Get Mystery Box with random crypto!

የዕንቁ መምህሮቻችን ትምህርቶች🔥

የቴሌግራም ቻናል አርማ memhrochachn — የዕንቁ መምህሮቻችን ትምህርቶች🔥
የቴሌግራም ቻናል አርማ memhrochachn — የዕንቁ መምህሮቻችን ትምህርቶች🔥
የሰርጥ አድራሻ: @memhrochachn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.95K
የሰርጥ መግለጫ

የ ዕንቁ መምህሮቻችን ትምህርቶች የሚለቀቅበት ቻናል

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 08:17:46 እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡
@memhrochachn
1.3K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 02:07:58 “አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡

አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178)
1.1K views23:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 23:09:40 "አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
1.4K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:25:23 ጌታችን ለወንበዴው <<በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ > የሚል ልመና እውነት እውነት እልሃለሁ ፤ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ብሎ ወዲያውኑ :መልስ ሰጠ በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ፧ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው ።
በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግስት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት ፡ከቁጣ የራቀ ምህረቱ የበዛው አምላክ :ክፉ ስራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል <የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል ስለዚህ ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ! ይህንን ምህረት ተስፋ አድርገን << ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንት በኃጢአት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ እያልን እንጸልያለን !
1.2K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:25:23 «ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን» ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ
1.3K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:12:09    ቃለ እግዚአብሔርን በአእምሮ ያይደለ በልብ መማር ወደ ፍቅር መልክ ያደርሳል፡፡ ሰፊ ጊዜን ሰጥቶ የአምላክን ቃል ከአንጀት መማር ፍቅርን ያሳድጋል፡፡ ለምን ቢሉ..."የእግዚአብሔር ቃል" በራሱ ፍቅር ነውና፡፡ እርሱ ሥጋ ለብሶ በዓለም ላይ የፍቅር ድምፆችን (ወንጌል) እንዳሰማ ሁሉ፤ ድምፁን ከእውነት በሰማን ጊዜ ፍቅርነቱ ከውስጣችን ሥጋ ይለብሳል፡፡ በአሳብ፣ በእቅድ፣ በድርጊት፣ በአኗኗር ውስጥ ዘልቆ ይገለጻል፡፡ ቃሉ "መንፈስና ሕይወት" ነው፡፡

@mehrochachn
1.1K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:09:41 "ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።"
#ቅዱስ_ሚናስ
1.0K views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:14:18 ሰው ሁን!

✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ዶክተር (ሐኪም) አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መሐንዲስ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መምህር አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ፖለቲከኛ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ጋዜጠኛ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መሪ፣ #መካሪ፣ #አውሪ፣ #ዘማሪ፣ #ጸሐፊ፣ #ለጣፊ፣ #ሰባኪ፣ #ሹመኛ፣ #ወገኛ.... ሌላም አትሁን፡፡

ዓለም፣ ኢትዮጵያ፣ ቤተ ክርስቲያንም ያጣችው ይህንን ሁሉ አይደለም፡፡ ሰው የሚሆንላትን እንጂ፡፡ ይልቁንስ ከሁሉ በፊት ሰው ሁን፡፡ ሰው መሆን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማንነት ነውና፡፡

"ሰብአዊነት የጎደለው ሙያ በመርዝ ዕቃ ላይ እንደተቀመጠ ጣፋጭ ምግብ ነው" ይላሉ አበው፡፡ የችግሮቻችን ሁሉ መነሻም ሰብአዊነት የጎደለው ግብራችን ነው፡፡

መጽሐፍስ ምን አለ? "ሰው ሁን፡፡" (1ነገ. 2፡3)

✿ሰው ለመሆን ያብቃን፡፡

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
1.2K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:39:39 "ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። "

ማቴ. 5÷43-47
1.0K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:34:02 «ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ(በእንባ) ምላቸው።ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"

ማር ይስሐቅ ሶርያዊ

@memhrochachn
1.3K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ