስታዝ ሰዒድ ሙ/ድ ኑር

https://t.me/Tewhed
https://t.me/Tewhed
586 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 21:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 00:28:14 ከታሪክ አምባ
(ክፍል ስድስት)
~~~
ጨካኙና ደም አፍሳሹ ሐጃጅ ብኑ ዩሱፍ ከሰዒድ ብኑል ሙሰይብ ጎን እየሰገደ ነበር። ከኢማሙ ቀድሞ ይነሳል፣ ቀድሞም ይወርዳል። ኢማሙ ሲያሰላምት ጊዜ ሰዒድ የሐጃጅን ልብስ ጨምድደው ያዙና ከሶላት በኋላ የሚሉትን ዚክር መዘከር ያዙ። ሐጃጅ ተነስቶ ሊሄድ በማሰብ ልብሱን ሊያስለቅቅ ይታገላል። ሰዒድ ደግሞ ሊያስቀምጡት ይጎትቱታል። ሰዒድ ዚክራቸውን እስከሚያጠናቅቁ በዚህ መልኩ ቀጠሉ። ከዚያም ሰዒድ ሁለት ጫማዎቻቸውን በማንሳት በሐጃጅ ላይ አነሷቸው።
“አንተ ሌባ! አንተ ሸፍጠኛ!! እንዲህ አይነት ሶላት ነው የምትሰግደው?! በነዚህ ፊትህን ላጣፋህ ነበር ያሰብኩት” አሉት።

ሐጃጅ ተነስቶ ሄደ። ወደ ሐጅ እየተጓዘ ነበር። ሐጁን ጨርሶ ወደ ሻም ተመለሰ። ከዚያም የመዲና ገዢ ተደርጎ ወደ መዲና መጣ። መዲና እንደገባ ባለበት ሁኔታ ቀጥታ ሰዒድ ብኑል ሙሰይብ ወደሚቀመጡበት ነበር ያመራው። ሰዎች ሊበቀላቸው እንጂ ለሌላ አልመጣም አሉ። ከፊታቸው ተቀመጠ።
* “አንተ ነህ አይደል እነዚያን ቃላት የተናገርካቸው?” አለ።
ሰዒድ፡ በእጃቸው ደረታቸውን ከደቁ በኋላ “አዎ እኔ ነኝ!” አሉት። * ሐጃጅ በዚህን ጊዜ እንዲህ አለ፡-
“ጥሩ አስተማሪና ቀጪ ስለሆንክ አላህ በመልካም ይመንዳህ። ካንተ በኋላ ሶላት አልሰገድኩም፣ ንግግርህን የማስታውስ ብሆን እንጂ” ብሎ ተነስቶ ሄደ።
[ታሪኹ ዲመሽቅ፣ ኢብኑ ዐሳኪር፡ 12/120]

ከታሪኩ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች:-

1- መልካም ሰለፎች ሰዎችን ከጥፋት ለማረም የነበራቸውን ቁርጠኝነትና ጥንካሬ፣
2- ጨካኙ ሐጃጅ ከሱ ከሚገመተው በተቃራኒ የቀረበለትን አሸማቃቂ ተግሳፅ መነሻ አድርጎ ስልጣን ሲይዝ ጊዜ ለበቀል አለመነሳቱ። እንዲያውም አመስግኖ መቀበሉ።
3- ሰዒድ ብኑል ሙሰይብ ረሒመሁላህ ሐጃጅን ፈርተው አለመታጠፋቸው የነበራቸውን ጀግንነት ያሳያል።

እኚህ ናቸው አባቶቼ --- አምሳያ ካለህ ዝከር
በሰው ልጅ ረጅም ታሪክ --- የማይገኝላቸው ወደር
የፍትህ የጀግንነት --- ጫፍ የተቆናጠጡ
ለጨካኞች ተንበርክከው --- ፍፁም እጅ የማይሰጡ።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
431 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:55:31 ወንድም እህቶች ሆይ!
~
ታላቁ ፍንዳታ (Big bang) እያሉ የሚጠሩት ንድፈ ሃሳብ ብዙ ትችት ያለበት፣ ፈፅሞ የማያሳምን፣ ተጨባጭ ማስረጃ ሳይሆን ግምት ላይ የተመሰረተ ንድፈ-ሃሳብ ነው። እንዲህ አይነቱን ያልተጨበጠ ንድፈ-ሃሳብ በቁርኣን እንደተገለፀ አድርጎ ማቅረብ ቁርኣንን በልቦለዳዊ ዝንባሌ (هوى) መፈሰር ስለሆነ አደገኛ ጥፋት ነው። የሰለፍ ምሁራንንና ቀደምት ታላላቅ ዑለማዎችን የቁርኣን ትንታኔ ለዚህ ላልተጨበጠ theory ድጋፍ እያደረጉ ማቅረብ በነሱ ላይ መዋሸት፣ ሌላ ድርብ ጥፋት መፈፀም ነው። ስለዚህ አላህን ልንፈራ ይገባል። "ሳይንሱ" በተለይም በስነ ፈለክ ጉዳይ የሚሰጠው ትንታኔ ጥቂት እውነት (ጫፍ) ይዞ ብዙ ግምት ወለድ ድምዳሜ መስጠት የበዛበት ነው። ስለዚህ የነሱን ትንታኔ ከቁርኣን ጋር ለማዛመድ መቸኮል አይገባም። ብዙዎቹ የሳይንስና ቁርኣን ትንታኔዎች ቁርኣንን ያላግባብ በመተንተን የታጨቁ ፀያፍ ስራዎች ናቸው። ሰዎች ግን ለራሳቸው የየቂን ክፍተት መድፈኛ ወይም የኢማን መሳሳት መጠገኛ ወይም ደግሞ ለ "ሳይንስ" "አምላኪዎች" ማሳመኛ አድርገው ማቅረብ ስለሚሹ በኢስላም ሚዛን በቅጡ ሳይመረምሩ፣ ታማኝ ዓሊሞች ምን እንደሚሉ ሳይፈትሹ፣ ምን አንድምታ እንዳለው አሻግረው ሳያዩ እንዲሁ እንደ ቁም ነገር ያራግቡታል። እንደ ትልቅ ነገር ይደመሙበታል። ሌላው ሁሉ ቢቀር የሚቀርቡላቸው ምስሎች፣ ዳታዎችና "facቶች" እራሱ ነጮቹ ያሉትን እንደወረደ ከመዋጥ ባለፈ እውነተኛ ስለመሆናቸው እንኳ ምንም ማረጋገጫ የላቸውም። የሚያረጋግጡባቸው መንገድም የላቸውም። ባጭሩ ከዚህ አንዳንዶች ከተለከፉበት ቁርኣንን ወደ ሳይንስ የማፍሰስ አባዜ እራሳችንን ልናርቅ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
613 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 11:48:36
قال الشيخ محمد بن عمر بازمول حفظه الله:

تــــزوج : فإن خفت من اختيار الزوجة، فاستعن بالاستخارة ، والاستشارة، وما خاب من استخار ، وما ندم من استشار!

تـــزوج : فإن خفت من المصاريف ومؤونة الأسرة ومن الفقر؛ فاستعذ بالله من الشيطان ، واعلم أن هذا لمة شيطانية، ألم تسمع قول الله تبارك وتعالى: { الشَّيْطَانُ يَعِدُكُمُ الْفَقْرَ وَيَأْمُرُكُمْ بِالْفَحْشَاءِ وَاللَّهُ يَعِدُكُمْ مَغْفِرَةً مِنْهُ وَفَضْلًا وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ } [البقرة: 268]!

تـــزوج : فإن خفت من الأولاد والعيلة ، فتذكر أن الله هو الرزاق، وأن الزواج طريق الغنى بإذن الله تعالى:
{وَأَنْكِحُوا الْأَيَامَى مِنْكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ إِنْ يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ } [النور: 32]

تـــزوج ፡ فإن خفت أن يشغلك الزواج عن العلم ... فاعلم أن هذه لمة شيطانية... فإن الرسول صلى الله عليه وسلم رغب الأمة في الزواج، ولو كان يتعارض مع طلب العلم لما رغب فيه، بل رأينا في واقع الحياة أن المتزوج يسهل عليه العلم والتحصيل والتزام طريق الخير أكثر من غيره.
t.me/Kunizewjeten2
606 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:18:34
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

عيد سعيد مبارك أعاده علينا وعليكم وعلى الأمه الإسلاميه بالخير والسعادة والبركات تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال.. )
531 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ