Get Mystery Box with random crypto!

ስንት_ይሁዳ_እያለላችሁ_እኔን_ለምን_በየዓመቱ ትደበድባላችሁ? /በምናቤ የሳልኩት፣ የይሁዳ ብሶት | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ስንት_ይሁዳ_እያለላችሁ_እኔን_ለምን_በየዓመቱ ትደበድባላችሁ?

/በምናቤ የሳልኩት፣ የይሁዳ ብሶት ከሲኦል/

የዛሬ አምስት ዓመት የተጻፈ!

ክፍል ሁለት /የመጨረሻው/

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ጋይስ ይሁዳ ነኝ! እንዴት ዋላችሁ አደራችሁ ልል ብዬ በሲኦል ቀንና ማታ የሚባል የለም፡፡ ስለዚህ በሲኦል መዋል ማደር የለም በስቃይ መኖር እንጂ፡፡ ይህንን ማመን ካቃታችሁ ስትመጡ አይታችሁ ታምናላችሁ፡፡ አይ ሐበሻ አቤት ወሬ ስትወዱ፡፡ አሁን የእኔን ብላክ ስቶሪ ለመስማት ቸኩላቹኃል አይደል፡፡ ለነገሩ ከእኔ ብትማሩ ባትማሩም ልንገራችሁ ምክንያቱም እኔም ከጌታዬ ስላልተማርኩ፡፡

ዳይ ወደ ገደለው፡፡ እናላችሁ… በሰፈሬ አንበሳ ሳልሆን አደገኛ የዝንጀሮ ገመሬ ሆኜ አደኩ፡፡ በኋላ ያሳደገኝ የአስቆሮቱ አገርና የወላጅ አባቴ የይሁዳ አገር ሰዎች ጦርነት ገጠሙ፡፡ እኔ ሆዬ ምንሽሬን ይቅርታ ቀስቴን ታጥቄ፣ ጦሬን ሰብቄ፣ ጋሻዬን በደረቴ ደቅድቄ ዘመትኩ ጦርነቱም ተጀመረ፡፡

ጥቂት እንደተዋጋን አንድ ጠና ያለ ሰው ‹‹እጅ በአየር፣ መሳርያ በምድር›› ብሎ ሊማርከኝ ፈለገ፡፡ እኔም ዩዲ ‹‹ሳትቀደም ቅደም›› ብዬ ፊቴ የቆመውን ጠና ያለው ሰውዬ ላይ እንደ ነብር በመወርወር ወደቅሁበት፡፡ ሰውዬውም ጥንቢራው ዞሮ እራሱን ሳተ፡፡ እኔ ልምታው መላክ ይቅሰፈው አላወቀም፡፡ ጓደኛዬ ‹‹ዩዲ ሳትሰለብ ስለብ›› አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ዩዲ ጓደኞቼ ይሁዳ የሚለውን ስም ሲያቆላምጡ የሚጠሩኝ ስም ነው፡፡

እኔም ጠና ያለውን ሰውዬ ገድዮ ሰለብኩት፡፡ ምርኮውን ከበዘበዝኩ በኋላ ወደ ጠላት ሰፈር ስገባ አንዲት ጎልማሳ ሴት አግኝቼ ማረኩ፡፡ የማረኳትን ሴት ሚስት ትሆነኝ ብዬ ወሰድኳት፡፡ አብረንም አደርን። መቼም አብረን ስናድር ጣራ ስንቆጥር እንደማናድር ታውቃላችሁ። የሚሆነው ነገር ሁሉ አድርገን አደርን፡፡ ኦህ ዩዲ…ታሳዝናለህ!

ታድያ አብሮ ያደረ ሰው ግለ ታሪክ መጠያየቁ አይቀርምና ያገሬውን የወንዜውን አውርተን ወደ ራሳችን ታሪክ መጣን፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ያቺ የማረኳት እንደ ሚስትም ያደረኳት ሴት ወላጅ እናቴ ሆና ተገኘች፡፡ እኔም ልጇ ሆኜ እርፍ አልኩት፡፡

በጦርነቱም ወቅት የገደልኩትና ብልቱን የሰለብኩት ጠና ያለ ሰውዬም ወላጅ አባቴ መሆኑን አወኩ። የነብዩ የእንባቆም ትንቢትም "እናቱን ያገባል፣ አባቱን ይገድላል ይሰልባል" የተባለው ጠብ ሳይል በእኔ ተፈጸመ።

ያ ድራማቲክ የመሰለ ሕይወት በእኔ ሲከሰት ግራ በመጋባት እጅግ ተጨነኩ፡፡ ያ ዘመን ደግሞ ጌታችሁ መጥቶ ወንጌል የሚያስተምርበት፣ ድውያንን የሚፈውስበት በአጠቃላይ ጌታችሁ በኢየሩሳሌም ልዩ ክስተት የነበረበት ዘመን ስለሆነ ከማዙካ ጋር ተነጋግረን በሼም የታጠረውን ታሪካችንን ይዘን ወደ ጌታ መጭ አልን፡፡ ወደ ጌታችሁ ለመሄድ የወሰነው ኃጢአተኞችን ያቀርባል፣ ይቅር ይላል፣ ሲበዛ ሰው ወዳድ ነው የማለውን ወሬ ሰምተን ነው።

ጌታ ጋር ደርሰን ያለውን ሂስቶሪ ዋን ባይ ዋን ነገርነው፡፡ ጌታም በገጠመን ነገር እኛን ከመኮነን ይልቅ በማዘን አጽናናን፤ ብዙ መከረን አስተማረን፡፡ በተለይ እኔን ዓይን ዓይኔን እያየ ሲናገረኝ ነብሴ ትንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ያ የሐዘኔታና ‹‹ትሸጠኛለህ›› የሚል ዕይታው ዛሬም ድረስ በሲኦል ውልብ ይልብኛል፡፡

ጌታችሁም ሳያሳፍረን/ጌታችሁ የምለው ጌታዬ ብዬ ለመጥራት በሥራዬ ስለማፍር ነው/ ማዙካን ከሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳን አንስት፤ እኔንም ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ቆጠረን፡፡ ለእኔም እንደ ጓደኞቼ ስልጣን ጸጋን ሰጠኝ፡፡

ምን ዋጋ አለው እኔ ሁሌ ምሾፈው ስልጣኔን፣ ጸጋዬን ሳይሆን እንደ ዘመኑ አንዳንድ ካህናትና አስተዳዳሪዎች በሙዳየ ምጽዋት ውስጥ የምትገባውን ጨላ ብቻ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ጌታችሁ በሰጠኝ ስልጣንና ጸጋ ድውይ ስፈውስ፣ ለምጽ ሳነጻ አጋንንት ሳስወጣ እንደነበር ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?

በተለይ አንድ ቀን እንዴት እንደተናደድኩ ልነግራችሁ አልችልም፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ በዛ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ተጋብዘን፤ ከጌታችሁ ጋር ሰብሰብ ብለን እያለን አንዲት ሴት በውድ ዋጋ የተገዛ ሽቱ ይዛ ከች አለች፡፡ አልባስጥሮስ ሽቱውን ስከልመው ፐ ብሸጠው ብዬ ጆፌዬን ጣልኩበት፡፡

ልጅቷም ተአምረኛ ነች ያንን ሁሉ ሽቱ ጌታዋ ላይ አርከፈከፈችው፡፡ እኔ ዝም ብዬ ከልማታለሁ፡፡ እሷም አውቃለች መሰለኝ በቆረጣ እያየችኝ ሽቶውን በሙሉ ጌታ ላይ አርከፍክፋ ስትጨርስ ይባስ ብላ የጌታዋን እግር በእንሳዋ አበሰችው፡፡ ዞር ብዬ ስሾፍ ጌታችሁ ላይ ያርከፈከፈችውን ሽቶ ባዶ ጠርሙሱን እግሬ ስር ጣለችው። በጣም ተናድጄ "ቁረሌው መሰልካት እንዴ ሽቶ የሌለውን ባዶ ጠርሙስ እግሬ ስር የምትጥለው" ብዬ ልናገራት አልኩና ጌታችሁን ፈርቼ ተውኩት።

በተለይ የሽቱው ብልቃጥ ባዶውን መሬት ላይ ሆኖ ስከልም በቅናት ተቃጠልኩ፡፡ መሬት መሬቱን እያየሁ ለጌታችሁ አንድ ሐሳብ አቀረብኩለት ‹‹ይህ በብዙ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር›› ብዬ አዛኝ አንጓች ሆንኩ፡፡ ጌታችሁም ነውር የነበረ ንግግሬን በፍቅር ‹‹ድሆች ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉ፣ እኔ ግን ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም›› ብሎ ሴቲቱን መልካም ሥራ እንደሠራች በሁላችን ፊት አመሰገናት፡፡ ካላመናችሁ ማቴ 26÷6-13 አንብቡ፡፡

ጭራሽ ያደረገችው ነገር ‹‹ወንጌል በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ለመታሰብያ ይሆናል›› ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት፡፡ ጉድ በል ሳጥናኤል….ከዛማ የእኔ ነገር ጨላ ላይ ማፍጠጥ፤ ካዝና ላይ ማጉረጥረጥ ሆነ፡፡ ከመቶ አስሬን እየቦጨኩ ፍራንካውን እንዲው ላልበላው መቀገር ሆነ ሥራዬ፡፡ በገንዘብ እና በሰይጣን መለከፍ አያድርስ ነው!

የሚገርማችሁ አሁን በየ ቤተ ክርስትያኑ ያሉ አገልጋይ ሳይሆኑ ተገልጋዮች ሙዳየ ምጽዋት እየከለሙ መገልበጥ መስረቅ የጀመሩት ከእኔ ኮርጀው ነው፡፡ አሁን ባልጠፋ ነገር እኔን ለሲኦል ዳፋ የዳረገኝን ነገር ከእኔ አይማሩ? ለዚህ እኮ ነው ‹‹ስንት ይሁዳ እያለላችሁ፤ ለምን እኔን በየዓመቱ ትወግራላችሁ›› የምለው፡፡ የምር በየ በተስክያኑ ስንት የሚወገር አስተዳዳሪ፣ ሒሳብ ሹም፣ ጸሐፊ፣ ተቆጣጣሪ፣ ጨላ ቆጣሪ አለላችሁ፡፡

ኤኒ ወይስ ችግር የለውም እያንዳንድሽ እኔ ጋር ስትመጪ የሙዳየ ምጽዋዕት ገንዘብ ገልብጠሸ፣ ቆጥረሽ የበላሽ ሁላ መከራሽን ትቆጥርያለሽ፡፡ ማን የሚሉት ዘፋኝ ነው ‹‹እኛን ነው ማየት ስትመጪ እሱ ብሎት፤ ለጉድ ተናንቀን በእንባ አንገት ላንገት›› ያለው፡፡ ጌታችሁ ሳይሆን ሥራችሁ ፈርዶባችሁ ሲኦል ስትመጡ ተቃቅፈን እንደምንላቀስ ተስፋ አለኝ፡፡

ከዚህ በኋላማ በውስጤ የጌታችሁ ፍቅር ሳይሆን የጨላ ፍቅር አደረ፡፡ ነጋ ጠባ ስለ ገንዘብ ነው የማስበው፡፡ ከመቶ አሥር የማገኘው አልበቃ ሲለኝ ከሐዋርያት ልቀፍል እፈልግ ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው እነሱ ጋር የማይነጠቅ የጌታቸው ጸጋና ፍቅር እንጂ የሚቀፈል ጨላ የላቸውም፡፡

ትዝ ይለኛል! የጸሎተ ሐሙስ ቀን ጌታችሁን ከጓደኞቼ ጋር ግራ ቀኝ ከበነው የመጨረሻ እራት እየበላን ሳለን፤ እኔ የጨላ ከረጢቴን ይዤ ዱቅ እንዳልኩ ጌታችሁን ሳየው አንድ ነገር እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ ጌታችሁም ‹‹ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይተጠኛል›› አለ፡፡ ጌታችሁ ይወደው የነበረው ዮሐንስ የሚባለው ወደ ጌታ ደረት ጠጋ ብሎ ‹‹ጌታ ሆይ ማነው›› አለው፡፡ ሐዋርያትም እጅግ ተጨነቁ "እኔ እሆን እኔ እሆን" እያሉ ታወኩ፡፡