Get Mystery Box with random crypto!

ዛፍዋም ከአንድም ሁለት ሦስቴ ብትነገረኝ እኔ ዘዴዬ ያዋጣኛል ብዬ ብልጠት ለመጠቀም ሞከርኩ፡፡ ብል | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ዛፍዋም ከአንድም ሁለት ሦስቴ ብትነገረኝ እኔ ዘዴዬ ያዋጣኛል ብዬ ብልጠት ለመጠቀም ሞከርኩ፡፡ ብልጠቴ ምን መሰላችሁ፡፡ ጌታችሁ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ለአምስት ሺ አምት መቶ አመታት ሲሰቃዩ የነበሩትን ነፍሳት ለማውጣት ሲኦል እንደሚወርድ አውቅ ነበር፡፡

እኔም ጌታችሁ በራሱ ሥልጣን ዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከክቡር ሥጋው ሳይለይ ቀድሜ ሞቼ ሲኦል ዱቅ ብዬ ልጠብቀው ወሰንኩ ምክንያቱም ከሲኦል ከሚወጡት ነፈሳት ጋር አብሬ ልወጣ፡፡ ኡኡቴ ተዘይዶ ተሞቷል፡፡

ጌታችሁም ብልጠቴን አውቆ ከዛፉ በጢንቢራዬ ቢጥለኝ አንጀቴ ተዘርግፎ ለአርባ ቀን በሰቀቀን ሳልሞት ቆየሁ፡፡ ጌታችሁ በሲኦል ያሉትን ነፍሳት ጥርግርግ አድርጎ ካወጣ በኋላ እኔ በአርባ ቀኔ ሞትኩ፡፡ አዳሜ ገነት ለመግባት የሚያስፈልገው ዘዴ/ብልጠት/ ሳይሆን ሕጉን መጠበቅ፣ ምግባር መሥራት ወዘተ ነው፡፡ በብልጠት የትም አትደርሱም፡፡

ጀለሶቼ ሲኦል ስሄድ ከሦስት ሰዎች በስተቀር ሲኦል ኦና ሆና ጠበቀችኝ፡፡ እነዚህ ሦስት ሰዎች ያልኳችሁ ጌታ በእለተ አርብ ከሲኦል ያላወጣበት ምክንያት በደላቸው፣ ኃጢአታቸው አገር አቀፍ ስለሆነ ነው፡፡ እነሱም ፈርዖን፣ ጽሩ ጻይዳ እና ሔሮድስ ናቸው፡፡

የፈርዖንን በደል እና ኃጢአት ዘመናችሁን ስትሰሙት፣ ስትማሩት ነው ያደጋችሁት ታሪኩን ለእናንተ ትቻለሁ፡፡ ጽሩ ጻይዳ በምድያምና በሜዶን አምልኮተ ጣዖትን አስፋፍቷል፤ ይባስ ብሎ ንጹሐኑን የመቃቢስን ልጆች ሲላ፣ አብያና ፈንቶስን አስገድሏል፡፡

ሔሮድስም እንደምታውቁት አሥራ አራት እልፍ/መቶ አርባ ሺ ሕፃናትን አስፈጅቶ፣ እስራኤልንም በደም ውሃ አርግቶ ግፍ ሠርቷል፡፡ እነዚህ ሦስቱ ክፉ ሰዎች ጌታችሁ በዲያቢሎስ መንግሥት በሲኦል ተዋቸው፡፡ ምክንያቱም ፍዳቸው ፅኑ ነውና፡፡ ሲዖልም አትለቅም ገነትም አትቀበልም፡፡

ጋይስ አጅሬም በሲዖል ብቻዬን አገኘኝ፡፡ ተዉ ያደረገልኝን የመከራ አቀባበል በቃላት ልነግራችሁ አልችልም፡፡ ጌታ የማረከበትን የሺ ዓመታቶች ነፍሳት ብስጭት እኔ ላይ ተወጣ፡፡ ያላደረገኝ ያላሰቃየኝ ነገር የለም፡፡ ስቃዩን ስትመጡ ስለምታዩት ያኔ ትረዱኛላችሁ፡፡

ነፍሳት ከሲኦል ሲወጡ፣ በሲኦል እንደ ተዋጡ የቀሩ ሦስቱ የሲዖል ጀለሶቼ ‹‹ዩዲ አይዞኝ እኛም እንዳንተ ተከርቸም ውስጥ ገብተን በነፍሳችን ቶርች ስንደረግ ነው የከረምነው፣ ዩዲ ሲዖል ቻል ነው የሚደረገው እንጂ አይለቀስም፡፡ ለነገሩ ብታለቅስ ማን ሊደርስልህ›› ብለው መከሩኝ ልበል አጽናኑኝ አላውቅም፡፡

ይኸው ሲኦልን ግዛቴ ርስቴ አድርጌ ከተቀመጥኩ ሁለት ሺ ዓታት አለፉኝ፡፡ ወድጄም በትንቢት ተገድጄም ጌታዬን ብሸጥም ለሳጥናኤል በሲኦል እየተገዛሁ እኖራሉ፡፡ ጀለሶቼ ገና ምን አየሁ ያ ‹‹ገሃነመ እሳት›› የሚባል ይጠብቀኛል አሉ፡፡

ዞሮ ዞሮ ነብዩ ኤርምያስ በትንቢቱ ‹‹ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፣ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ›› የተባለው ቀደምት ትንቢት፤ የዕንባቆምም ንግርት፤ ጌታችሁም የተናገረብኝ ሁሉ ደርሶብኝ ባልበላሁት ሠላሳ ብር ጌታችሁን ሽጬ ለዘመነ አዝማናት አሳሬን እበላለሁ፡፡

ጋይስ እኔ አሁን በሲኦል እየተቀበልኩ ያለሁት መከራ ከበቂዬ በላይ ነው፡፡ ግን እናንተ ሁሌም በየዓመቱ ስትረግሙኝ ስትደበድቡኝ በኋላ በሲኦል ተገናኝተን ከምንላቀስ፤ ለራሳችሁ ብትጠነቀቁ፣ የጌታችሁን ትዕዛዛት ብትጠብቁ፣ ንስሐም ገብታችሁ ብትጸድቁ ነው የሚያዋጣችሁ፡፡ ለማንኛውም የእኔ ፋሲካ በሲኦል መሰቃየት ስለሆነ እችለዋለሁ፡፡ ‹‹ላይችል አይሰጥ›› አሉ!

አንድ ነገር እወቁ የሲኦል የመግቢያ በር ላይ ለሚመጡት ምስኪን ነፍሳት አቀባበል የማደርገው እኔ ስለሆን ወደ ተሻለ የስቃይ ቦታ ለመሄድ ከፈለጋችሁ በመልክ ባታውቁኝም ‹‹ዩዲ›› ካላችሁኝ የሐበሻ ፈገግታ እና ሰላምታ ሳቀርብ እኔ መሆኔን እወቁ፡፡ ይቺ የሲኦል የመግባብያ ኮዳችን ትሁን፡፡

እኔ ካለሁበት እስክትመጡ በሲኦል ናፍቆት እጠብቃቹኃለሁ፡፡

ዩዲ ከሐዲ ነኝ ከሲኦል!

የዓመት ሰው ይበለን!

ሚያዝያ 7-8-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ