Get Mystery Box with random crypto!

.......ባህላው ቡሄ....................ወዳጆቼ ኑ እስቲ ቡሄ እንበል ተቀበሉኝ እስቲ | መንፈሳዊ ትረካ ብቻ

.......ባህላው ቡሄ....................ወዳጆቼ ኑ
እስቲ ቡሄ እንበል ተቀበሉኝ እስቲ ቡሄ በሉ......ሆ (2)
ሰዎች ሀሉ.....ሆ
የኛማ ጌታ......ሆ የአለም ፈጣሪ.....ሆ
የሰላም አምላክ.....ሆ ትሁት መሀሪ...ሆ
በደብረ ታቦር........ሆ የተገለጠው ...ሆ
ፊቱ እንደፀሀይ...ሆ በርቶ የታየው....ሆ
ልብሱ እንደብርሃን....ሆ ያንፀባረቀው...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ያዕቆብ ዩሀንስ...ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ...ሆ አምላክን
አዩ....ሆ ሙሴ ኤልያስ...ሆ
አባቱም አለ ....ሆ ልጄን ስሙት....ሆ
ቃሌ ነውና .....ሆ የወለድኩት...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና (2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
.......
ታቦር አርሞንኤም...ሆ ብርሃን ታየባቸው ........ሆ
ከቅዱስ ተራራ...ሆ እጅግ ደስ አላቸው....ሆ
ሰላም ሰለም.....ሆ የታቦር ተራራ....ሆ
ብርሃነ መለኮት......ሆ ባንቺ ላይ አበራ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.....
በአባቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት.....ሆ
በእናቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአጎቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአክስቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
ተከምሯል...ሆ እንደኩበት....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2(
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን (2)
.......
የአመት ልምዳችን...ሆ ከጥንት የመጣ...ሆ
ከተከመረው ....ሆ ከመሶቡ ይምጣ
በደብረ ታቦር ...ሆ ጌታ ስለመጣ...ሆ
የተጋገረው ....ሆሙልሙሉ ይምጣ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.......
በተዋህዶ...ሆ ወልድ ያከበረው....ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ....ሆ ወልደ ማርያም ነው...ሆ
ቡሄ በሉ ...ሆ ቡሄ በሉ .....ሆ
የአዳም ልጆች...ሆ ብርሃንን ...ሆ ተቀበሉ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ኢትዮጽያውያን....ሆ ታሪክ ያላችሁ...ሆ
ባህላችሁን....ሆ ያዙ አጥብቃችሁ...ሆ
ችቦውን አብሩ..ሆ እንደአባቶቻችሁ...ሆ
ሚስጥር ስላለው...ሆ ደስ ይበላችሁ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
......
ለድንግል ማርያም...ሆ አስራት የሆንሽ...ሆ
ቅዱሳን ፃድቃን ....ሆ የሞሉብሽ ...ሆ
በረከታቸው ያደረብሽ...ሆ ሁሌም እንግዶች ...ሆ
የሚያርፉብሽ....ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ....ሆ ኢትዪጵያ ነሽ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛምበራልን(2)
........
ለሀዋርያት ...ሆ የላከው መንፈስ ...ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ...ሆ ፀጋውን ያፍስስ ....ሆ
በበጎ ምግባር ...ሆ እንድንታደስ ...ሆ
በቅን ልቦና ...ሆ በጥሩ መንፈስ...ሆ
በረከተ ቡሄ...ሆ ለሁላችን ይድረስ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን (2)
አመት አውደ አመት ድገምና አመት ድገምና...........
..............እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል
ይሁንላችሁ ፡፡ጎዶሊያስ

@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka

t.me//menefesawitereka