Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ menefesawitereka — መንፈሳዊ ትረካ ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ menefesawitereka — መንፈሳዊ ትረካ ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @menefesawitereka
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነምህረት ስላለኝ ነው ምክንያት..........
መልቀቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ @Ermiyas3 ላይ ወይም ደግሞ @Enate_mariyam3 ላይ አናግሩኝ #Ermiyas

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-23 11:25:43 Watch "ዘርሽ ማነዉ አሉኝ?" on YouTube


2.5K viewsMele Ye Enatu, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-18 20:23:45
2.6K viewsZe Amlak , 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-16 11:34:06

2.5K viewsMele Ye Enatu, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-02 06:53:05 #ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ ማስጮህ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን
አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣ ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን


@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
t.me//menefesawitereka
3.3K viewsእኔን ተውኝ ህልሜ እዚ ነው, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-02 06:52:33 .......ባህላው ቡሄ....................ወዳጆቼ ኑ
እስቲ ቡሄ እንበል ተቀበሉኝ እስቲ ቡሄ በሉ......ሆ (2)
ሰዎች ሀሉ.....ሆ
የኛማ ጌታ......ሆ የአለም ፈጣሪ.....ሆ
የሰላም አምላክ.....ሆ ትሁት መሀሪ...ሆ
በደብረ ታቦር........ሆ የተገለጠው ...ሆ
ፊቱ እንደፀሀይ...ሆ በርቶ የታየው....ሆ
ልብሱ እንደብርሃን....ሆ ያንፀባረቀው...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ያዕቆብ ዩሀንስ...ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ...ሆ አምላክን
አዩ....ሆ ሙሴ ኤልያስ...ሆ
አባቱም አለ ....ሆ ልጄን ስሙት....ሆ
ቃሌ ነውና .....ሆ የወለድኩት...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና (2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
.......
ታቦር አርሞንኤም...ሆ ብርሃን ታየባቸው ........ሆ
ከቅዱስ ተራራ...ሆ እጅግ ደስ አላቸው....ሆ
ሰላም ሰለም.....ሆ የታቦር ተራራ....ሆ
ብርሃነ መለኮት......ሆ ባንቺ ላይ አበራ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.....
በአባቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት.....ሆ
በእናቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአጎቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአክስቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
ተከምሯል...ሆ እንደኩበት....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2(
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን (2)
.......
የአመት ልምዳችን...ሆ ከጥንት የመጣ...ሆ
ከተከመረው ....ሆ ከመሶቡ ይምጣ
በደብረ ታቦር ...ሆ ጌታ ስለመጣ...ሆ
የተጋገረው ....ሆሙልሙሉ ይምጣ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.......
በተዋህዶ...ሆ ወልድ ያከበረው....ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ....ሆ ወልደ ማርያም ነው...ሆ
ቡሄ በሉ ...ሆ ቡሄ በሉ .....ሆ
የአዳም ልጆች...ሆ ብርሃንን ...ሆ ተቀበሉ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ኢትዮጽያውያን....ሆ ታሪክ ያላችሁ...ሆ
ባህላችሁን....ሆ ያዙ አጥብቃችሁ...ሆ
ችቦውን አብሩ..ሆ እንደአባቶቻችሁ...ሆ
ሚስጥር ስላለው...ሆ ደስ ይበላችሁ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
......
ለድንግል ማርያም...ሆ አስራት የሆንሽ...ሆ
ቅዱሳን ፃድቃን ....ሆ የሞሉብሽ ...ሆ
በረከታቸው ያደረብሽ...ሆ ሁሌም እንግዶች ...ሆ
የሚያርፉብሽ....ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ....ሆ ኢትዪጵያ ነሽ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛምበራልን(2)
........
ለሀዋርያት ...ሆ የላከው መንፈስ ...ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ...ሆ ፀጋውን ያፍስስ ....ሆ
በበጎ ምግባር ...ሆ እንድንታደስ ...ሆ
በቅን ልቦና ...ሆ በጥሩ መንፈስ...ሆ
በረከተ ቡሄ...ሆ ለሁላችን ይድረስ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን (2)
አመት አውደ አመት ድገምና አመት ድገምና...........
..............እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል
ይሁንላችሁ ፡፡ጎዶሊያስ

@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

t.me//menefesawitereka
2.3K viewsእኔን ተውኝ ህልሜ እዚ ነው, 03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-02 06:52:33 ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======
ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======
በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======
አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======
የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ
አዝ======
አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ
የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ
እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ
ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ
አዝ======
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ
በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ
ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
አዝ======
ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ
በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ
በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን ይድረስ - ሆ
= = = = = =
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
= = = = = =

እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር
ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር
= = = = = =

የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት(፪)
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት ሀገር ብለን የድንግል ናት
ያቆዩልንን የአበው ቀደምት
ይገባልና ልንጠብቀው
ባህላዊውን የአባቶች ትውፊት(፪)

@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
t.me//menefesawitereka
2.2K viewsእኔን ተውኝ ህልሜ እዚ ነው, 03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 15:07:09 ውድ የ #መንፈሳዊ_ትረካ ቻናል ተከታታዮች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ከሚዲያ እርቀን እነደቆየን ይታወቃል እናም በ እግዚያብሄር ስም ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን
ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ እርእሠ ጉዳዮች እንመጣለን የተለያዩ ትረካዎችን እንለቃለን አብሮነታችሁ አይለየን ተዋህዶ ሀይማኖታችንን እግዚያብሔር አምላክ ይጠብቅልን የ በእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ፀሎት በረከቷ አይለየን አሜን

t.me//menefesawitereka
2.0K viewsE S, 12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 20:35:04
3.2K viewsZe Amlak, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 17:02:15 እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን እየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና እንደተናገረ ተነስቶአልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና ከሙታን ተነሣ እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩዋቸው። እነሆም ኢየሱስ ነገርኋችሁ። በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ። እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው።

--------------------------◈-------------------------

ሞት ጠፍቶልናል "ደስ ይበላችሁ። "

◇◇◇ ማቴ 28÷5-9 ◇◇◇



ለሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ::

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን ⁣⁣
2.9K viewsZe Amlak, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 16:05:44 ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን

በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤

አሠሮ ለሰይጣን

አግዓዞ ለአዳም፤

ሰላም

እምይእዜሰ

ኮነ

ፍሥሐ ወሰላም።

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ አደረሰን ።⁣
2.6K viewsZe Amlak, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ